የፍ/ቤት እግድ እና ክርክር ባለበት የማዕድን መገኛ መሬት ላይ አልሚዎች በህገወጥ መንገድ የማዕድን ቁፋሮ እንዲያደርጉ መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን የማራ ማይነርስ የማዕድን ምርመራና ማምረት ሥራ ድርጅት አስታወቀ።

“በከሳሽ ብርሃነመስቀል ክንፈ የማራ ማይነርስ የማዕድን ምርመራና ማምረት ሥራ ድርጅት እና በተከሳሽ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዉሃ ማእዲንና እነርጂ ቢሮ መካከል የነበረው ዉዝግብ እልባት አገኘ” በሚል ከሁለት ሳምንት በፊት በቢሮው አማካይነት በማህበራዊ ሚዲያው መገለፁ ሀሰተኛ መረጃ ሲሆን ህገወጥ ስለመሆኑ ድርጅቱ ቅሬታ አቅርቧል።
የፌድራል የመጀመሪየ ደረጃ ፍርድ ቤት በ6/8/17 ዓ/ም የተፃፈ የዕግድ አቤቱታ በቀረበው አቤቱታ መነሻ የዋለው ችሎት ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪሰጥ በመ/ቁጥር 10544 መሠረት በስር ፍርድቤት በ17/7/17 ዓ/ም የተሰጠ የዕግድ ማንሳት ውሳኔ ሳይፈፀም ታግዶ እንዲቆይ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 332 እና 335 መሰረት ታዟል” በሚል ወሳኔ ሰጥቷል።
ፍርድቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ ሳይሰጥበት በእግድ ክርክር ወቅት ተይዞ በነበረው መሬት ላይ በአሁኑ ወቅት ሌሎች አልሚዎች በህገወጥ መንገድ የማዕድን ቁፋሮ እያደረጉ ስለመሆኑም ድርጅቱ አክለው አስታውቋል።


ፍርድቤቱ የስር ፍርድቤት ዕግድ ውሳኔ ስሽር “የሥር ፍ/ቤት ዕግዱ ቢቀር መ/ሰጪ ላይ የሚደርስ ጉዳት አልነበረም፣ በእግዱ ጊዜ የተሰሩ ተግባራት ህገ ወጥ ሊሆን ይገባል። መጣሳቸውን ፍ/ቤቱም አረጋግጠዋል፡፡ እግዱ እየተነሳ ከሆነ የፍሬ ነገር ክርክሩም ትርጉም አይኖረውም፡፡ እግዱ ሊነሳ የማይገባው ገና ክሱ እልባት አላገኘም። እግድ ተሰጥቶ እያለ ፍ/ቤቴ እዚህ ላይ እርምጃ ሳይወስድ ብቻ ዕግድ ማንሳቱ ተገቢ አይደለም” ብሏል።
በመሆኑም አሁንም ክልሉ ህገወጥ ተግባር ከመፈፀም ህጋዊ መንገድ በመከተል ለሚነሱ መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏