ከአርባምንጭ ወደ ዎላይታ ሶዶ ሲገዝ የነበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአንድ ቢሮ መኪና ተገልብጦ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

በዛሬው ዕለት ወደ አራት ሰዓት ገደማ 8 ሰዎች ይዘው መነሻውን አርባምንጭ በማድረግ ወደ ዎላይታ ሶዶ ስጓዝ በምዕራብ አባያ ወረዳ መግቢያ አከባቢ አደጋው መከሰቱን ለWT ሚዲያ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ከምዕራብ አባያ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት በተጨማሪነት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በአደጋው ሞት ያልተመዘገበ ቢሆንም ሾፌሩን ጨምሮ ከባድ እና ቀላል ጉዳት በመድረሱ ተጎጂዎቹ ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል መጓዛቸውን ያመለክታል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን አደጋው የደረሰበት መኪና ባለቤት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ እንደሆነም WT ሚዲያ ከመረጃው ለማጣራት ችሏል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WT ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia