የካዎ ጦና መናገሻ የነበረችው እና የዕድሜ ባለጸጋዋ ዎላይታ ሶዶ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትገኛለች።
ውቢቷ ዎላይታ ሶዶ 7 መውጫ እና መግቢያ በሮች አሏት።
በርካታ ተፈጥሯዊ እና ባላህዊ የቱሪስት መስህቦች ያሉባት ዎላይታ ዞን ፤ የመንትዮቹ የአጆራ ፏፏቴ መገኛ ናት።
በዎላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አጆራ ቀበሌ የሚገኝ ተፈጥሯዊ መስህብ ሥፍራ ሲሆን፤ አጆራ ፏፏቴ ሶኬ እና አጃንቾ ከሚባሉ ወንዞች የሚፈጠር ድንቅ የፏፏቴ መስህብ ነው።
የቱሪዝም መስህቦቹ ከዎላይታ ሶዶ በ56 ኪ.ሜ ከወረዳው ከተማ ቦምቤ ደግሞ በ5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሁለቱ ፏፏቴዎች ተራርቀው ገደሉን እየተምዘገዘጉ ይወርዳሉ። አጃንቾ 210 ሜትር ወደ ትልቁ ገደል ጢሰ መስሎ ይወርዳል። ሶኬ ደግሞ 170 ሜትር ቀልቁል የሚወረወር ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው፡፡

ሁለቱ ፏፏቴዎችም አንድ የሚሆኑበት ዋሻም አላቸው፡፡ ፏፏቴዎቹ ሲጣመሩም ቡቡቃ ወንዝን ይፈጥራሉ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዶንጋዎች ከርቀት በድንበር ሆነው ውበቱን ይመለከቱታል።
የአጆራ ፏፏቴዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ተፈጥሯዊ መስህብ ሥፍራ ሲሆኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኩል ዶንጋ ህዝብ ይዋስኗል።
አጆራ ፏፏቴ ሶኬ እና አጃንቾ ከሚባሉ ወንዞች የሚፈጠር ድንቅ መስህብ ናቸው። ሁለቱ ፏፏቴዎች ተራርቀው ገደሉን እየተምዘገዘጉ ይወርዳሉ። እነዚህ ሁለቱ ፏፏቴዎች ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታዎች ናቸው።
#Ebc #ebcdotstream #Landoforigins #Wolaita #Tourism #Ajorafalls