1000053413

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቢሮዎች “መረጃ እየሰጡ ነው” በሚል አብዛኞቹ ንፁሐን የዎላይታ ተወላጆችና ሌሎችም እየተሰደዱ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በክልሉ በዎላይታ ሶዶ የሚገኙ የክልል ቢሮዎች ውስጥ ከ20 ፐርሰንት ያነሰ የሰው ኃይል ብቻ ተገድበዉ እንዲሰሩ ስገደዱ ለሌሎች ማዕከላት ከ90 ፐርሰንት በላይ በአድሎ መፈቀዱም አነጋጋሪ ሆኗል።

አሁን አሁን ለጠላት “መረጃ አውጥተዋል” በሚል በተለያዩ ቢሮዎች የሚሰሩ ስደት እየደረሰባቸው እንዳለ የብሔሩ እንዲሁም ሌሎች ምሁራኖች የገለፁ ሲሆን ከዚህ ቀደም በክልሉ ህዝቦች ላይ ከፍተኛ በደልና የኢኮኖሚ ምዝበራ እያካሄደ መሆኑን በተደጋጋሚ በመረጃ አስደግፈን መግለፃችን ይታወሳል።

ለአብነት ያህል፦ ክልሉን እርቃኑን ያስቀረው የማአድን ዝሪፊያ፣ በስልጣን ላይ መባለግ፣ የኢንቨስትመንት መሬት ዝሪፊያ በጋሞ አመራሮች እና ኢ-ፍትሃዊ የስልጣን ክፍፍል እና ኢፍትሃዊነት የቢሮ ኃላፊ ምደባ በአንድ ብሄር ተወላጆች መያዙ በጥልቀትና ከሰነድ ጋር መዘገባችን ይታወቃል።

በተለይ ከኢኮኖሚ ምዝበራ ጋር በተያያዘ በአንድ ቢሮ ውስጥ የቢሮ ኃላፊ ከጋሞ፣ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ከጋሞ ሆኖ በተመደቡበት ቢሮዎች ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራና የሀብት ሽሽት እየተደረገ መሆኑን ገልፀን እንደነበረ ይታወሳል።

ከወቅቱ ከተጠቀሱና አሁንም እየቀጠሉ ካሉ ቢሮዎች መካከል ከአርባምንጭ ማዕከል ገቢዎች ቢሮና ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ መሆኑን በወቅቱ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።

በሌላ በኩል በዲላ ክላስተር ገጠር መንገድ ቢሮ፣ አከባቢ ጥበቃ ቢሮ፣ አንዲሁም ውሃ ማአድን ቢሮ መሆናቸውንና በእነዚህ ክላስተር ኃላፊና ፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ከአንድ ብሔር መወከላቸው ከፍተኛ የሀብት ምዝበራ መኖሩን የኢኮኖሚ ቋሚ ኮሚቴና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ማጣራታቸውን ገልፀን ነበረ።

ይህንን መረጃ ከሰራን በኃላ የክልሉ ኢንስፔክሽን ቲም እና ከፌዴራል የመጣ አንድ ስውር ቡድን በተጠቀሱ ቢሮዎች ከፍተኛ ምዝበራ መኖሩን በቅርቡ አረጋግጦ ስለሚሄድ ከውስጥ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትልቁ የፌዴራልና የክልሉ አጣሪ ኮሚቴ ያጣራው ጉዳይ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት 6ቱም ክላስተር የሚሰሩ የዎላይታ ተወላጆች “መረጃ እየሰጣችሁ ነው” በማለት ከቃል ማስጠንቀቂያ አልፎ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራ እንዳለ ከ6ቱም ማዕከል ቢሮዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ አረጋግጧል።

ለደህንነቱ ስሙ እንዳይጠቀስ የተጎጂዎቹ ተወካይ “ይህንን በአሉባልታ ንፁሐንን የዎላይታ ምሁራንንና ሌሎችንም ተረጋግተው እንዳይሰሩ እያሳደደ ያለው ጥቂት የአንድ ሰፈር አመራር ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ እንዲያደርግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የፌደራል አካል እየጠየቅን ይህ የማይሆን ከሆነ አስፈላጊውን እርምጃ እንደምንወስድ በአፅኖት እንጠይቃለን” ብለዋል።

ሁልጊዜ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የሚያቀርባቸው መረጃዎች በምንም መስፈርት ከግለሰቦች ወይንም ከትኛውም ማህበረሰብ ጥላቻ የመነጨ ሳይሆን በሁሉም አከባቢ ህጋዊ እና ፍትሐዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት እንዲኖር እንዲሁም ምቹ ሆነው አድሏዊነት የለለው አመራሮች እንዲፈጠሩ፤ ህብረተሰቡን በእኩልነት የሚያገለግል መዋቅር እንዲዘረጋ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ መታወቅ አለበት።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia