1000053989

አፈትልኮ የወጣ|By Journalist Natnael Gecho

ቅድመ ዝግጀት ተጠናቅቆ ለክልሉ ካብኔ እና ምክርቤት ይቀርባል የተባለለት ይሄው የክልሉ ቢሮዎችን በትነው ቁጥራቸውን የመቀነስ እንቅስቃሴ መረጃ አፈትልኮ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ደርሰዋል።

እንደ መረጃው ከሆነ ለጊዜው በቅድሚያ ወደ ተግባር የሚገባው የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና የኢንቨስትመንት ቢሮ ወደ አንድ ቢሮ የሚጠቃለሉ ሲሆን የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ እና የወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ደግሞ በተመሳሳይ ወደ አንድ ቢሮነት የሚቀየሩ ይሆናሉ።

በተጨማሪም አፈትልኮ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተበትነው በአንድ ቢሮ ለማደራጀት እንቅስቃሴ መጀመሩን አረጋግጧል።

ክልሉ ከተደራጀ ሁለት አመት ሳይሞላው ወደ ተቋም መበተን እና ብወዛ እንዴት ሊገባ እንደቻለ ተጨባጭ መረጃዎች ባይኖሩም ግን ግለሰቦችን የማጥቃት፣ ተቋማትን ከአከባቢው የማሸሽ ፖለቲካዊ ሴራ ሊሆን እንደሚችል አንድ ከፍተኛ የክልሉን ፖለቲካ የሚከታተል ምሁር አስረድተዋል።

ምሁሩ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩን ሲያብራራ “የዚሁ ከፌደራል ጀምሮ በተዋረድ የመጣውን ተቋም በትኖ ከእንደገና ቁጥር ቀንሶ የማደራጀት ሁኔታ ከህግ አንፃር ተቀባይነት የለለው ከመሆኑም ባሻገር እነኝህን ተቋማት መልሶ ሲደራጁ ደግሞ የት አከባቢ እና በማን እንዲመሩ ይደረጋል የምለው የመጨረሻ ውጤት ሲደርስ ማየት አጠቃላይ የአካሄዱን አላማ ግልጽ የሚያደርግ ይሆናል” ብሏል።

ይሄው በአሁኑ ወቅት ቅድመ ዝግጀት የተጠናቀቀለት የተቋም መበተን እና ብወዛ ለምክርቤት ከመቅረቡ በፊት ለቀጣይ ሮብ ዕለት ለካብኔ ለማቅረብ ቀን ቀጠሮው መያዙንም WT ሚዲያ ከመረጃ ምንጩ አረጋግጧል።

አሁን ባለን መረጃ በተመሳሳይ የተደራጁ ደቡብ ምዕራብ ሆነ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የራሳቸውን ክልል ህገመንግስት በግልጽ በማሳተም ይህ ከማድረግ ባሻገር የርዕሳነ መስተደድር ህንፃዎችን ለመገንባት ቦታ ተረክበው፣ ጨረታ አውጥተው፣ በጀት መድበው ወደ ተግባር እንቅስቃሴ የገቡ ቢሆንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን ከንግግር ያለፈ የርዕሰ መስተደድር ህንፃ ለመገንባት ወደ ተግባር አለመግባቱ ለተለያዩ ፖለቲካዊ ትርጉሞች ተጋላጭ አድርጓል” በሚል በርካቶች ይተቻሉ።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia