1000055287

አማዞን ኃላፊነቱ የተወሰነ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ከሀገር ውስጥ ባለፈ በዓለምእቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ዘርፍ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገለፀ።

ማህበሩ በኅብረት ሥራ ጽንሰ ሀሳብ፣ በፋይናንስ አገልግሎትና ማርኬቲንግ እንዲሁም በሀገር አቀፍና ዓለማአቀፍ ተሞክሮዎች ላይ የጠራ አስተሳሰብ በመያዝ ለራዕዩ መሳካት በጋራ መንቀሳቀስ እንዲቻለው ከመላው ባለሙያዎቹና የስራ አመራር አባላቱ ጋር በጽንሰ ሀሳብና ተሞክሮዎች ላይ ዳሰሳና ምልከታ እያደረገ መሆኑ ተነግሯል።

ማህበሩ ከሀገር ውስጥ ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚው ዘርፍ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት ግዙፍ ራዕይ አንግቦ ዘርፉን እንደተቀላቀለ የተናገሩት የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳሰና ዋና ሰፊ ስራ ለመስራት ብቃት ያላቸው ወጣት አመራሮችና የባለሙያዎች ስብስብ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የፋይናንስ አገልግሎትን ዝቅተኛ ለሆነው የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ በወርሃ ጥር 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደረጃ የተመሰረተው አማዞን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በአነስተኛ ወለድ የመኪና፣ የቤት እና የአነስተኛ በዝነስ ስራዎች ብድርበማሰራጨት አባላቱን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለመኪና እና ቤት እስከ 2 ሚሊዮን እና ለአነስተኛ የቢዝነስ ስራዎች እስከ 500 ሺህ ብር የብድር ጣሪያ እያቀረበ ነው ያሉት ሥራ አስፈጻሚው በአጭር ጊዜ ከ90 በላይ ለሚሆኑ አባላቱ ብድር አመቻችቶ በራይድ ታክሲ ሥራና በአነስተኛ ቢዝነስ ተግባራት ውስጥ ገብተው የተሻለ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ አሰራሩን ወደኮር ባንኪንጊ ሲስተም እየቀየረ መሆኑን የጠቆሙት ሥራ አስፈጻሚው በቀጣይ ከባንኮችጋር ተመሳሳይሲስተም ለመጠቀም እና ተመሳሳይ ፕሮዳክቶች ለማቅረብ የማዘመን ስራ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አማዞን አባላትን ለማፍራት ቤት ለቤት እና በየድርጅቶች እየተንቀሳቀሰ እንደሚሰራ የጠቀሱት ሥራ አስፈጻሚው በየቀኑ ቢያንሰ 10 አባላት ማህበሩን እየተቀላቀሉ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ አማዞን በቦሌ ክፍለ ከተማ 22 ጎላጎል ጀርባ ከሚገኘው ኪያሜድ ኮለጅ ጎን ባለው ህንጻ 1ኛ ወለል ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ቅርንጫፎችን ለመክፈት እየሰራ ነው።

የዚሁ የአማዞን ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳሰና ዋና ከአንድ አመት በፊት ከህግ አግባብ ውጪ ዳሞታ የዎላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅነት አለአግባብ እንዲነሳ ተደርገው በፍርድቤትም ጭምር ቀርበው እውነት መረጋገጡን በተደጋጋሚ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መዘገቡ ይታወሳል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #Wolaita