1000061642

ከኢትዮጵያ ቱርካና ሐይቅ ከፍተኛ የዓሣ ምርት በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያና ሌሎች ሀገራት እየተዘረፈ መሆኑ በአከባቢው ስጋት ፈጠረ።

በኬንያ የሚኖሩ ሶማሌያውያን ግለሰቦች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዘልቀው በመግባት ከቱርካና ሐይቅ ከፍተኛ መጠን ያለውን የዓሣ ምርት በሕገወጥ መንገድ እያወጡ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ዳሰነች ወረዳ ኦሞራቴ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ቱርካና ሐይቅ ያለውን ከፍተኛ የዓሣ ሀብት በእጅጉ እየጎዳው ነው።

ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ቶን ዓሣ ምርት በሕገወጥ መንገድ እየተጫነ ወደ ተለያዩ አገራት እየተወሰደ ስለመሆኑ WT ሚዲያ በአከባቢው ባደረገው ምርመራ አረጋግጧል።

ይህ ሕገወጥ ዝውውር የሀገርን ጥቅም የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ በኢትዮጵያ በኩል በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱት እንዳይሰሩ ከክልል ጀምሮ ያሉ የአካባቢው አመራሮች ከሕገወጥ ግለሰቦች ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል በተግባሩ ውስጥ እጃቸው እንዳለበት WT ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ባካሄድነው ምርመራ ዘገባ ዙሪያ ምላሹን ከኢትዮጵያ እና ከኬንያ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን በዝርዝር መረጃ እንመለስበታለን።