አትሌት ቀነንሳ በቀለ “ባዶ ወረቀት ተሰጥቶኝ ንብረቱ ለሌላ ባለሀብት ተሽጧል” በሚል ከፍተኛ ቅሬታ አቀረበ
አትሌቱ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታ እያሰማ እንደሚገኝና አመራሮቹ ጉዳዩን ለማስጨረስ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንደተቀበሉም ተነግሯል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ለአትሌት ቀነንሳ በቀለ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የእንቨስትመንት መሬት እንዲሰጥ በወቅቱ የዞኑ አስተዳደሪ አሁን ላይ ደግሞ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አባይነህ አበራ አማካይነት መሬት ሳይሰጥ ባዶ ደብዳቤ ብቻ ሰጥተው እንደነበር ለWT ሚዲያ የደረሰው የቅሬታ መረጃ ያመለክታል።
አትሌት ቀነንሳ በቀለ የእንቨስትመንት መሬት ሳይረከብ ደብዳቤ ብቻ በተቀበለበት ቦታ ላይ ግለሰቦች ሲያመርቱ የነበረው ሙዝ በዞኑ አስተባባሪነት አቶ ኢያሱ ወንድወሰን ለተባለ ተሸጥል።

በዚህ የተነሳ አትሌቱ ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታ እያሰማ እንደሚገኝና አመራሮቹ ጉዳዩን ለማስጨረስ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንደተቀበሉም ለWT ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም ጋሞ ዞን አብዛኞቹ የእንቨስትመንት ጥያቄዎች በህጉ መሠረት በክልሉ ካቢኔ ተወሰነው መተላለፍ ሲገባው በአመራሮቹ ትዕዛዝ ብቻ እየተላለፈ እንደሆነ WT ሚዲያ በተደጋጋሚ በመረጃና በሰነድ በማስደገፍ መዘገቡ ይታወሳል።
ለዝርዝር መረጃ እንመለስበታለን።