
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ሀብቴ ከትናንት በስቲያ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በጂንካ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸው ተገለጸ።
እሳቸው የታሰሩበት ምክንያት ከመስኖ ስራ ጋር በተያያዘ ሙስና ፈጽመዋል በሚል እንደሆነ ለWT ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የክልሉ ኦዲት ቢሮ ባካሄደው ምርመራ ተጨባጭ ግኝት አግኝቶ በጥቅም ትስስር ተጠያቂነት ባያረጋግጥም፣ የፌደራል ኦዲተሮች ባደረጉት ተጨማሪ ኦዲት ግኝቶች ተከትሎ መታሰራቸው ታውቋል።
በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የቢሮው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ የተባሉ ግለሰብ በፖሊስ እየተፈለጉ ቢሆንም፣ ስልካቸውን አጥፍተው ከአካባቢው መሰወራቸው ተነግሯል።
በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።