በዞናችን ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮች ከተለምዷዊ የእርሻ አስተራረስ ዘዴ ተላቆ በመካናይዜሽን ማሳቸውን በትራክተር የማሳረስ ልምዱ ከዓመት ዓመት እየጨመረ መጥቷል አለ የወላይታ ዞን እር/ተፈ/ኃ/ ልማት መምሪያ።
ለዚሁ ማሳያ ይሆን ዘንድ በ2012 ዓ/ም በልግ በ2 እና ሶስት ሺህ ሄክታር በትራክቴር ይታረስ የነበረው ማሳ በተያዘው ምርት ዘመን በልግ ወቅት ላይ ከ18 ሺህ ሄክታር ማሳ በላይ በትራክተር የታረሰ ሲሆን ከ45_50 ትራክተሮችን በኪራይ ከኦሮማያ፣ ከሲዳማ፣ ከሃድያ እና ከግል ኢንቨስቴሮች ተወስዶ ታርሷል ብለዋ የወላይታ ዞን እር/ ተፈ/ኃ/ ልማት የመምሪ ኃለፊ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማሪያም።
የቲራክቴሮቹ ኪራይ በ2012 ዓ/ም አንድ ሄክታር ከ 2000_2500 ብር ሲሆን ዘንድሮ አማካይ ዋጋ በሄ/ር 3000 እና ከዛ በላይ ቢሆንም የአርሶ አደሩ ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ባመቻቸው 30 በ70 ብድር እንደሌሎች ዞኖች ዞናችንም ተጠቃሚ እንድሆን ዕቅድ አቅደን ስንሰራ የቆየን ቢሆንም እዚህ ግባ የሚባል ስራ አልተሰራም፤ ከዕቅዳችንና ከጎረበት ዞኖች አፈፃፀም አንጻር እጅግ ዝቅተኛ ነው።
ለአብነት ኪንዶ ኮይሻ ላይ የአንድ ማዕከል ሱቅ ባለበት አቶ ተሾሜ አላሮ 3 ትራክቴር በአንድ ላይ ባለፈው ሳምንት ዱጉኖ ፋንጎ ወረዳ እነ አርሶ አደር ማሞ 1 ትራክቴር ያስገቡ ሲሆን ኦፋ ላይ በማህበር የተደራጁ ሶስት ማህበራት የኢንቨስትሜንት ፈቃድ ለማውጣት በጥቃቅን ችግሮች የተያዙ ሲሆን ከሚመለክታቸው አካላት ጋር በውይይት ለመፍታት በሂደት ላይ ይገኛል።
ከዚህም በተጨማሪ የዎላይታ ዳሞታ ዩኒየን 4 ትራክተር ለመግዛት ጫረታ ላይ ከመኖሩም በላይ ከATA ጋርዚያቶ በመሆን የመለዋወጫና የስልጠና ማዕከል ግንባታ በሶዶ ከተማ ፑንዱኒያ ላይ ከ15 ሚሊየን ብር ወጪ ወጥቶ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል።
እንደነ ዱጉና ፋንጎ፣ አባላ አባያ፣ ኪንዶ ኮይሻ፣ ሆብቻ፣ ዳሞት ወይዴ፣ ቦሎሶ ቦምቤ፣ ሁምቦ፣ ኦፋ፣ ዳሞት ሶሬና ሁሉም ወረዳዎች የመሄሩ ዕቅድ አካል አድርጎ እንድፈፅሙ ብደረግ።
ትራክተር መግዛት የትኛውንም ዓይነት የንግድ ተሽከሪካሪ ከመግዛት ይበልጣል።
አንድ ትራክቴር በቀን ከ20 ሺህ ብር በላይ ገቢ ያስገኛል አንድ አውቶብስ ግን ግማሽ ያህሉን አይሸፍንም በሌላ በኩል ለእርሻ በሬ የግጦሽ ቦታ ካለመኖሩ ጋር አርሶ አደሩ ለመኖ መቸገሩ በተከፈተው በር ተጠቃሚ እንድሆኑ አመራሩና ባለሙያ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።
Wolaita Times, 05/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹