wol city edited

ብልጽግና ፓርቲ “የማያዉቃት” ታሪካዊቷ ዎላይታ ሶዶ… (በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተጋባዥ ጸሓፊ)

By Journalist Natnael Gecho

Design by Journalist Natnael Gecho

በፖለቲካ አለም willful ignorance የሚባል ነገር አለ እና ይሄን ለምን እንዳነሳሁ እመለስበታለሁ። በቅርቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ደረጃ ከተማነት ጎንደርና ጅማን በታሪካዊነታቸዉ ምክንያት አጭቻለሁ ማለቱ ይታወሳል።

በእዉነቱ ከተሞች ለሁለተኛ ደረጃ ከተማነት በምን አይነት መሥፈርቶች ይመረጡ የሚለዉ ሰፊ ርዕስ ነዉና እሱን ትተን፣ የተጠቀሱት ከተሞች ታሪካዊነታቸዉ የሚካድ አይደለም። በቅርስም ደረጃ ጎንደር በፋሲል ቤተመንግስት፣ ጅማም በአባጅፋር ቤተመንግሥት ትታወቃለች።

የበርካታ ነገስታት ምድር የሆነችዉ ዎላይታ ሶዶ መሰል ቤተመንግስትሽ የት አለ ከተባለች ዛሬ ላይ የላትም። ይህ የሆነዉ በአጼ ምኒልክ ምክንያት ነው በወረራዉ መጨረሻ፣ በዎላይታ ሶዶ ዳልቦ የሚገኝ ቤተመንግሥት በእሳት ጦሩ አጋይቷል፣ እሳቱም ያወደመዉ ንብረት ከትልቅነቱ የተነሳ እስከ ሶስተኛዉ ቀን ጭሱ ይወጣ ነበር።

ስለዚህ ዛሬ ላይ በምንም መንገድ ቤተመንግሥት የለሽም ተብላ ዎላይታ ሶዶ ምንም የምትከለከልበት አመክንዮ አይሰራም፣ ምክንያቱም ቅርሷን ያወደመባት ሚኒልክ ነዉና። በተጨማሪ ይህንን የቅርስ ዉድመት ለማስታወስ በቦታዉ ደረጃዉን የጠበቀ የዎላይታ ብሔራዊ ሙዚየም መገንባት አለበት፣ ይህ የወደመዉን ቅርስ ባይተካም እንኳን ትልቅ ትርጉምፐየሚሰጠዉ ነው።

ሌላዉ የዎላይታ ሶዶ አስገራሚ ቅርስ ሞቼ ና ቦራጎ ጎንጎሏ (የሞቼ ልጅ የቦራጎ ዋሻ) ነው። ይህ ከ74ሺ አመት በፊት ሰዉ እንደኖረበት የሚነገርለት ዋሻ የከተማዋ አካል ነው። አሁንም ጥናት እየተካሄደ ቢሆንም፣ ዋሻዉ አሁንም ኢትዮጵያ አሏት ከሚባሉ ትልቅ ሐብቶች አንዱ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተለይ መሠረተ ልማት ከተሟላለትና በደምብ ከተዋወቀ ትልቅ የቱሪዝም ሐብት ነው።

ሌላዉ የከተማዋ ታሪካዊ የተፈጥሮ ሐብት የሆነዉ በቀድሞ የዳሞት ኪንግደም መጠራቱን የቀጠለዉ የዳሞታ ተራራ ነው። ይህ ተራራ አቡነ ተክለኃይማኖት፣ ሳሶ ሞቶሌ የሚባለዉን የዳሞት ንጉስ ያጠመቁበት ቦታም ይገኝበታል። በቅርቡ ወደ ተራራዉ የሚያወጣ 10ሺ ደረጃ የመሥራት ሐሳብ ተነስቶ መነጋገሪያ እንደነበረ ይታወሳል። ግምባታዉ እዉን ከሆነ ተጨማሪ የቱሪስት መስህብ ከመሆን አልፎ፣ በተለይ በመብራት እንዲንቆጠቆጥ ከተደረገ በምሽት የከተማዋን ገጽታ ይቀይራል።

ዎላይታ የታሪክ እና የጀግኖች ሐብታም በመሆኑ ወደፊት በከተማዉ እምብርት ቦታዎች ላይ መንገድ ዳር ፓርኮችን በመስራት የሳሶ ሞቶሌን በአንድ ቦታ፣ የካዎ ጦናን በሌላ ቦታ ሐዉልቶችን አሁን አለም ላይ ከፍተኛ በሚባል የጥራት ደረጃ በመገንባት ቅርስ ማስቀመጥ ይቻላል። ሌሎችም ፍሬዉ አልታዬ፣ አቡነ ጴጥሮስ እንዲሁም አባባ ዋንዳሮና የመሳሰሉትን የሚዘክሩ ሐዉልቶችን በመሥራት ከተማዋን የታሪክ ሐብቷን በአግባቡ እንድትገልፅና እንድትጠቀም ማድረግ ይቻላል።

አንድ ደግሞ የብልጽግና ሰዎች የሚቀልዱት ዘመኑን የማይመጥን ሁዋላ ቀር ቀልድ አለ; ዎላይታ ሶዶ ሐይቅ የላትም የሚል። ለማንኛውም በ New York ከተማዉ central park ስንት ሰዉ ሰራሽ ሐይቅ አለ? አዲስ አበባስ ሐይቅ አላት ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች ጣል አድርገንላቸዉ፣ በአሁኑ ሰአት አንድ ታታሪ ወጣት በከተማዋ በፈጠረዉ ጁኒየን በሚባል ፓርክ ጀልባ የሚንሸራሸርበትን ሰዉ ሰራሽ ሐይቅ መፍጠሩንም እናስታዉሳቸዉ።

በአለም ደረጃ ቱዝላ፣ ባርሴሎና እንዲሁም አምስተርዳም ከተሞች አስደማሚ ሰዉ ሰራሽ ሐይቆችን ሰርተዉ ትልቅ የቱሪስት መስህብ አግኝተዋል። በነገራችን ላይ ለዎላይታ ሶዶ ብቻ ሳይሆን ለአዲስ አበባም ቢታሰብ ጥሩ ነው። በጤናማ አዕምሮ ለሚያስብ ለየትኛዉም ኢትዮጵያዊ በተለይ በታሪክና በተፈጥሮ ሐብቷ ዎላይታ ሶዶ የምሥራቅ አፍሪካ ፈርጥ እንደሆነች ግልጽ ነው።

እጅግ ምቹ የአየር ጸባይ፣ ወባ የሌለባት በመሆኗ ለሐገር ዉስጥም ሆነ ለዉጪ እንግዳ አስተማማኝ መዳረሻ ነች። ዎላይታ ሶዶ ያላት የማደግ እምቅ አቅም ከሕዝቧ ታታሪነት፣ ባህሉን አክባሪነትና ከእንግዳ ተቀባይነቱ ጋር ተደምሮ ነገዋ ብሩህ መሆኑን በማስረገጥ የፖለቲካ ተንኮሉን በንቀት ወደታች ይመለከታል።

እናም ቅድም willful ignorance ያልኩት ብልጽግና ይሄ ኢትዮጵያ በኩራት ለአለም ልታሳይ የሚገባት የአንድ ከተማዋ ሐብት ጠፍቶት ሳይሆን በፖለቲካ ሸፍጥ ነው ከተማዋን የሚሸሻት ልላችሁ ነው። ሸፍጥ የትም አያደርስም፣ የዎላይታም ሕዝብ ለዘመናት በሌሎች ቀዬ ከተማ እያለማ ሲባረር የኖረበት ታሪክ አይደገምም!!!!

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita