በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በመመሳጠር ሁለት ትልቅ ከተሞችን የበላውን ባለሀብቱ አመራርን በመረጃና ማስረጃ ስንፈትሸው 👇
አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣ በአሁኑ ወቅት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ-ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ በብሔር ጥላቻ፣ በጎጠኝነት እና በሙስና ተግባራት በተደጋጋሚ እንደሚወነጀሉ ከቅርብ ምንጮች የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለይ ደግሞ በዎላይታ ህዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻ እና በሙስና የተጨማለቁ ድርጊቶች ተዘርዝረዋል።

አቶ ብርሃኑ ቀደም ሲል የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት ከወላይታ ጋር ለመደራጀት “በስነልቦና አንገኛኝም” የሚል አቋም ሲያራምዱና ወላይታን ሲያንቋሽሹ እንደነበር ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የከተማና መሠረተ-ልማት ቢሮ ኃላፊነት ከተሰጣቸው በኋላም ቢሆን፣ በወላይታ ህዝብ ላይ የጀመሩትን ጥላቻና እኩይ ተግባር በብዙ መልኩ እንዳጠናከሩት ተመልክቷል።
ከሥራ ማባረር እና ፍርድ ቤት ውሳኔ
ከወሰዷቸው “እኩይ ተግባራት” አንዱ የአለም ባንክ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ-ልማት ፕሮግራም/UIIDP/ ተጠቃሚ የሆኑትን የዎላይታ ዞን ከተሞች (አረካ እና ቦዲት) ከፕሮግራሙ ተጠቃሚነት ማስወጣት ነበር።
በተጨማሪም ከ12 ዓመታት በፊት በድሮ ደቡብ ክልል ሥር በአለም ባንክ ፕሮግራም ላይ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ የዎላይታ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ከፍተኛ ባለሙያዎችንና የፕሮግራሙን አስተባባሪ ጨምሮ በድምሩ ሰባት (7) ሰዎችን፣ የዎላይታ ብሔር በመሆናቸው ብቻ ከሥራ እንዳባረሩ ተገልጿል።
በምትካቸውም የራሳቸው ወገን የሆኑትን ሰዎች ያለ ውድድር ቀጥረው በማሰራት የጎጠኝነታቸውን ባህሪ አንፀባርቀዋል ተብሏል።
ይህን ሕገ-ወጥና አድሎአዊ አሠራር በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት የዎላይታ ተወላጅ ባለሙያዎች፣ በመጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በበታች ፍርድ ቤት አሸናፊ ሆነዋል።
ፍርድ ቤቱ ሰራተኞችን ወደ ሥራ እንዲመለሱ አልያም አሠሪና ሰራተኛ ሕጉን ተከትሎ ተገቢው የስንብትና ካሳ ክፍያ ተፈጽሞላቸው በክብር እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል።
ይሁንና አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በጎጠኛ አመለካከት ተጠናውቷቸውና እራሳቸውን ከሕግ በላይ አድርገው በማየት የፍርድ ሂደቱን ለማዛባት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የበታች ፍርድ ቤት ውሳኔን አፅንቶ ይግባኙን ውድቅ አድርጓል።
የሙስና ወንጀሎች
በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በህግ የበላይነት የማያምኑ፣ ቅንነትና ፍትሃዊነት የጎደላቸው፣ በሙስና የተጨማለቁ ግለሰብ እንደሆኑ ተጠቁሟል።
ከፈጸሟቸው የሙስናና ብልሹ አሠራሮች መካከል ቅጥርና ዝውውር ተከልክሎ እያለ ከ38 በላይ የጋሞ ተወላጆችን ያለ ውድድር በቢሮ መቅጠር፣ ያለ ፈቃድና ጨረታ የቢሮ ሕንፃ የውስጥ ክፍሎችን ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ማሠራት፣ እና ለመኪና እድሳት ያለ ጨረታ ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣት ይገኙበታል።
የክልሉ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ በመሆናቸውም አብዛኛው የግንባታ ፕሮጀክቶች ያለ ጨረታ ለዘመዶቻቸው በማደል የህዝብ ሀብት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲመዘበር እያደረጉ ነው ተብሏል።
ለቢሮ የተከራዩት ሕንጻም ላይ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ሲሆን፣ በሮማን ፀጋዬ ስም የሚታወቀውና በአሁኑ ጊዜ የክልሉ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን መስሪያ ቤት የተከራየው ሕንፃም የእሳቸው እንደሆነ በሰፊው ይወራል።
የመረጃ ምንጩ እንደገለጸው፣ ይህ ሁሉ ተግባር በሰነድና በማስረጃ የተረጋገጠ ነው፣ የዎላይታ ህዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻም “ልክ የለውም”፣ እውነትና ፍትህ እስከሚረጋገጥ ድረስ ትግሉ እንደሚቀጥል እና ከአለም ባንክ ፕሮግራም የወጡት አረካና ቦዲት ከተሞች ተመልሰው የፕሮግራሙ ተጠቃሚ እስከሚሆኑ ድረስ ትግሉ በተባበረ መንገድ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ተሰጥቷል።