የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አዲስ ኃላፊ አገኘ፤ የቀድሞው ኃላፊ በሙስና ክስ ሊቀርብባቸው ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ዶክተር ጌትነት በጋሻውን አዲስ ኃላፊ አድርጎ መሾሙን WT ሚዲያ አረጋግጧል።
ይህ ሹመት ከኃላፊነታቸው የታገዱትን አቶ አክሊሉ አዳኝን የሚተካ ሲሆን፣ አቶ አክሊሉ በሰራቸው ሙስና እና ብልሹ አሰራሮች በህግ እንዲጠየቁ አቅጣጫ መቀመጡ ታውቋል።
ከሁለት ቀናት በፊት WT ሚዲያ እንደዘገበው፣ የቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አክሊሉ አዳኝ ከሥልጣናቸው እንዲታገዱ በፌዴራል ሥራ አስፈፃሚዎች ውሳኔ ተላልፎ ነበር።
ይህ ውሳኔ ከስድስት ወራት በፊት የተላለፈ ቢሆንም፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ መረጃውን ለሌሎች የክልሉ ካቢኔዎች ባለማስታወቃቸው ምክንያት አቶ አክሊሉ በኃላፊነታቸው ላይ ቆይተው ነበር።
የፌዴራል ሥራ አስፈፃሚዎች ይህንን ሲያውቁ፣ አቶ አክሊሉ ወዲያውኑ ከሥልጣናቸው እንዲታገዱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ከኃላፊነት መታገድ በተጨማሪ፣ አቶ አክሊሉ አዳኝ ለሰራቸው ሙስና እና ብልሹ አሰራሮች በህግ እንዲጠየቁ አቅጣጫ እንደተቀመጠላቸው ተገልጿል።
WT ሚዲያ በዘገባዎቹ አቶ አክሊሉ አዳኝን በተመለከተ የሙስና ቅሌት መረጃዎችን በተደጋጋሚ ሲያወጣ እንደነበር ይታወሳል።
የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እንዳመለከቱት፣ የፌዴራል ምርመራ ቡድን በግለሰቡ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ላይ ህጋዊ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ መረጃዎችን እያደራጀ ነው።
አቶ አክሊሉ ከኃላፊነታቸው መነሰታቸው እስኪነሱ ትናንት ማምሻው ድረስ የእግድ ደብዳቤ እንዳልተሰጣቸው እና የፌዴራል አመራሮችን ውሳኔ እንዲቀይሩ ለማግባባት ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካ ምንጮች ገልጸዋል።
አሁን በይፋ የቢሮው ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ዶክተር ጌትነት በጋሻው፣ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮውን በአዲስ መልክ ለማዋቀር እና የሙስና ስጋቶችን ለመቅረፍ ተግዳሮት እንደሚገጥማቸው ይጠበቃል። ይህ ሹመት በክልሉ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ ላይ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ያመጣል ተብሎ ይታሰባል።
በዚህ ለውጥ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።