1000061537

አቶ ሞቶሎሚ ጢሞቴዎስ ሳላ የዎላይታ ቴሌቪዥን እና ዎጌታ ሬዲዮ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ

ይህ ሹመት የቀድሞው የዎላይታ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሴባ ናና ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

WT ሚዲያ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የዎላይታ ቴሌቪዥን እና ዎጌታ ማህበረሰብ ሬዲዮ በአንድ መዋቅር ስር እንዲሆኑ አዲስ የአደረጃጀት ለውጥ ተደርጓል።

በዚህ አዲስ አደረጃጀት ሁለቱ ተቋማት በየራሳቸው ዘርፍ ኃላፊዎች እየተመሩ በአንድነት የሚሰሩ ይሆናል።

ከዚህ ቀደም እነዚህ ሁለት ተቋማት ራሳቸውን ችለው በየመዋቅራቸው ሲንቀሳቀሱ ነበር።

አቶ ሞቶሎሚ ጢሞቴዎስ ሳላ ከዚህ ቀደም በዎጌታ ሬዲዮ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ በመሆን እንዲሁም የዎጌታ ሬዲዮ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በዚህ ወቅትም ጠንካራና ውጤታማ አመራር ማሳየታቸው ተገልጿል።

ይህ አዲስ ውህደትና ሹመት፣ እነዚህ ሁለቱ የዎላይታ ማህበረሰብ ተቋማት ከመንግሥት ልሳን ከመሆን ባለፈ የህዝብን ድምፅ በማስተናገድ ለውጥ ያመጣሉ ወይ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል።