አነጋጋሪው የደቡብ ክልል ምክርቤትና የርዕሰ መስተዳድሩ ውዝግብ ምንድነው ?

አነጋጋሪው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እና የርዕሰ መስተዳድሩ ውዝግብ ምንድነው ?

ነባሩ መዋቅር ገና ተደራጅተው ሳይጠናቀቅ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣት በተዋቀረው አዲስ መስሪያቤቶች ፕረዚዳንቱ ሹመት እንዳይሰጥ የፌደራል መንግስት መከልከሉ ተነገረ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባጠናቀቀው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ፣ የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ያፀደቀው አብዛኞቹ መስሪያ ቤቶች ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተጠሪ እንዲሆኑ መደረጉ ሰፊ ውይይትና ክርክር አስነስቷል። 

በተጨማሪም፣ ርዕሰ መስተዳድሩ በምክር ቤቱ አቅርበው ለማፅደቅ የሞከሩት የሹመት ጥያቄ በፌዴራል መንግስት ትዕዛዝ ውድቅ መደረጉንና ምርመራ መጀመሩን ታማኝ ምንጮች ለWT ሚዲያ ገልጸዋል።

በሌሎች ነባር ክልሎችም ሆነ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር አብረው በተዋቀሩ ክልሎች የመዋቅር ለውጥ ሳይደረግ፣ ገና ምስረታውን ባልጨረሰ በሁለት ዓመት ክልሉ ውስጥ አዲስ ጥናት ተካሂዶ አዲስ መዋቅር መቅረቡ በርካታዎችን እያነጋገረ ይገኛል።

 ምንጮች እንደሚሉት፣ ይህ አዲስ መዋቅር በክልሉ የተፈጸሙ ከፍተኛ ሌብነቶችንና የህግ ጥሰቶችን ለመሸፈን ያለመ ስትራቴጂ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ ይላሉ።

ምክር ቤቱ በ3ኛ ቀኑ ውሎው ረቂቅ አዋጆችን ከመመርመርና ከማፅደቅ ባሻገር፣ የሚቀርቡ ሹመቶችንም መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ በክልሉ ኮሙኒኬሽን ተገልጾ ነበር። 

ነገር ግን፣ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን ከበደ ከፓርቲ ጋር ሳይመካከሩ በክልሉ ምክር ቤት ያቀረቡት ሹመት በፌዴራል መንግስት ትዕዛዝ ውድቅ መደረጉንና ምርመራ እንዲጀመር መታዘዙን WT ሚዲያ ዘግቧል። 

ይህ ድርጊት የርዕሰ መስተዳድሩ ዋነኛ ዓላማ “የግል ጥቅም ትስስርን በመጠቀም አብዛኛውን የክልሉ መስሪያ ቤቶች ተጠሪነታቸው ለእሳቸው በማድረግ የሌብነት መዋቅሩን ህግ አድርጎ ለማጽደቅ ያለመ ነው” ሲሉ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ ርዕሰ መስተዳድሩ በፌዴራል መንግስት በጀት አማካኝነት በተደራጀ ሌብነትና ዝርፊያ ከመፈጸም ባለፈ፣ በራሳቸው የትውልድ አካባቢያቸው ብቻ በርካታ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስገንባት ላይ መሆናቸው ቅሬታ አስነስቷል። 

ክልሉ 32 ብሔረሰቦችን ያቀፈ ቢሆንም፣ የልማት ትኩረቱ በአንድ አካባቢ ላይ ማተኮሩ በሌሎች የክልሉ ከተሞችና ብሔረሰቦች ዘንድ የመገለል ስሜት ፈጥሮ ተቃውሞዎችን እያስነሳ ይገኛል።

WT ሚዲያ በቅርቡ ባወጣው ዘገባ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው መደበኛ የካቢኔ ስብሰባ ላይ በርካታ አወዛጋቢ ውሳኔዎች መተላለፋቸውን አረጋግጧል። 

እነዚህ ውሳኔዎች የአንዳንድ ቢሮዎችን መበተን፣ መደባለቅና ከደረጃ ዝቅ ማድረግን ያካተቱ ሲሆን፣ ከክልሉ ምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠሩ ነው።

እነዚህ ቢሮዎች መታጠፍ ወጪን ለመቆጠብና አላስፈላጊ ብክነትን ለመቀነስ ተገቢ እርምጃ ቢሆንም፣ ከወዲሁ ከፍተኛ ቅሬታና ስጋት ከሙሁራን ዘንድ እየተሰማ መሆኑን WT ሚዲያ ዘግቧል። 

በተለይም የክልሉ የቢሮ ክፍፍልና የሹመት አመዳደብ ከፍተኛ የፍትሃዊነት ችግር እንዳለ እየታወቀ፣ አብዛኛውን ቢሮ በአርባምንጭ ክላስተር ማድረጉ ከፍተኛ የፍትሃዊነት ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል።

ከአራት ቀናት በፊት በWT ሚዲያ የወጣው ዘገባ፣ እነዚህ ውሳኔዎች ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን በትውልድ አካባቢያቸው ለማስገንባት ካላቸው ፍላጎት ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጿል።

 ምንጮች እንደሚጠቁሙት፣ ፕሬዝዳንቱ ለዚህ ዓላማ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል አሁን በቢሮ ደረጃ የሚገኙትን የንግድ ቢሮና የኢንዱስትሪ ቢሮ ወደ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በማዋቀር የአመራር ለውጥ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ውሳኔ ከአምስት ቀናት በፊት በተካሄደው የክልሉ ካቢኔ ስብሰባ ላይ ይፋ አድርገዋል።

ይህ አደረጃጀት በተለይ ዶ/ር ቦጋለ ቦሼን ጨምሮ ሌሎች ወደ ከፍተኛ ስልጣን እርከን ሊመጡ ይችላሉ ተብለው የታሰቡ የዎላይታ ተወላጆችን ለማጥቃት ያለመ ነው ሲል WT ሚዲያ መዘገቡ ይታወሳል።

 አቶ ጥላሁን ከበደ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ በማጣት እንደቆዩ በመግለፅ፣ አሁን ላይ የመጨረሻ ሙከራቸው የሆኑትን ሁለት ተቋማትን በማዋሃድ ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩትን የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቦጋለ ቦሼን ወደ ሌላ ቢሮ በመውሰድ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን በትውልድ አካባቢያቸው ለማድረግ ያለሙትን ለማሳካት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ምንጮቹ አብራርተዋል።

በሀገሪቱ ከተሞች በየጎዳናው በአባታቸው በእናታቸው አቅፍ ሆነው ማደግና መማር የሚገባቸው ህፃናት፣ ወጣቶችና ሴቶች በአካባቢው ምንም የስራ እድል ባለመፈጠሩ በስደት እንዲሁም በተስፋ መቁረጥ ላይ እንደሆኑ አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ።

 ከ200 ሺህ በላይ የተማሩ ስራ አጥ ወጣቶች መኖራቸው፣ ርዕሰ መስተዳድሩ “ለእኔ ብቻ” የሚል አስተሳሰብ እንዳላቸው ያሳያል ተብሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ መንግስት እስካሁን ለህዝብ በይፋ ባልተሰራጨበት ሁኔታ የተለያዩ አዋጆችንና ደንቦችን ማፅደቅ ከህግ አንፃር ይቻላል ወይ በሚል ድርጊቱን ግልፀኝነት የጎደለው እያሉ በርካቶች እየተቹ ይገኛሉ።

 የመንግስት አመራሮች መረጃ ለወራት በመደበቅ ይፋ አለማድረጋቸው ለሚመሩት ህዝብ ካለመታመን ባሻገር መሰል በርካታ ጉዳዮች በድብቅ እየተሰሩ መሆናቸውን ግልጽ ማሳያ እንደሆነ ብዙዎች ይገልጻሉ።

ከዚህ በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሶስት ወራት በላይ ተሰርቆ ተደብቆ የነበረው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፍ ደብዳቤ ከድብቅበት መውጣቱ ይታወሳል።

 ይህ አዲስ የቢሮ አደረጃጀትና አመዳደብ የክልሉን ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና የአመራር ምደባ ጉዳይ ይበልጥ የሚያወሳስበው መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ። #Ethiopia #southethiopia