1000053201

የዎላይታ ዉሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ፈጣን ስኬታማ ጉዞ ምን ያስተምረናል?

(በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተጋባዥ ጸሓፊ)

“ይህንን ለመጻፍ ያነሳሳኝ በዎላይታ ቴሌቪዥን ስለ ድርጅቱ ተሰናድቶ አየር ላይ ከተወሰኑ ወራት በፊት የዋለ አንድ ፕሮግራም ነው። ድርጅቱን ያቋቋመዉ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ ነው።

ድርጅቱ ከዞኑ አልፎ በአጎራባች ክልሎች ሳይቀር ዉጤታማ ሥራዎችን ሰርቶ ፕሮጀክቶችን በታቀደላቸዉ ጊዜ በመፈጸም ተመስክሮለታል። ድርጅቱም በጥሩ ሁኔታ ትርፋማ መሆኑም ተገልጿል።

ይህ በጣም አበረታችና ተሞክሮዉ ወደሌሎች ዘርፎችም መሸጋገር ያለበት ተግባር ነው። ለምሳሌ ትልልቅ የሕንጻ፣ እንዲሁም የመንገድ ተቋራጮችን፣ አማካሪ ድርጅቶችንም በማቋቋም በአካባቢው የሚሰሩ የመሠረተ ልማት ግምባታዎችን መሥራት ያስፈልጋል።

በተለይ የዎላይታ ሕዝብ ስኬት በከፍተኛ ደረጃ ተቋማት ግንባታና የቡድን ሥራ ጋር የተያያዘ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፣ ያለን ብዙ የተማረና ለየትኛዉም ሥራ ዝግጁ የሆነ የሰዉ ሃይል መባከን የለበትም።

መሰል ትልልቅ ድርጅቶች የእዉቀት ሽግግር እና የሥራ እድል ፈጠራ በተጨማሪ የከፍተኛ ሐብት ምንጭም እንደሆኑ በማወቅ መንቀሳቀስ ይገባል፣ ሌሎችንም ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች መዘርዘር ይቻላል።

በደምብ የደረጀ አቅም መፍጠር ከተቻለ ወደ አጎራባች እንዲሁም መላዉ ኢትዮጵያዊ በተጨማሪም በአፍሪካ እንዲሁም በአለም ዉስጥ ስም ያላቸዉን ድርጅቶችን ከመፍጠር የሚያግደን የለም።

በደቡብ ኢትዮጵያም ደረጃ ስናይ ተመሳሳይ ችግር አለ፣ በቅርቡ እንኳን በስድስት ከተሞች የሚገነቡ የክልል ቢሮዎች ሕንጻዎች ግንባታ ለሌሎች ኮንሥትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተሰጥቷል፣ የቢሊየን ብሮች ፕሮጀክት መሆኑን ልብ በሉ። ይህ በግልጽ የክልሉ አግይ አካሄድ የሚያሳይ በመሆኑ መስተካከል አለበት።

በአካባቢው ያለዉ ብዙ የተማረ ኃይል በጠንካራ ድርጅቶች ታቅፎ አካባቢውን እንዲገነባ ማድረግ ይገባል። ትንሽም ትልቅም ሥራዎችን በራስ አቅም ለመወጣት በትኩረት መሥራት ይገባል። ታዲያ የሚገነቡ ድርጅቶች የጥራት ችግርና ለሐብት ብክነት እንዳይጋለጡ በጥንቃቄ መሥራት ያስፈልጋል።

ከመንግሥት ለአካባቢው የሚመደበዉ ገንዘብ ወደ ነባር የሐብት ቅርጫቶች ተመልሶ እንዳይገባና የክልሉ ሕዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የመሰል ድርጅቶች ሚና የጎላ ነውና በተጨማሪም ተወዳዳሪ ተቋማት በሐገር ደረጃም ትርጉማቸዉ ብዙ ስለሆነ በክልልም በዞንም ደረጃ የሚመለከታቸዉ አካላት፣ ከዎላይታ ዉሃ ሥራዎች ድርጅት በመማር መንቀሳቀስ አለባቸዉ።”

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባገኘነው መረጃ መሠረት ይሄው ግዙፉ ሀገርአቀፍ ተወዳዳሪነትን በአጭር ጊዜ ያረጋገጠው የዎላይታ ውሃ ስራዎች ከተቋቋመበት አጭር ጊዜ በተግባር ልቆ በመገኘት ያከናወናቸው እና እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ለመጥቀስ ያህል 👇

  1. የኢትዮጵያ መብራት ሃይል አገልግሎት የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት፣
  2. የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ የመጠጥ ውሃ መስመሮች ማዛወሪያ ፕሮጀክት፣
  3. የበቅሎ ሰኞ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣
  4. የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳውሮ ተርጫ ካምፓስ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት፣
  5. የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ካምፓስ የመጠጥ ውሃ መስመር ማዛወሪያ ፕሮጀክት፣
  6. የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እና ዋና ፖሊስ ጣቢያ ግንባታ ስራ፣ የመርካቶ ፊልም አዳራሽ ግንባታና ጥገና ስራ፣ ሊጋባ ፓርክ ኮሪደር ልማት፣ ፑንዱንያ 9ኛ የከተሞች ፎረም ዝግጅት፣ የማዘጋጃ ካዳስተር ህንጻ ግንባታ፣
  7. በጉራጌ ዞን እምድብር ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት፣
  8. በስልጤ ዞን ሙርጡጤ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት፣
  9. ከንባታ ዞን ኤራራሞ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት፣
  10. ጉራጌ ዞን ሜጌቻ 2 መካከለኛ የመስኖ ፕሮጀክት፣
  11. ባስኬቶ ዞን ሺኖ ኤርጌኖ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት፣
  12. ሀዲያ ዞን ሀንዶሼ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት፣
  13. ፖንድ ስራ በአራት ዞኖች በአላባ፣ ሃዲያ፣ ከንባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን የማህበረሰብ ኩሬ መስኖ ፕሮጀክት፣
  14. በዎላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ ካሬታ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት፣
  15. ሃዲያ ዞን ኤልኮሜ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት፣
  16. የ30 እና ዮሐንስ መንደሮች የመጀመሪያ ዙር የውሃ መስመር ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣
  17. ሃዲያ ዞን አጃቾ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት
  18. ስልጤ ዞን የውል ባረግ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት፣
  19. የጎፋ ዞን ሎማቴ መካከለኛ መስኖ ፕሮጀክት፣

21.ዳውሮ ዞን አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት፣

  1. ቦንጋ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት፣
  2. የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቢሮ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት፣ አርዳይታ፣ ታማ ሻሎ፣
  3. የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቢሮ ጥገና እና ጊቢ የማስዋብ ስራ፣
  4. በዎላይታ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ጊቢ የማስዋብ ስራ፤ ጉተራ አዳራሽ ፋውንቴን ስራዎች በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው። ይሄው የዎላይታ ዉሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ከላይ የተጠቀሱትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶችንም በራሱ አቅም እና በተዋቀረው ጠንካራ አደረጃጀት በጊዜ እና በጥራት በማጠናቀቅ በታማኝነት በማስረከብ የሚታወቅ አንቱታን ያተረፈ ግዙፍ አላማ የሰነቀ በርካቶችን ያሳተፈ ተቋም እንደሆነ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ግዙፉ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የገቢ አቅሙን ለማሳደግና ለተማረው የሰው ሀይል ስራ እድል መፍጠርን ዋንኛ አላማው አድርጎ ተመስርቶ ከተዋቀረ በአጭር ጊዜ ውስጥ በየቦታው እየታዩ ያሉትን የፕሮጀክቶች አለመጠናቀቅን በጥራት እንዲሁም በተወጠነለት ጊዜ በማጠናቀቅ መንግስት ላይ ያለውን ጫና መቀነስ እና ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚ ማድረግ የሚለውን በተግባር እያሳየ ያለ ድርጅት መሆኑን በበርካታ ተቋማት ዘንድ ተመራጭ እንዲሆን እያደረገ ስለመሆኑ በቅርበት የሚያውቁት ይመሰክራሉ።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia