ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ከአዲስ መፅሐፋቸው ሺያጭ የሚገኘው ገቢ በሙሉ በጎፋ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱት ወገኖች እንዲሆን ወሰኑ።
የኢፌዴሪ የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ “ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።


መጽሐፉ የአገር በቀል ዕውቀትና ብሂል ለአገራችን ፖለቲካ መፍትሄ ጠቋሚ መንገድ ጠቋሚ ነው ተብሏል።
ዶ/ር ተስፋዬ መጽሐፋቸውን ያሳተሙበት ዋና ዓላማ ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ በሙሉ ባለፈው ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ሻቻ ጎዚዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የትምህርት ቤት ግንባታ ማስገንባት መሆኑን አስታውቀዋል።
ይህ ውሳኔ በአደጋው ምክንያት የተፈናቀሉ እና የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን፣ መጽሐፉም ለዚህ ሰብዓዊ ዓላማ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎለታል።