1000055045

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳዊት ገበየሁ ከህገወጥ ማዕድን ጋር በአዲስአበባ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።

የቀድሞ የኮንስ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የክልሉ ረዳት መንግስት ተጠሪ የነበሩ አቶ ዳዊት ከአራት ተጠርጣሪዎች ጋር መታሰራቸውንና ፍርድቤትንም ቀርበው በደረቅ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳዊት ገበየሁ በቁጥጥር ሲውሉ በህገወጥ መንገድ የተገኘ መርኩሪ ነው የተባለውን ማዕድን ከአራት ሰዎች ጋር በመሆን በአዲስአበባ ቦሌ አካባቢ ለመሸጥ ሲደራደሩ ከአምስት ቀን በፊት እጅ ከፍንጅ መያዛቸውንም ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ግለሰቦቹ የአዲስአበባ ቦሌ ክፍለከተማ ፍርድቤት ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር የቀረበ ሲሆን በመርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርምር ጊዜ ተጠይቆ ፍርድቤቱ በመፍቀዱ በደረቅ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አረጋግጧል።

የከፍተኛ አመራሩን በወንጀል ተጠርጥረው እስር ቤት ስለመግባቱ መረጃ በተመለከተ የክልሉ መንግስት መረጃው እንደደረሳቸውና ግለሰቡ “ከኃላፊነት ተነስተው በህግ መጠየቅ አለበት” የሚል ገለልተኛና የፀና አቋም ስለመኖሩም ከደረሰን መረጃ ለማረጋገጥ ሞክረናል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia