አቶ ደሳለኝ ከበደ በአቶ ጥላሁን ከበደ ላይ ያነሷቸው አስር ቁልፍ ነጥቦች ምንድናቸው ?
ትናንት WT ሚዲያ የዘገበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የጋሞ ልማት ማህበር ቦርድ አባል የሆኑት አቶ ደሳለኝ ከበደ ካዛ ከቦርድ አባልነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ የገለጿቸውን 10 ዋና ዋና ምክንያቶችን አሳጥረን ለአንባቢያንና ተመልካቾች እንደሚከተለው እናቀርባለን።
እነዚህ ከታች የተዘረዘሩ ነጥቦች በተለይም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት በሆኑት አቶ ጥላሁን ከበደ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሲሆን፣ አቶ ደሳለኝ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ዝርዝር ውስጥ ጎልተው የወጡ ናቸው።
ለመሆኑ በአቶ ጥላሁን ከበደ ዙሪያ የቀረቡት አስር ቁልፍ ክሶች ምንድናቸው ?
1. የአርባምንጭ እርሻ ልማት መሬት ቅርምት እና ጥላሁን ከበደ አጥፊ አካሄድ:
አቶ ደሳለኝ እንደገለጹት፣ ከ200 ሄክታር በላይ የአርባምንጭ እርሻ ልማት ድርጅት መሬት በአቶ ጥላሁን ከበደ ቀጥተኛ ትእዛዝ፣ አንባገነናዊና ስግብግብ ውሳኔ እንዲሁም የሙስና ተግባር ለልዩነህ ዱባሌ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ እና ለጥቂት ግለሰቦች በብዙ ቢሊዮን ብሮች ተላልፏል። ይህንን የተቃወሙ ሰዎች ላይም የማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ነው ብለዋል።
2. የልማት ማህበሩ የሰው ሀብት አስተዳደር መመሪያ መጣስ:
ቦርዱ የሰው ሀብት አስተዳደር መመሪያ ቢያፀድቅም፣ በአቶ ጥላሁን ከበደ ቀጥተኛ ትእዛዝ የወንጀል ሪከርድ ያለባቸው፣ ጡረታ የወጡ እና ከመንግስት ተቋማት ከኃላፊነት የተነሱ ግለሰቦች ተቀጥረው ከፍተኛ ብልሹ አሰራርና ሙስና እየፈጸሙ መሆኑን አቶ ደሳለኝ በክስ መልክ አቅርበዋል።
3. ከህግ ከተፈቀደው ጊዜ በላይ በቦርድ አባልነት ለመቀጠል ያሉ ስግብግብ ፍላጎቶች እና አቶ ጥላሁን ከበደ:
አቶ ደሳለኝ አቶ ጥላሁን እና አቶ አዋሽ ከ15 ዓመት በላይ በቦርድ አባልነት መቆየታቸው ህገወጥ መሆኑን ጠቁመዋል። የቦርድ አባልነት ከሁለት የስልጣን ዘመን በላይ መሆን ባይገባውም፣ ራሱ አቶ ጥላሁንን ጨምሮ ከ25 ዓመት በላይ የግል ቤት ያደረገ ግለሰብ መኖሩ ከፍተኛ የጥቅም ትስስር፣ የጥቅም ግጭት እና ስር የሰደደ ብልሹ አሰራር እንዲንሰራፋ አድርጓል ብለዋል።
4. አንድ የቦርድ አባል (የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ስራ አስፈጻሚ) ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በመቆየቱ የሚፈጠር የጥቅም ግጭት:
የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ስራ አስፈጻሚ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በኃላፊነት መቆየቱ እና የባንክ አካውንት ፈራሚ መሆኑ የጥቅም ግጭት የሚፈጥር በመሆኑ አስቸኳይ እርምት እንዲወሰድ በተደጋጋሚ ሀሳብ ቢያቀርቡም ቸልተኝነት መኖሩን ገልጸዋል። ቅርንጫፉ ሆን ተብሎ የተተወው የቅርንጫፉ ስራ አስፈጻሚ ከአቶ ጥላሁን ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠሩና የእሱ ቀኝ እጅ በመሆኑ ነው እየተባለ እንደሚነገርም አክለዋል።
5. ሰላም ማይክሮ ፋይናንስ እንዳይመሰረት ጥላሁን ከበደ እየተጫወተ ያለው ሌብነትና አሉታዊ ሚና:
አቶ ደሳለኝ እንዳመለከቱት፣ አቶ ጥላሁን ከበደ ሰላም ማይክሮ ፋይናንስ እንዳይመሰረት አሉታዊ ሚና እየተጫወቱ ነው።
6. ከኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በግፍ ለተፈናቀሉ የጋሞ ተወላጆች መብት አለመከበር:
ለተፈናቀሉ የጋሞ ተወላጆች ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ፕሮጀክት ተዘጋጅቶ ጥረት ቢደረግም፣ ፈላጭ ቆራጩ አቶ ጥላሁን ከበደ ጉዳዩ ባለመሆኑ ህዝቡ እስከ ዛሬ በችግር እየተሰቃየ መሆኑን አስረድተዋል።
7. የልማት ማህበሩ የቦርድ አባል ከሰብሳቢው፣ ከህዝቡና ከህግ በላይ መሆኑ:
አቶ ጥላሁን ከበደ “ማዶላ” ከተባለ “ቆሻሻ ሰነድ” ጋር በተያያዘ ከጋሞ ህዝብ ህልውና ጠላቶች ጋር በመተባበር ከህዝብ የተገለሉ ቢሆንም፣ ልማት ማህበሩን ሪፎርም በማድረግ ለውጥ ሲመጣ የእራሱ በማስመሰል ተከፋይ አክቲቪስቶች እንዲያመልኩት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ጥላሁን አቅምና ሀሳብ ቢኖረው ኖሮ እሱ ሰብሳቢ በነበረበት ጊዜ አሁን አጭር ጊዜ ውስጥ የተገኘውን ለውጥ ማምጣት ይችል እንደነበር ተናግረዋል።
8. በጋሞ ዞን በተለይ በሻራ እና ዘይሴ የተፈጠሩ ችግሮች እና የአቶ ጥላሁን ሚና:
አቶ ጥላሁን ከበደ “ካልደፈረሰ አይጠራም” በማለት መብታችን ይከበር ያሉ ንጹሃን ዜጎች በግፍ እንዲገደሉና ሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲፈጸም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አቶ ደሳለኝ በይፋ ከሷል።
የሟቾች ቤተሰቦች እና የፍርድ ቤት ክርክር ሂደቶችን ዋቢ በማድረግ “ህገመንግስታዊ ስርዓት በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ ነበር” በሚል የፈጠራ ክስ የተከሰሱት ንጹሃን ግለሰቦች ከግድያው ጀርባ እጃቸው የሌለበት መሆኑን ገልጸዋል።
9. በጋሞ ዞን ሰላም፣ ህግ የበላይነት እና ልማት ላይ ያሉ ችግሮች:
በጋሞ ዞን በፖሊሶችና በፖለቲካ አመራሮች የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ብልሹ አሰራሮች እና የግፍ ግድያዎችን ለማስቆም የቀረቡ ሀሳቦች “ህግ ሳይሆን ፖለቲካ ነው የማገዛው” በማለት በአቶ ጥላሁን መሳለቂያ እንደሆኑ ተናግረዋል። ይህ ደግሞ ህዝቡ ሰው ሰራሽ ችግሮች እንዲገጥመው ያደረገ ሲሆን፣ አቶ ጥላሁን በቀን 24 ሰዓት እየሰሩ የጋሞ ህዝብ የኢትዮጵያዋ ኮንጎ እንዲሆን እየተረዱ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
10. የልማት ቁጭት፣ ተነሳሽነትና ብቃት ያላቸውን የቦርድ አባላትና የተቋሙን አመራሮች መግፋት:
አቶ ደሳለኝ እንደሚያብራሩት፣ አቶ ጥላሁን ከበደ ተቋሙ ላስመዘገባቸው ስኬቶች የማይተካ ሚና የተጫወቱ የቦርድ አባላትን (ለምሳሌ እጩ ዶ/ር ወንድማገኝ ታዬን) ያለ ምንም ምክንያት ከቦርድ አባልነት አስወግደዋል።
በተጨማሪም፣ ለወራት ያለምንም ክፍያ አገልግለው በቦርዱ ውሳኔ ደመወዝ እንዲተከልላቸው ተደርጎ ጉልበታቸውን የሰጡትን የቀድሞ ስራ አስኪያጅ አቶ ትግሉ ሃይሌን ስራ ካቆሙ በኋላ እውቅና እንዳይሰጣቸው አድርገዋል ተብሏል።
በመጨረሻም፣ አቶ ትግሉ ሃይሌ ከስራ ከለቀቁ በኋላ የአርባምንጭ እርሻ ልማትን ለመቀራመት አቶ ጥላሁን ያሰማሯቸው ወንበዴዎች ዓላማ እንዳይሳካ ጥረት በማድረጉ ሽልማት ሲገባው በህገወጥ መንገድ ከስራ የተባረረውን አቶ ተካልኝ ተፈሪንም ጠቅሰዋል። አቶ ደሳለኝ በመግለጫቸው፣ ህዝብ እና መንግስት እነዚህን እውነታዎች እንዲያውቁና ተቋሙን ከጥፋት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።
እንደሚታወቀው WT ሚዲያ በተደጋጋሚ ከላይ የተነሱ ጉዳዮች ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አማካይነትና እየተካሄደ የሚገኘውን የሌብነት፣ የአድልዎ አሰራር፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ኢፍትሃዊነት፣ ከህግ በላይ ስልጣንን መጠቀም እንዲሁም ሌሎች ተጨባጭ ብልሹ አሰራሮችን በሰነድ አስደግፈን በየቀኑ ለህዝብ ይፋ እያደረግን እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው።
በመሆኑም ይሄው የርዕሰ መስተዳድሩ አከባቢ ተወላጅ እንዲሁም ስራዎችን በቅርበት ለረጅም ጊዜ እየሰራ የነበሩት ግለሰብ ወደ ህዝብ ያጋለጡት መረጃ የሚዲያችን እውነተኝነትና ለተበደለው ማህበረሰብ የምናደርገው የመረጃ አብዮት ሀቅ ያስመሰከረ ነውና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አፋጣኝና ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ እናቀርባለን።