1000054992

ሰበር መረጃ

ባለፉት ሰባት አመታት በሀሳብ ልዩነት ምክንያት አለመግባባት ውስጥ የነበሩ የዎላይያ ተወላጆች በህዝብ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመቆም እርቅ አወረዱ።

የዎላይታ ህዝብ የአንድነትና የእርቅ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ህዝባዊ ኮንፈራንስ በተለያዩ ጉዳዮች ምክክር አድርጓል።

በዚሁ ላለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የዎላይታ ሕዝብ የአንድነት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ኮንፈረንስ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቅቋል።

በውይይት መድረኩ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል
በሕዝቡ ዘንድ የሚነሱ ስር የሰደዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ አንጻር አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ባለሀብቶች፣ ማህበረሰብ አንቂዎች እና ሌሎችም የሚጠበቅባቸውን ባለመወጣታቸው ሕዝቡን ይቅርታ የጠየቁበት ተገልጿል።

ቀጣይ ሁሉም የዎላይታ ተወላጆች በያሉበት የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሳይሰስቱ እንደሚሰሩ የተነሳ ሲሆን በየአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመፍታት ሕብረተሰቡን በፍትሃዊነትና በታማኝነት ከማገልገል አንጻር የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለዋል ተሳታፊዎቹ በመግለጫው።

በገፊና በሳቢ ምክንያቶች የሚከሰተውን የህጻናት ፍልሰት ለመከላከል በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

በየቦታው ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ወደፍጻሜ እንዲደርሱ ልዩ ርብርብ ይደረጋል ተብሏል።

በአጠቃላይ ሕዝቡና በአመራሩ መካከል ያለው አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ተሳታፊ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ቸገልጿል።

በመጨረሻም ለዎላይታ ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የብሔሩ ተወላጆች የእውቅና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

By Journalist Natnael Gecho

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #Wolaita