በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው
ከዚህ በፊት የነበሩ የተለያዩ ልዩነቶች በጋራ ውይይትና እርቅ ተዘግተው ለጋራ ህዝብ ጥቅም በአንድነት ለመሰለፍ ያስችላል የተባለለት ታላቅ ሁሉ አቀፍ ህዝባዊ መድረክ በቅርቡ በዎላይታ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በተለይም ባለፉት አመታት በአካባቢው እየተከሰቱ የሚገኙ ዘርፈብዙ ውስብስብ የህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳይገኝና ለጥቃት እንዲጋለጥ የውስጥ አንድነት ባለመኖሩ በተናጠል ወይንም በጠልፎ የመጣል አካሄድ በተለይም ሰፊውን ህዝብ በእጅጉ የጎዳ በመሆኑ ይሄው ሁሉንም ህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፈው የሰላምና የእርቅ መድረክ በጋራ ጉዳይ በአንድነት ለመቆም ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑም ተነግሯል።
አንድ የዚሁ ታሪካዊ መድረክ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የሆኑት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንደገለፁት “ዝግጅቱ እውን እንዲሆን የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።
በተለይም መድረኩ በተጨባጭ በዞኑ ውስጥና ሌሎች ቦታዎች የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ተወላጆች እንዲሁም በተለያዩ ሀሳብ ልዩነት ውስጥ የሚገኙትን በሙሉ ለማሳተፍ የሚያስችል እንደሆነ አክለው ገልጸዋል።
ጨምረውም የዚህ መድረክ አዘጋጅ ኮሚቴዎች የመጀመሪያ ሆነ የመጨረሻ ግብ በህዝብ ጥቅምና አንድነት ለመፍጠር ከፍተኛ ጉጉትና ያላቸው ከተለያዩ ሀሳብ ልዩነት ያላቸውም ጭምር የተካተቱበት እንደሆነ በማስረዳት በቅርቡ በይፋ ተገልጾ ታሪካዊው መድረክ እንደሚካሄድም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።
ባለፉት ስደትና ሰባት አመታት በአካባቢያችን እየተከሰቱ የሚገኙ ዘርፈብዙ ውስብስብ የህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳይገኝ የውስጥ አንድነት አለመኖር በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ ተወላጆች ከዚህ በፊት የነበሩ የፖለቲካ ሆነ የሀሳብ ልዩነቶችን በአደባባይ በህዝብ ፊት በውይይትና እርቅ በመዝጋት ያለጥላቻ በጋራ ተጋግዘን መጓዝ ይበጀናል፥ የትናንቱ ልዩነትና ቁርሾ እንተወውና ለጋራ አላማ “በአንድነት መቆም ያስፈልጋል” የሚለውን የፀና አቋም በተለያዩ መንገዶች በተደጋጋሚ ማንፀባረቃችን ይታወሳል።
በመሆኑም በቅርቡ ይካሄዳል የተባለው ይሄው ሁሉአቀፍ የሰላምና የእርቅ መድረክ ከፖለቲካ ባሻገር በተጨባጭ የታፈኑ ነገሮችን ነጻ ማዉጣት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ አለመገደብና ማሳተፍ፣ የተሰደዱ ጋዜጠኞችንና እና ሚዲያዉን ነጻ ማዉጣት፣ ባሉ ሕጋዊ መንገዶች ከዞን፣ ክልልና የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕዝቡን ሁሉንም አይነት ሕጋዊ ጥያቄዎች በነጻነት ማንጸባረቅ፣ በዞኑ ተጨባጭ ለዉጦችን ማምጣት፣ ምሁራንን ማሰባሰብ፣ በመልካም አስተዳደር ረገድ ሕዝቡ የሚመሰክርላቸዉን ለዉጦች ማምጣት እንዲሁም ብቁና ህዝባዊ ወግንና ያላቸውን በየዘርፉ የሚያሳትፈውን ሰፊ አውድ ለመፍጠር ዕድል የሚከፍትበት እንዲሆን ትኩረት እንዲሰጠው ከወዲሁ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጥሪ ያቀርባል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
Ethiopia #southethiopia
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው