1000057071

By Journalist Natnael Gecho

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ተመስገን አለማየሁ በእስር ቆይተው ከአንድ ወር በፊት 6 ዓመት ከ 5 ወር እስር እንዲሁም የ75 ሺህ ብር ቅጣት እንደተፈረደበት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰውን መረጃ መነሻ አድረገን መዘገባችን ይታወሳል።

ለበርካታ ወራት ከዎላይታ ሶዶ ማረሚያ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የቀድሞ ከንቲባ አቶ ተመስገን በቀረበባቸው 7 የተለያዩ የሙስና፣ ስልጣን አለአግባብ በመጠቀም እንዲሁም ተያያዥ ክሶች ቀርበውበት በዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤቱፈት ውሳኔ ማግኘቱን ምንጮቻችን አስረድተው ነበር።

አሁን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ተመስገን በፍርድቤት ይግባኝ መጠየቁን ተከትሎ በነፃ ማሰናበቱን ያመለክታል።

እኚሁ የቀድሞ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ ስታሰሩ የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ የነበሩ ሲሆን ከዚያ በፊት የዎላይታ ዞን ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ኃላፊ፣ የወረዳ አስተዳዳሪ እንዲሁም ሌሎች ኃላፊነት ላይ ስለመስራታቸው ከግል ማህደራቸው የWT ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የእሳቸው ከእስር መለቀቅ በአከባቢው በቅርቡ የተፈጠረ የአንድነትና የእርቅ ውጤት ሳይሆን እንዳልቀረም ምንጮች አስረድቷል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia  #Wolaita