GridArt_20250724_171753266

በሲዳማ ክልል የደቡብ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉነህ ተክሉ ራሳቸውን እንዳጠፉ ተዘግቧል።

የማለዳ ምንጮች እንደገለጹት፣ አቶ ሙሉነህ የዞኑን ግምገማ መድረክ ተከትሎ ሕይወታቸው አልፏል።

አቶ ሙሉነህ ተክሉ የደቡብ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ከመሆናቸው በፊት የአለታ ጩኮ ከተማ ከንቲባ እንደነበሩም የማለዳ ምንጮች አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ በሲዳማ ክልል ውስጥ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ወሬዎች እየተሰሙ ሲሆን፣ በርካታ ግለሰቦችም እየተከሰሱ ይገኛል።

በቅርቡ የክልሉ ጸጥታ ኃላፊ መታሰራቸው ይታወሳል። የአካባቢው የመብት ተሟጋቾች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲነሱና በሌሎች እንዲተኩ ጥያቄ እያቀረቡ ነው።

ይሁን እንጂ፣ የዛሬው የአቶ ሙሉነህ ተክሉ ሞት ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ከወጡ መረጃዎች ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ እስካሁን WT ሚዲያ ለማጣራት ባደረገው መረጃ መሠረት የተገለጸ ነገር የለም።

ይህ ዜና በቀረበው መረጃ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ትክክለኛነቱ ገና ያልተረጋገጠ መሆኑን በድጋሚ እናሳውቃለን።

Ethiopia #Sidama