arbmch

by Wolaita Times Media

By Journalist Natnael Gecho

የፅንፈኝነትና የጥላቻ እንቅሰቃሴዎች በግልጽ መወገዝ እንዳለበት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ።

በአከባቢው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ድንበር ተሻጋሪ ፅንፈኝነት የጋሞ ህዝብ ለዘመናት የሚታወቅበትን የሰላም ተምሳሌትነት ላይ ጥላሸት የሚቀባ በመሆኑ በጊዜው ሀይ ሊባል እንደሚገባም የዩንቨርስቲው ተማሪዎችና ነዋሪዎች አክለው ጠቁመዋል።

የመረጃ ምንጮቹ ይሄን ሀሳብ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የገለፁት በትናንትናው ዕለት አንድ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረው መገደሉን ተከትለው ነው።

አስተያየት ሰጭዎቹ በተፈጠረው ነገር ሀዘናቸውን በመግለፅ የሚመለከታቸው አካላት መሠል ዘግናኝና አስነዋሪ ድርጊት በአከባቢው እንዳይከሰት ፅንፈኛውን በህግ ተገቢ ፍርድ እንዲሰጥ በማድረግ ማረጋገጥ እንዳለበት ጠይቀዋል።

አንድ የሟች ጉዋደኛው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንዳስረዳው “የሥነ- ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የ2ኛ አመት ተማሪ የሆነው ናትናኤል ፀጉ አሰፋን የወጣበት ማህበረሰብ መነሻ ተደርጎ ሳይዘጋጅ በጥላቻ “በትግራይ ጦርነት ወቅት ወታደር ነበርክ፣ ጁንታ ነበርክ” እያለ ሌላኛው ተማሪ ከኃላ በመምጣት መጥቶ ህይወት እንዲያልፍ አድርጓል” ብሏል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የ2ኛ አመት ተማሪ የነበረው ናትናኤል ፀጉ

አስተያየት ሰጪው ተማሪ ከሟች ሆነ ከገዳይ ተማሪ ብሄር እንዳልሆነ በመግለፅ ዩንቨርስቲ የትምህርት ቦታ እንጂ “የጃውሳ ፋኖ ሆነ ጁንታ ነበርክ” እየተባባሉ በጥላቻ፣ በበቀልና በፅንፈኝነት የቡድን አላማ ማሳኪያ በፍፁም መሆን እንደሌለበት በማስጠንቀቅ ተመሳሳይ ጥቃት በሌሎች ላይ እንዳይከሰት አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አስረድቷል።

መሠል በፅንፈኞች የሚቀነባበር ብሄር ተኮር ጥቃቶች በአከባቢው ያለ እንደሆነ ለረጅም ጊዜ ከሌላ አከባቢ በመምጣት አርባምንጭ የሚኖር ግለሰብ ለጠየቅነው ሲመልሱ “አንዳንድ ድንበር ተሻጋሪ ፅንፈኞች በሰላምና በፍቅር የሚታወቅ ጋሞ አባቶች ስም የሚያጠላሽ ተግባር፣ በማንነታቸው ምክንያት እንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ማስተጓጎል እንዲሁም በብሄር መፈረጅ አልፎ አልፎ ይስተዋላልና በአስቸኳይ መታረም አለበት” ብለል።

ጋሞ ዞን ሆነ ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ የብዝሀ ብሄሮች ሰላማዊ ምቹ መኖሪያ መሆኑን በመጥቀስ በአርባምንጭ ዩንቨርስቲ የተከሰተውን ጥቃት አውግዘው በትግራይ ጦርነት ወቅት በምዕራብ አባያ አከባቢ “በፅንፈኞች አቀናባሪነት ተፈጥሮ የነበረው ዘግናኝ የብሄር ጥቃት ዳግም የሚያስታውስ አይነት” በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት መፈተሽ እንዳለባቸውም ተማፅነዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የ2ኛ አመት ተማሪ የሆነው ናትናኤል ፀጉ ጉዳይ በተመለከተ ዩንቨርስቲው በፌስቡክ ገፁ “ተማሪው ከጉዋደኛው በነበረው በግል ፀብ ህይወት አልፏል” ብሎ ዘግቦ ስለነበር ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ የዩኒቨርስቲውን የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ለማገኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌

👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏

👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲

 🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #አርባምንጭ #ዩንቨርስቲ #ጋሞ