1000062915

“በግፍ ከተነጠቀ በኃላ በድል የተመለሰው ዋንጫ፤ የዎላይታ ህዝብ ለእውነትና ለፍትህ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ትግል እውነተኝነትን በአደባባይ የሚያረጋግጥ ነው” ሲሉ በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ገለፁ።

በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ፣ የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር እና የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በግፍ ተነጥቆ የነበረው ዋንጫ ለዎላይታ ዲቻ መሰጠቱን ተከትሎ የተሰጠውን ውሳኔ ተከትለው ፓርቲዎቹ ለWT ሚዲያ መግለጫ ሰጥተዋል።

የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ) በሰጠው መግለጫ፣ “የዎላይታ ሕዝብ ከፍታውን የሚያረጋግጠው ለእውነትና ለፍትህ በሚያደርገው ፍትሐዊ ትግል ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የወሰነው ውሳኔ ተገቢ ነው ብለን እንወስዳለን። ነገር ግን ፌደሬሽኑ ያለአግባብ ለእንግልትና ለሞራል ጉዳት ለተዳረገው ለዎላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ፣ ለደጋፊዎቹና ለመላው ዎላይታ ሕዝብ ክብሩን የሚመጥን ካሳ ልከፍልና ልካስ ይገባል” ብሏል።

የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ዎህነን) ደግሞ፣ “የጦና ንቦች በግፍ የተወሰደብን ዋንጫ ወደ ቤቱ በሰላም በመመለሱ የተሰማንን ደስታ በዎላይታ ሕዝብ ስም ይገልፃል። እንኳን ደስ አላችሁ!!” በማለት ደስታውን ገልጿል።

የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) በበኩሉ ረዘም ያለ የደስታ መግለጫ አውጥቷል።

መግለጫው የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ የሚደግፍ ሲሆን፣ የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ አመራርና ደጋፊዎች ፍትህ እንዲረጋገጥ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

“በመጨረሻም የዎላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ተጫዋችች፣ አሰልጣን፣ የክለቡ አመራር፣ ወደር የማይገኝላቸው የዲቻ ደጋፊዎች፣ መላው የዎላይታ ህዝብ አጠቃላይ ስፖርት አፍቃሪ ኢትዮጵያዊያን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን” በማለት መግለጫውን አጠናቋል።

ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክስተት ሲሆን፣ በፍትህ እና በህግ የበላይነት ጉዳይ ላይ ትልቅ ትምህርት ሰጪ ነው ብሏል።

የፌደሬሽን ውሳኔ ተከትሎ የግብፁ ዛማሌክ አለቃ የሆነው ይሄንን ውሳኔ ተከትሎ ዎላይታ ዲቻ የዋንጫ ባለቤት ከመሆን በተጨማሪ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ውድድር ላይ በታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሳተፍ ይሆናል።

በተያያዘ ዜና የዚሁ የፌዴሬሽኑ ወሳኔ ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት በዎላይታ እና ሌሎች ቦታዎች የሚገኙ የክለቡ በርካታ ደጋፊዎች አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

Ethiopia #southethiopia #Wolaita