ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሌሎችም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስደረጉበት ሆስፒታል ላይ ኩላሊቱ ከየት የመጣ ነው በሚል ምርመራ መጀመሩ ተገለፀ።

የኬኒያ መንግስት ከሀገር ውስጥ ለጋሾች የሚገኝ ኩላሊት ለውጭ ዜጎች ንቅለ ተከላ እየተከናወነ ስለመሆኑ በቀረበ ቅሬታ በኤልዶሬት የሚገኘውን የሜዲሄል ሆስፒታል ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
የኬንያ የጤና ሚኒስትር በኬንያ እየተፈፀመ ነው የተባለውን ህገ-ወጥ የኩላሊት ንቅለ ተከላ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በ2023 ከንቅለ ተከላ ማኅበሩ የተለያዩ ጥቆማዎች ደርሰውት የምርመራ ቡድን አዋቅሮ የምርመራ ሥራ መስራቱንም አስታውሷል።
በተለይ ቅሬታ የቀረበበት “ሚድሂል” የተሰኘው ሆስፒታል ደረጃ 5 ሆስፒታል መሆኑንና ፍቃዱን ካገኘ በኋላ ባለፉት 5 አመታት እስከ 2023 ድረስ 372 የኩላሊት ንቅለ ተከላዎችን ማከናወኑን ጠቅሷል።
አብዛኞቹ ንቅለ ተከላዎች የተደረገላቸው የኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ፣ኮንጎ እና ሶማሊያ ዜጎች መሆናቸውንና የአውስትራሊያ፣ እስራኤል፣ ጃፓን፣ አሜሪካ እና የእንግሊዝ ዜጎችም ንቅለ ተከላ እንደተደረገላቸውም ይጠቅሳል።
ሆኖም በሆስፒታሉ በኩላሊት ሰጪውና ተቀባዩ መካከል ያለው ግንኙነት በአብዛኛው ግልፅ ያልሆነ እና አስፈላጊ ዶክመንቶች ያላካተተ ስለመሆኑ መግኝቱ መጠቀሱንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በተጨማሪም ሆስፒታሉ የሞት ሪፖርቶችን የማይመዘግብና የዲሲፕሊን ኮሚቴ ስብሰባም አለመደረጉን ያነሳ ሲሆን ያለ ጤና ሚኒስቴር ፈቃድም የሰው ናሙና ምርመራዎች በህንድ ሃገር እንዲመረመሩ ስለመደረጉ ይጠቅሳል።
በዚህ ግኝት ላይ የሚፈርሙት የስምምነት ውል በቋንቋቸው አለመተርጎሙ ሌሎች መሰል ግኝቶች ቢገኙም የተቋቋመው ኮሚቴ ህገወጥ ንቅለ ተከላ እንዳለ ከመጠርጠር ውጪ አስተማማኝ ማስረጃ አለማግኘቱን አንስቷል።
ኮሚቴው በወቅቱ ለንቅለ ተከላ ከውጪ የሚመጡ ሰዎች በማዕከል እንዲመዘገቡ እና አስፈላጊ ዶክመንቶችን እንዲያቀርቡ፤ የተሻለ የጤና ስርዓት ካለባቸው ሀገራት የሚመጡ ደግሞ የአካል ዝውውር ወንጀል ሊፈፀም ስለሚችል በተገቢው አካል እንዲጣራ ምክረ ሃሳብ ቀርቦ ነበር።
የኬንያ የጤና ሚኒስትር ሚድሂል ሆስፒታልን ጨምሮ በሀገሪቱ የንቅለ ተከላ ህክምና እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው 7 የጤና ተቋማት ደኅንነታቸውን እና ከህጉ ጋር እንደሚሰሩ ለማረጋገጥ ክትትል እንደሚያደርግም አስታውቋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏