1000062053

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች ከፍተኛ ዝሪፋያ ውስጥ የተሳተፉትና የመንግስት ትዕግሥት ከፍተኛ ቁጣ በህዝቡ ዘንድ ሊቀሰቅስ እንደሚችል ተመላከተ

የክልሉን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉና በዲላ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አንድ ምሁር ስለጉዳዩ ለWT ሚዲያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጉዳዩን ከመንግስት ባለስልጣናትና በክልሉ ካሉ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ካሉ ከዎላይታ ከጋም እና ከጌዴኦ ከጎፋ እና ከኮንሶ ምሁራኖች ጋር በቅርበት የሰሩና ሰፊ ትንታኔ መስጠት የሚችሉ ምሁር እንደሆኑ WT ሚዲያ አረጋግጧል።

ትላንት በወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ በክልሉ ት/ት ቢሮ ኃላፊ ላይ የወጣውን መረጃ እውነት እንዳልሆነ ለማስመሰል ትናንሽ ሚዲያዎች የገፅታ ግንባታ ስራ ለመስራት መሞከራቸውን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ በነበሩ ወቅት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ 12ት ዞኖችና ከክልሉ ማዕከላት እንዲሁም ከተለያዩ ባለሀብቶች ከፍተኛ የሆነ ሚሊየን ብሮች ተሰብስቧል ይለናል ምሁሩ።

አላማው ደግሞ በክልሉ አስተናጋጅነት የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ምክኒያት በማድረግ በደማቅ ስነስርአት በዓሉን ለማክበር በሚል ቀጥታ በክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ ትዕዛዝ ሰጪነት የተሰበሰበ ገንዘብ ነው።

ይህንን ገንዘብ ያለ ኦዲት እና በመንግስት ፋይናንስ ስርአት የማይመራ በመሆኑ ቀጥታ ለበዓሉ በሚል በጋሞ ተወላጆች ብቻ በተቋቋመ ኮሚቴ ውስጥ አፈጉባኤ በመሆኗ ብቻ የገንዘቡን ወጪ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ለሁለት ወጪውን እንደመሩ ከክልሉ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፍተኛ በመሆነ ጥቅም ትስስር ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ በክልሉ በተደረገ ሪፎርም ወደ ጂንካ ሲመደቡ ለወራት ቢሮ አልገባም ቦታው አይመጥነኝም ብለው ከጥላሁን ጋር ሰጣገባ ውስጥ ቢገቡም ሪፎርሙ የተሰራው በፌዴራል እንጂ በጥላሁን ከበደ እንዳልሆነ ተረድተው ወደ ጂንካ አምርተዋል።

ይህንና ሌላ መረጃ ከቢሮአቸው እየወጣ እንዳለ ሲሆን ለእስቴድየም ቅድመ ክፍያ፣ ለእንግዳ መስተንግዶ አልጋ፣ ለፕሮሞተር፣ ለአርባምንጭ ውስጥ ለውስጥ አስፖልት ስራ ለአቢይ ኮሚቴ እና ሌሎች በርካታ ወጪዎች ከፍተኛ ሚሊዮን ብሮችን ለአፈጉባኤው አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ ለሌሎች አካላት እንደተሰጠ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በክልሉ በውሃና በአድን ቢሮ ከዚህ ቀደም የተዘረፈውን ጨምሮ በመአድን ሀብት ዙሪያ ከክልሉ እስከ ፌዴራል ድረስ የተዘረጋ የሙስና ሰንሰለት እንዳለ መገንዘብ ችለናል።

በተለይ ከድንጋይ ከሰል ጋር በተገናኘ በርካታ የፌዴራልና የክልል እንዲሁም የኦሮሚያ ባለሀብቶችና ባለስልጣናት እጅ እንዳለ እኚሁ ምሁር አስረድቶናል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተንሰራፋው ሙስናና ብልሹ አሰራር ሌብነት ከፍተኛ ቁጣ ሊቀሰቅስ እንደሚችል ምልክቶች እንዳሉ የሚያሳይ ነገር እንዳለ ምሁሩ አስረድተዋል።

አሁን አሁን በክልሉ የፍትሃዊነት ችግር ጎልቶ መውጣት አንድ አከባቢ ብቻ እንዲለማ መደረጉና ይህንኑ ደግሞ በገንዘብ እንዲደግፉ አቅም የሌላቸውን አመራር አካላት በየዞኑ በመመደብ ርዕሰ መስተዳድሩ የፈለጉትን ገንዘብ እየጠየቁ ከሁሉም መዋቅር እየሰበሰቡ ለራሳቸው ትውልድ አከባቢ ልማት ማዋላቸው ህዝቡን ወደቁጣ እንደሚያስገባ ስጋታቸውንም አክለዋል።

የክልሉን ብልሽት በዎላይታ ሶዶው በ4 ቀን ግምገማ በቂ መረጃ ወስዶ የሄደው የፌዴራሉ ብልፅግና ፓርቲ እስካሁን ዝምታን መምረጡ ያጠፉ አመራሮች ይበልጥ እንዲያጠፉ በዝምታ እየታለፈ ከፍተኛ ሚሊየን ብሮች እና ሀብቶች ከክልሉ እየተዘረፉ እንደሚገኙ ነው እኚሁ ምሁር ያብራሩት።

በተለይ ክልሉ ውስጥ ብልሽት የፈፀሙ አመራሮች አጠቃላይ የሌብነት አውራቸው አቶ ጥላሁን በመሆኑ ሌብነታቸውን በገሀድ በማድረግ ከቀን ወደ ቀን በፎቶና በመድረክ ወሬ ብቻ በፎቶ ክልሉን አጅበው የልማት ቀጠና ለማስመሰል እየጣሩ ይገኛሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በ6ቱ ማዕከል የክልሉ ቢሮ ኪራይ በዲላ ክላስተር ከ4ቱ ቢሮዎች 3ቱ በመንግሥት ቤት ሲሆኑ አንዱ በኪራይ በዎላይታና በሌሎች አከባቢዎች በብዛኛውን ቢሮ በመንግስት ቤት ሲሆን በአርባምንጭ ክላስተር ሁሉም በሚባል ደረጃ በኪራይ ነው ይህም አብዛኛውን የአመራር ቤትና ለኪራይም በወር እስከ 800,000 ብር በአማካይ እየተከፈለ አብዛኛውን ወደ አመራር ኪስ ይገባል።

አሁን ላይ በማዕከላዊ ክልል የቢሮ ግንባታ የጀመረ ቢሆንም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኪራይ ስም ከፍተኛ ገንዘብ አመራሩ ሼር ስለሚያደርግ ለክልሉ ቢሮ ግንባታ ወሬም የለም ይህ ሌብነት በአቶ ጥላሁን ከበደ ዘመን እለት እለት እየጨመረ እየሄደ ሌብችም የሚሸለሙበት ክልል ሆኗል።

Ethiopia #southethiopia #Gamo