አንድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ ኃላፊ በ23 ሚሊዮን ብር የቤት እቃዎች ግዥ መፈፀሟ ውዝግብ አስነሳ።
በተጨማሪም እኚሁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሶ፣ መኖሪያቸው አዲስ አበባ ሆኖ በየጊዜው ከጅንካ ከተማ በአውሮፕላን እየተጓዙ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

ከዚህም ባሻገር፣ ከታማኝ ምንጮች እንደተገኘው መረጃ፣ በቅርቡ በአዲስ አበባ ለሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከዱባይ በ23 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቤት እቃዎች ማስመጣታቸውን ለWT ሚዲያ ከደረሰው ተጨባጭ መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።
WT ሚዲያ ባደረገው ዳሰሳ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስድስት መዋቅሮች ከተከፋፈለ በኋላ የተደራጀ ዝርፊያ እየተካሄደ መሆኑን አመልክቷል።
ምሁራን በክልሉ ውስጥ የፖለቲካ እና የሀብት ክፍፍል ኢ-ፍትሃዊነት እንደታየበት ጠቁመዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች መካከል በሙስና፣ ስልጣንን አላግባብ መጠቀም እና በግል ጥቅማጥቅም የተሳሰሩ ግንኙነቶች እየጨመሩ መምጣታቸውም የበርካቶችን ትኩረት ስቧል።
ልማት በአንድ አካባቢ ማተኮሩ ቅሬታ ፈጥሯል
ክልሉ 32 ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፈ ቢሆንም፣ የልማት ትኩረቱ በአንድ አካባቢ ላይ ማተኮሩ በሌሎች የክልሉ ከተሞች እና ብሔረሰቦች ዘንድ የመገለል ስሜት እየፈጠረ ነው።
ይህ ኢ-ፍትሃዊነት እና አድሏዊ አሰራር በጊዜ ካልተስተካከለ ሌሎች መዘዞችን ሊያስከትል እንደሚችል በርካቶች እየጠቆሙ ነው። የሚመለከተው አካል ጉዳዩን ፈትሾ መፍትሄ እንዲሰጥም ጥሪ ቀርቧል።