1000061275

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራር የፓለቲካ ስክነትና አንድነትን አሳስበዋል።

አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ፣ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የንቅናቄ የሚመሩ የፓርቲና የመንግስት ተግባራት የ90 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ ዘጠና ቀናት ዕቅድ ውይይት መድረክ ላይ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

አቶ ገብረመስቀል ባደረጉት ንግግር፣ “አዳራሽና ቢሮ ውስጥ ሲሆን ስለ አንድነት የሚያወራ ውጪ ሲሆን የሚያሴር፣ ተግባሩ ሌላ የሆነ ሁለት ጭንቅላትና ሁለት ምላስ ያለው፤ የተለየ ሀሳብ የሚያነሳና ትግል የሚያደርግ አመራርን በተደራጀ መንገድ ለማጥቃት ዘመቻ የሚያደርግ ሴረኛ፣ አፉና ልቡ ሌላ የሆነ ወላዋይ አመራር ፈፅሞ ሊኖር አይገባም።” ሲሉ የፓለቲካ ስክነትን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአመራሩ ሃሳብና የተግባር አንድነት ላይ ትኩረት ያደረጉት አቶ ገብረመስቀል፣ አመራሩ “በእውነትና በመርህ ላይ ተመስርቶ የህዝብን ጥቅም ማዕከል አድርጎ መምራትና በጊዜ የለኝም መንፈስ በትጋት መስራት ይኖርበታል።” ብለዋል።

ይህ ንግግር በክልሉ ውስጥ ያለውን የአመራር ብቃትና አንድነት የማጠናከር ፍላጎት ባሻገር በክልሉ ከፍተኛ አዳራሽና ቢሮ ውስጥ ሲሆን ስለ አንድነት የሚያወራ ውጪ ሲሆን የሚያሴር፣ ተግባሩ ሌላ የሆነ ሁለት ጭንቅላትና ሁለት ምላስ ያለው፤ የተለየ ሀሳብ የሚያነሳና ትግል የሚያደርግ አመራርን በተደራጀ መንገድ ለማጥቃት ዘመቻ የሚያደርግ ሴረኛ ስለመኖሩ የሚያንፀባርቅ እንደሆነ ተገልጿል።