የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ወደ መደበኛ ስራ ለመግባት የሚያስችል ቅድመ እንቅስቃሴ እያጠናቀቀ ይገኛል።

ባለፈው ሳምንት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት በህጋዊነት መዝግቦ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ በማካተት በህጋዊነት ለመስራት የሚያስችል ፍቃድ በ22/10/ 2013 ዓ.ም በባለስልጣኑ አዲሱ አዋጅ ቁጥር መሰረት የሚያስፈልጉ ቅድሜ ሁኔታዎችን በማሟላቱ በክልሉ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያ ሚዲያ መሆኑ ይታወቃል።

ያንን መነሻ በማድረግ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ወደ መደበኛ ስራ ለመግባት የሚያስችል ቅድመ እንቅስቃሴ እያጠናቀቀ ዋና ቢሮን በዎላይታ ሶዶ ከተማ በ21 ማዞሪያ ወደ መርካቶ ገበያ መግቢያ ባለው ቶኪዮ ህንፃ ሶሶተኛ ፎቅ ላይ መከፈቱን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።

ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም የተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት በውስጥ መስመር ሚዲያው በጅምር ላይ በግለሰብ ደረጃ እያደረገ የሚገኘውን ጥረት ለመደገፍ በጠየቁት መሠረት “በዎላይታ ታይምስ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000417514213 መሆኑን እንገልፃለን።

በቅርቡ በተደራጀ መንገድ ወደ እናንተ እንመለሳለን🙏

ሚዲያ የልማት አንቀሳቃሽ ሞተር ነውና ኑ በጋራ እንስራ🙏

Wolaita Times, 30/10/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹