የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽኑ ውሳኔ መሠረት ዎላይታ ዲቻ የኢትዮጵያ ዋንጫ ባለቤት ሆኗል !!
ይሄንን ውሳኔ ተከትሎ ዎላይታ ዲቻ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ውድድር ላይ የሚሳተፍ ይሆናል።


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በቀን 24/10/2017 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የታገዱ ተጫዋቾችን በማሰለፍና በዳኝነት አድሎ ያሸነፈው የኢትዮጵያ ዋንጫ በፎርፌ ተሸናፊ ሆኖ ዋንጫው ለዎላይታ ድቻ ተመላሽ እንዲደረግ ወስኗል።
በዚሁም የዎላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ በአፍሪካ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የ2025/26 የውድድር ዘመን ተሳታፊ እንዲሆን ወስኗል።
የዎላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ቦርድ በዚሁ በኢትዮጵያ ዋንጫ ክለቡ ተበድሏል ዋንጫው ለዎላይታ ዲቻ ይገባል በሚል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።