በዎላይታ ሶዶ ከተማ ለተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ ምክንያት እየሆኑ ያሉና በስፋት የሚታዩ የመንገድና ትራፊክ ዘርፍ ችግሮች ምንድናቸዉ ? (የተለያዩ የዘርፉን ባለሙያዎች በመጠየቅ የተዘጋጀ)

1. የመንገድ ጥበት
በከተማዋ ከፌደራል መንገዶች ጀምሮ፣ የዉስጥ ለዉስጥ አስፋልት መንገዶችም የእግረኛ መንገዶችም ጭምር ጠባብ ናቸው። ሐገር አቋዋራጭ የፌደራል መንገዶች በተለይ ከተማዋን ሲያቋዋርጡ በትንሹ በ አንድ በኩል ብቻ 3 lane በማድረግ ሶስት መኪና በአንድ ጊዜ ሳይጨናነቅ እንዲሄድባቸዉ መደረግ ሲገባዉ ያ በዲዛይን አለመደረጉ ትልቅ ስህተት ነው ከከተማዋ ትልቅነት አንጻር።
ሌላው የዉስጥ ለዉስጥ አስፋልት መንገዶቹ በአብዛኛው ፣የተገነቡት በሕዝቡ መዋጮ መሆኑ የሚበረታታ ቢሆንም፤ ረዥም የአስፋልት መንገድ ለመሥራት በሚል፣ አስፋልቶቹ እንዲጠቡ መደረጉ ትልቅ ስህተት ነው። አሁን ላይ የመንገዶቹ ጥበት ካለዉ የትራፊክ መጨናነቅ ጋር ተደምሮ አደጋን ቅርብ አድርጎታል። ወደፊት መንገዶችን አሰፍቶ መሥራት ያስፈልጋል።
2. የከተማዋ የሕዝብ ብዛትና የመሰረተ ልማቶቿ አለመጣጣም
በቅርቡእንኳን ለኮሪደር ልማት የሁለተኛ ደረጃ ከተሞች ተብሎ ገንዘብ ለተለያዩ ከተሞች ሲመደብ ዎላይታ ሶዶ የደቡብ ኢትዮጵያ ትልቋ የመጀመሪያዋ ማዕከልና በሕዝብ ብዛት፣ በታሪካዊነት እና በእድሜ ቀዳሚ ብትሆንም፣ የሚገባትን በብሄር ጭቆና ምክንያት መከልከሏ ይታወሳል። መሰል አሰራሮች ከተማዋ የሚገባትን መሠረተ ልማት እንዳታገኝ ማነቆ ሆነዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የከተማዋ ሕዝብ ቁጥር እጅግ በጣም ጨምሯል ለዚህም፣ በዎላይታ ሕዝብ ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የደረሰዉ ብሔር ተኮር ጥቃትና ማፈናቀል፣ የአዲሱ ክልል ማዕከልነት ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም በቅርብ ዓመታት በትግራይ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተከሰቱት የሰላም መደፍረሶች ምክንያት ብዙዎች ሰላማዊቷንና ሰዎች በብሄራቸዉ ምክንያት ምንም የተለዬ ጫና ስለማይደርስባቸዉ ለንግድ ለሥራና ለኑሮ ተመራጭ አድርጓታል።
በነዚህና በመሳሰሉት ምክንያቶች የከተማዋ ሕዝብ ቁጥር እጅግ በጣም ጨምሯል። ስለዚህ መንግስት እነዚህ ነገሮችን ከግምት በማስገባት መሠረተ ልማቶችን ለከተማዋ በልኳ ሊያሟላላት ይገባል።
3. የመንገዶች ጠመዝማዛነት
በተለይ የፌደራል ሐገር አቋዋራጭ መንገዶች ከልክ በላይ በከተማዋ ሲያቋርጡ ጠመዝማዛነት ይስተዋልባቸዋል፣ ይሄም በዲዛይን መስተካከል የነበረበት ነው፣ መነሳት ያለባቸዉ ነገሮች መነሳት አለባቸዉ ካሳ ክፍያን መሸሽ ተገቢ አይደለም። ጋራዎችን መሸሽ ሳይሆን መናድና መደርመስ ተገቢ ነው ለከተማ አስፋልት። ለአብነት ማረሚያ አካባቢ ና ከኦቶና በመናፈሻ አልፎ ወደቀይመስቀል የሚደርሰዉን መንገድ መጥቀስ ይቻላል። አንዳንድ ዉስጥ ለዉስጥ መንገዶችም መሰል ችግሮች ይታይባቿል።
4. የትራፊክ ምልክቶች ጉድለት
ለምሳሌ ከአብርሃም ሆቴል እስከ ዋዱ ያለዉ መንገድ በግምባታ ምክንያት በመዘጋቱ ፣እንደአማራጭ እያገለገሉ ያሉት በአይከን አካዳሚ ና በዉሃና ፍሳሽ በኩል የሚወስዱ ሁለቱ የአስፋልት መንገዶች ምንም አይነት የትራፊክ ምልክት ስለሌላቸዉ ለአደጋ ተጋላጭ ናቸዉ።
5. የመኪና ማቆሚያ ቦታ ችግር
ከመንገዶች ጥበት ጋር ተደምሮ መኪኖች ሲቆሙበት መንገዶች የበለጠ ይዘጋጋሉ ።ለዚህ መፍትሔዉ ከእንግዲ በዋና ዋና መንገዶች የሚገነቡ ሕንጻዎች የመኪና ማቆሚያ እንዲኖራቸዉ ማስገደድ በሕግ ደረጃ ያስፈልጋል፣ ቦታ ካላቸዉ ከሕንጻዎች ዉጪ በግቢያቸዉ መኪና ማቆሚያ ማድረግ ይገባል።
6. የታክሲ መጫኛና ማዉረጃ ቦታዎች ችግር
ተሳፋሪን በየቦታዉ ማዉረድና መጫን ክልከላ ከተደረገባቸዉ ቦታዎች ዉጪ የተለመደ ቢሆንም በተለይም ብዙ ታክሲና ተሳፋሪ ያለባቸዉ መነሻ ቦታዎች ከመንገድ ወጣ ያሉ ቦታዎች ቢዘጋጅላቸዉ ጥሩ ነው።
7. የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ብዛትና ችግር ፈቺ ሕግ አለመነደፍ
እነዚህን ተሽከርካሪዎች ከዋና ዋና መንገዶች ማዉጣቱ ተገቢ ነው። በተጨማሪም ለነሱም እንደታክሲዎቹ ሁሉ ከመንገድ ወጣ ያሉ መነሻ ቦታዎች ማዘጋጀት ይገባል (የተወሰኑ የተዘጋጁ ቦታዎች አሉ እነዛ አበረታች ናቸዉ)።
8. ከሞተር ሳይክል ጋር የሚያያዙ ችግሮች
ሞተር ሳይክሎች ሰዉ ለመጫን ባልተፈቀዱ ቦታዎች ላይ መቆማቸዉና የትራፊክ ፖሊሶች ሲመጡ አንዳንዴም፣ ተሳፋሪ ለመሻማት የሚያደርጉት ሩጫ ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ መፍትሔ ይፈልጋል።
9. ድንኳኖች
አንዳንዴ ለሰርግ ብዙ ግዜ ደግሞ ለለቅሶ እየተባለ በአስፋልት መንገዶች ላይ የሚጣለዉ ድንኳን ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነው። በተለይ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ባለባቸዉ ቦታዎች ላይ አስገዳጅ ክልከላ መደረግ አለበት። ለሕብረተሰቡም አማራጭ መፍጠር ያስፈልጋል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ለንግድ ትርኢትና ባዛርም የተጣሉ ድንኳኖች አሉ። ለመሰል ዝግጅት የሚሆን የኤግዚቢሽን ማዕከል ዎላይታ ሶዶ ያስፈልጋል።
10. የተቦረቦሩ አስፋልቶችን ቶሎ አለመጠገን
አስፋልት ገና መቦር ሲጀምር ቶሎ ካልተጠገነ ወደ ከባድ ብልሽትነት ስለሚያድግ፣ ቶሎ መጠን ያስፈልጋል።
11. ግምባታ ላይ ያሉ የአስፋልት መንገዶች መጓተት
መንገዶቹ ካላቸዉ አስፈላጊነት አንጻር ቀንና ማታ ተሰርተዉ ቶሎ የሚጠናቁበት ሁኔታ መፈጠር አለበት። በተለይ ከታቀደላቸዉ ጊዜ በላይ በምንም ተአምር ሳይጠናቀቁ መቆዬት የለባቸዉም።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WT ሚዲያ👏
#Ethiopia