1000053469

“አገልግሎት ማግኘት ከጀመርን ጀምሮ መብራት ይመጣል ይሄዳል፣ ችግሩ ምንድንነው ሰንል የፖለቲካ ምላሽ ነው የሚሰጠን በኃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች ስልጣናቸውን ከማስጠበቅ የዘለለ ምንም እያደረጉልን አይደለም” ሲሉም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርቧል።

ለ20 አመታት በኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ መቆየታቸውን የሚናገሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን ነዋሪዎች ሲሆን “ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ጥያቄያችን ምላሽ አልባ ሆኖብናል” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

“አገልግሎት ማግኘት ከጀመርን ጀምሮ መብራት ይመጣል ይሄዳል፣ ጠፍቶ ለወራት ይቆያል፣ ሲመጣ በደቂቃዎች ይጠፋል፣ ችግሩ ምንድን ነው ሰንል የፖለቲካ ምላሽ ነው የሚሰጠን፣ በሃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች ስልጣናቸውን ከማስጠበቅ የዘለለ ምንም እያደረጉልን አይደለም” ሲሉ ነው የተናገሩት።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አንድ ነዋሪ ችግሩን እስካሁን ታግሰን ለምደነው ቆይተናል፣ አሁን ግን ብሶብናል፣ መጣ ስንል ይጠፋል፣ በቀን 15 ጊዜ ይጠፋል፣ በጣም የሚያሳዝን ነው፣ መብራት ጠፋብን የሚል ሰው ወደ ፖለቲካ እየተወሰደበት ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌትርክ አገልግሎት የኮንሶ ዞን አገልግሎት መስጫ ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ገልሲሞ ኡርማሌ፥ “የማህበረሰቡ ብሶት ይገባናል፣ ችግሩ አለ፣ ይሄ እየሆነ ያለው ግን የኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ በተደረገባቸው አካባቢ የሚኖሩ እና እንስሳት ጠባቂዎች የመብራቱን ስኒ በተደጋጋሚ ስለሚመቱት ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም ” የተለያዩ እፅዋቶች በገመዶች አካባቢ ስላሉ ሲንቀሳቀሱ ይነኩታል፣ በዚህም ይቋረጣል፣ ሰዎችም ዛፎችን ሲቆርጡ ይጥሉበታል፣ እንደነዚህ ባሉ ተደራራቢ ችግሮች ነው የሚቆራረጠው፣ በቀን 15 ጊዜ ይጠፋል የተባለው ስህተት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሥራ አስኪያጁ “ችግሩ በጣም አሳሳቢ ነው፣ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ተቋሙ የሪሃብቴሽን ስራ በመስመሩ ላይ እንዲሰራ ከፌደራል ተወስኖ ጫረታም ወጥቷል፣ ተቋሙም ጥረቶችን እያደረገ ነው፣ መስመሩ እረጅም በመሆኑ ነው አስቸጋሪ የሆነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ማህበረሰቡን አወያይተን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ ገልሲሞ፥ የኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታ በተደረገበት አካባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በገመዶቹ ላይ አላስፈላጊ ድምጽ ሲሰሙ እና ቃጠሎ ነገር ካለ በየቀበሌዎች ላሉ አመራሮች ጥቆማ እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Konso