ከኦቶና ሆስፒታል ቃጠሎ ባሻገር የዎላይታ ዞን ምክርቤትና የዎላይታ ሶዶ ከተማ ምክርቤት በተመሳሳይ ቀን ለየብቻ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ለምን አደረጉ ?
አስተዳደራዊ አሉታዊ ጉዳዮች፣ ትኩረት መደረግ ያለበት ጉዳይ፣ የክልሉ ፈርጅ አንድ ከተሞች ነባራዊ ሁኔታ ምን ይመስላል ? ፖለቲካዊ አሉታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ (የብሄሩ ተወላጆች እና መዋቅሮች ላይ ያላቸውን ባለቤትነትና ተሳትፎ፣ ኢኮኖሚዊ አሉታዊ ጉዳዮችን፤ ህጋዊ አሉታዊ ጉዳዮችን እንዲሁም ልዩ ትኩረት በሚያስፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮች የዘርፉ ባለሙያዎች ሀሳብ ያካተተ ልዩ ጥንቅር እንደሚከተለው ዝርዝር ይዘን ቀርበናል።
ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ፖሊቲካዊ አገልግሎቶችን በተሻለ ደረጃ የሚያቀርቡ እንደመሆናቸው በከተሞች ይህንን አገልግሎት የሚፈልግ ነዋሪ በተፈጥሮ እድገትን፤ ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረገው ስደት፤ በከተሞች ወሰን መስፋፋት እንዲሁም ከሌሎች ከተሞች የሚመጡ ነዋሪዎችን በመጨመር በህዝብ ብዛታቸው ላይ ተደማሪ ለውጦችን እያስመዘገቡ መሄዳቸው እይቀርም፡፡
የከተሞች የህዝብ ብዛት መጨመር ነባራዊ እውነታ ሆኖ ነገር ግን ወደ ከተሞች የሚካለለው ወይም የሚገባው ህዝብ ቁጥር የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን፤ የስራ ዕድሎችን፤ የአገልግሎት አሠጣጦችንና የዘመነ ህይወትን ፍለጋ የሚመጣውን ነዋሪ ፍላጎት ያማከለ የከተሞች ዕድገት የማይኖር ከሆነ ከተሞች ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ መሆናቸው ይቀርና የተፋፈጉ እና በነዋሪዎቻቸው የማይወደዱ ስለሚሆኑ ተጨማሪ ኃይል መሳብ ቀርቶ ያለውንም ማስቀጠል ስለ ሚያስቸግራቸው ማርጀት ይጀምራሉ፡፡
ይህንን የከተሞች ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የከተሞችን ዕድገት ሁለንተናዊ ጤናማነት ማረጋገጥን የነዋሪዎችን የዚህ ዕድገት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግ ከተሞችን ከሚመሩ አመራሮችና ከተሞችን ከሚመሩ በየደረጃው ካሉ ተቋማት ይጠበቃል፡፡
ለዚህ ግብ አፈጻጸም ይረዳ ዘንድ በየወቅቱ የከተሞችን ደረጃ እየፈተሹ በሚደረግላቸው ምዘና መነሻ በሚያስመዘግቡት ውጤት ከተሞች ደረጃ ይወጣላቸውና የከተማነት ፍርጃቸውን ባለበት እንዲያስጠብቁ፤ እንዲያሳድጉና ወደ ኋል እንዲያፈገፍጉ ይደረጋል፡፡
በክልሉ ከተሞች በተደረገላቸው ጥናት መሠረት የፈርጅ ለውጥ ያደረጉ ሲሆን ለዚህ ጽሁፍ ዓለማ ብቻ ሲባል ቀድሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በከተሞች የደረጃ ፍረጃ በፈርጅ አንድ ደረጃ ተመድበው የነበሩ የሶስት ከተሞችን ማለትም የዎላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና የዲላ ከተሞችን ወደ ሪጂዮፖሊት ከተማ አስተዳደርነት ያደረጉትን የከተማነት የፈርጅ ለውጥ መነሻ በማድረግ የዎላይታ ሶዶ ከተማን የከተማነት ፈርጅ ለውጥ ምንነት፣ ጠቀሜታ እና ጉዳት በተመለከተ WT ሚዲያ ከዘርፉ ባለሙያዎች ያገኘውን ተጨባጭ እውነታዎችን እንደሚከተለው እንዳስሳለን፡፡
የክልሉ ፈርጅ አንድ ከተሞች ነባራዊ ሁኔታ ምን ይመስላል ?
አሁን በክልሉ በሪጂዮፖሊት ከተማ አስተዳደርነት የታጩት ከላይ የተገለጹ ሶስት ከተሞች ቀድመው ፈርጅ አንድ የከተማ አስተዳደር ከተሞች ተብለው የሚጠሩ የነበሩ ናቸው፡፡ አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተዋቀረ ከአንድ ዓመት በኋላ በከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ የከተሞችን ፈርጅ ለመወሰን ባወጣው አዋጅ መሠረት ባጠናው የዳሰሳ ጥናት መሠረት እነዚህን ሶስት ከተሞች ( ዎላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ዲላ ) በሪጂዮፖሊትነት ደረጃ እንዲፈረጁ እና በልዩ ሁኔታ እንዲያድጉ ለማድረግ በሚል ለክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ለትችት በማቅረብ ለክልሉ ምክር ቤት ለውሳኔ ለማቅረብ ዕቅድ ይዟል፡፡
ትኩረት መደረግ ያለበት ጉዳይ ምንድነው ?
👉 እነዚህ ሶስቱም ከተሞች በጋራ ዕኩል ደረጃ (ፈርጅ አንድ) ደረጃ የሚገኙ የነበሩትን ብቻ አንድ ደረጃ በማሳደግ ሁሉንም ወደ ሪጂዮፖሊት የከተማ አስተዳደርነት ማሳደግ በከተሞቹ መካከል ለፈርጅ ለውጥ የተደረገውን ውድድር የይስሙላ ያደርገዋል፡፡
👉 ከዚህም በተጨማሪ የሪጂዮፖሊ ከተማ ላለበት አከባቢ ማዕከል ሆኖ በዙሪያው ያሉ ከተሞችን አስተሳስሮ የሚያሳድግ ከተማ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ መስፈርት ስናይ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ውጪ ሌሎች ከተሞች በ20 ኪሎሜትር ራዲየስ እንኳ ሌላ የከተማ አስተዳደርም ሆነ የወረዳ ማዕከል እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ግን በ20 ኪሎ ሜትር ራዲየስ እንኳ ብቻ እንኳ 3 የከተማ አስተዳደርና 7 የማዘጋጃ ቤት ከተሞችን አቅፋለች፡፡
👉 ይህ እውነታ በከተማ ገቢ፣ በህዝብ ብዛት፣ በቆዳ ስፋት፣ በዕድገት ፍጥነት፣ በንግድና አገልግሎት ማዕከልነት፣ በቀጣይ የማደግ ዕድል ወዘተ ጉዳዮችም ጭምር በልዩነት የሚታይ ሆኖ ሳለ የዎላይታ ሶዶ ከተማን በዚህ ማዕቀፍ በልዩነት አለማየት እና ከላይ በተጠቀሱ መስፈርቶች በተመሳሳይ መዳኘት የፈርጅ አወጣጥ ስርዓቱን ወደ ፖለቲካዊ ውሳኔ የጎተተው ይመስላል፡፡
👉 በክልሉ በኩል ከዚህ ቀደም ለዎላይታ ሶዶ ከተማ የተሰጠው የከተማ ደረጃ ፍረጃ ምንም ያስገኘው ውጤት አልነበረውም፡፡ ክልሉም የፈርጅ አንድ ከተሞችን በልዩነት ለመደገፍና በሚየስመዘግቡት ውጤት ላይ ተንተርሶ የደረጃ ፍረጃ ለማከናወን የተጓዘበት ርቀት ባለመኖሬ ከተሞቹ ባሉበት ያለምንም ልዩነት የፈርጅ ለውጥ እንዲያደርጉ መደረጉ የስድስቱ የክልሉ ማዕከላት ከተሞች የዕኩልነት ውሳኔ ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡
👉 በክልሉ ውስጥ ከዎላይታ ሶዶ የሚበልጥ ከተማ ባለመኖሩ የፈርጅ ለውጥ ይኑር ቢባል እንኳን ከዎላይታ ሶዶ የሚጀምር በመሆኑ በተለየ ሁኔታ ጠቃሚ አልያም ጎጂ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡
የዎላይታ ሶዶ ከተማ የፈርጅ ለውጥ ሂደት በአዎንታዊ እና በአሉታዊ እይታ፦ በአዋጁ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 3 ተራ ቁጥር 2 ላይ የተቀመጠው የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ እንመልከታቸው።
አስተዳደራዊ አሉታዊ ጉዳዮች ምንድናቸው ?
👉 የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ መሆኑ የዎላይታን ህዝብ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ የበላይ ባለቤትነት በማውጣት የከተማውን ተቋማት ከዞኑ አስተዳደር ይልቅ ለክልሉ የላይኛው ተቋማት በማድረግ በከተማው አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የዎላይታ ህዝብን ሚና ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋው ይሆናል።
👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ በቅርቡ በመስፋት ያካለላቸው 16 ቀበሌያት የዎላይታ ሶዶ ከተማን የወደፊት ዕድገት ያማከሉ ሆነው ሳለ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስጦታነት የቀረቡ ያደርጋቸዋል።
👉 የከተሞች የፈርጅ ለውጥ የከተሞች የዕድገት መለኪያ እንጂ ከከተማው ፖለቲካዊ ተጠሪነት ጋር የሚገናኝ ባለመሆኑ ከተማዋ ባትወዳደርም በክልሉ ውስጥ በሁሉም መስፈርት የሚበልጣት ከተማ በሌለበት ተወዳድራ እንዳለፈች በማስመሠል የውድድሩን ውጤት በፖለቲካዊ ተጠሪነት ማባዛት ተገቢነት የሌለው አሠራር ነው።
👉 የኢትዮጵያ ከተሞች ዕድገት የከተሞቹ ነባራዊ ሁኔታ የፈጠረው ብቻ ሳይሆን የከተማው አካል የሆኑ ብሄሮች ሚናም ጭምር የታከለበት መሆኑ
👉 የከተማው ተጠሪነት ለክልሉ በመሆኑ መነሻ ከከተማው የሚነሱ ይግባኞች እና ቅሬታዎች በዞኑ በኩል ስለማይታዩ ወደተበታተኑት ይክልሉ የማዕከል ከተሞች ነዋሪዎች እንዲጉላሉ ያደርጋል።
👉 ውሳኔዎች ቅሬታ ያለባቸው የብሄሩ ጥያቄዎች በሙሉ ወትሮም ስለ ብሄሩ ዕድገትና ለውጥ ግድ በማይላቸው የክልል መዋቅር አመራሮች እና ባለሙያዎች እጅ እንዲወድቅ ያደርጋል።
ፖለቲካዊ አሉታዊ ጉዳዮች ምንድናቸው ?
👉 ለዎላይታ ዞን አጠቃላይ አመራር በዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ ምንም ዕጣ ፈንታ እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡ ይልቁንም የከተማው ዕጣ ፈንታ ከተለያዩ ብሄሮች የተውጣቱ አመራሮች ለሚመሩት የክልሉ ቢሮዎች ይሠጠዋል፡፡
👉 የዎላይታ ዞን እና የዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚገናኙበትን አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ገመድ ዳግም እንዳይገናኙ አድርጎ ይበጥሰዋል፡፡
👉 ለክልሉ አመራር ታማኝ የሆኑና ዎላይታ ዞን አመራር የተከፉ አልያም ስልጣን ፈላጊና ስልጣን ያጡ አካላትን ክልሉ መጠቀሚያ በማድረግ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ እንዲሾም በማድረግ በብሄሩ ዞንና በዎላይታ ሶዶ ከተማ አመራር መካከል ልዩነትና ተቃርኖ በመፍጠር የብሄሩን አንድነት እስከ ወዲያኛው ይበትነዋል።
👉 የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከተለያየ መዋቅር የሚሰየሙ በመሆናቸው ለየዞናቸው መዋቅራዊ ፍላጎት የከተማውን አመራር ሊጠቀሙበት መቻላቸው በክልሉ አመራር የፍላጎት ልዩነት መነሻ የከተማውን አመራር አንድነት ይሸረሽርና የአመራር ስርዓቱን ይበትነዋለወ፡፡ ይህም ለከፍተኛ ጣልቃ ገብነት በር ይከፍታል።
👉 የብሄሩ ተወላጆች እና መዋቅሮች በዎላይታ ሶዶ ላይ ያላቸውን ባለቤትነትና ተሳትፎ (ሹመት ቀርቶ) ያርቀዋል።
👉 የዎላይታ ዞን አስተዳደር የብሄሩ መሪ (የዎላይታ ህዝብን ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚያስፈጽም መዋቅር) ሆኖ ሳለ የዎላይታ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ማዕከል በሆነችው እና በመላው ዎላይታውያን የለማችው ከተማ ላይ የመወሰን ምንም ዓይነት ዕጣ ፈንታ አይኖረውም፡፡
👉 አሁን ባለው ነባራዊ ሀገራዊ ሁኔታ የፌዴራል ከተሞች ተብለው ከተለዩ ሁለት ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ውጪ የብሄር ከተሞች ሆነው ለሌሎች የአስተዳደር እርከኖች ተላልፈው የተሰጡ ከተሞች አለመኖራቸው ( አዳማ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ ሽሬ፣ ሀዋሳ ተጠሪነታቸው ለክልል ይሁን እንጂ ከተሞቹም ክልሉም የአንድ ብሄር መሆናቸው )፤
👉 የክልሉ መንግስት የዎላይታ ሶዶ ከተማ በዋናነት በነዋሪዎቿ ጥረትና ድጋፍ ያደገች መሆኗ ይታወቃል፡፡ የክልሉ መንግስት የዎላይታ ሶዶ ከተማን ከብሄሩ ነጥሎ የመውሰድና የማስተዳደር ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት የብሄሩን አስተዳደርና የዞኑን ምክር ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ መሄዱ ልዩ አሻጥር ያለበት መሆኑ ( ምንም እንኳ እነዚህ አካላት ከተማዋን ከብሄሩ ቆርጠው ለሌላ አካል የማስተላለፍ ስልጣን ባይኖራቸውም)፤
👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ ጉዳ የሁሉም የዎላይታ መዋቅሮች እና ህዝብ ጉዳይ ሆኖ ሳለ የተቀሩት 22 መዋቅሮችም ሆነ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም አጠቃላይ የዎላይታ ህዝብ እንዲያውቅ አለመደረጉ፤
ህጋዊ አሉታዊ ጉዳዮች ምንድናቸው ?
👉 በኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1 የተቀመጠው የብሄር ብሄረሰቦችን ህዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ህገ መንግስታዊ መብትን የሚጻረር በመሆኑ፤
👉 የብሄር ብሄረሰቦችን ህዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ህገ መንግስታዊ መብት ብሄሩ በሚኖርበት ጂኦግራፊያዊ ድንበር ውስጥ የሚተገበር መሆኑና የዎላይታ ሶዶ ከተማ የዎላይታ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር የጂኦግራፊ ወሰን ውጥ የምትገኝ በመሆኗ፤
👉 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደረጃጀት ( ማዕከላዊ ኢቲዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵ ክልሎችን ይጨምራል ) ዞኖች ከሌሎች የሃገሪቱ ክልሎች ማለትም ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ ወዘተ አንጻር የተለየ አደረጃጀት ያለውና በዞን ደረጃ ህግ አውጪ ክንፍ ያላቸው የብሄረሰብ ዞን መሆናቸው፤
👉 በዚህም የዎላይታ ዞን በዞን ደረጃ መንግስት ያለው የብሄረሰብ ዞን ( ሶስቱንም የመንግስት አካላትን ይዞ) እንጂ እንደ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል ዞኖች በዞን የአስተዳደር ዕርከን የሚመራ አለመሆኑ ( በኦሮሚያ እና አማራ ክልል ዞኖች ዞኖች አስተዳደር የተሰየመላቸው የአስተዳደር ዕርከኖች እንጂ የህግ አውጪው ምክር ቤት የሌላቸው መሆኑን ልብ ይሏል)፤
👉 ከተማው ለክልል ተጠሪ እስከሆነ ድረስ የብሄሩን ፍላጎት ብቻ የሚከተል ሳይሆን በረጅም ጊዜ የክልሉና የሌሎች ነዋሪዎች ፍላጎት በሚል ሰበብ ከተማዋን ከብሄሩ እጅ እና ክትትል ለማውጣት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።
ኢኮኖሚዊ አሉታዊ ጉዳዮችስ?
👉 የከተሞች ፈርጅ የከተሞች የዕድገት ደረጃ መለኪያ እንጂ የከተሞች ተጠሪነት መወሰኛ አይደለም፡፡ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ እጅግ የሚበልጥ ዕድገት ላይ ያሉ ከተሞችም ጭምር ( አዋሳ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ ወዘተ) ከብሄር ተጠሪነት ባልወጡበት ክልል በሚል ካባ ብቻ ብሄሩ ብቻ ለማይመራው መዋቅር ተጠሪ ማድረግ ከተማዋን የመዋጥ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የከተሞች የእድገት ደረጃን በፖለቲካ ተጠሪነት ሰበብ ለመቸንከር የታቀደ ዓላማ ነው፤
👉 የክልሉ መንግስት ከተደራጀ ጀምሮ ለዎላይታ ሶዶ ከተማ የመጣን ዕድል ከመቀማት ውጪ ለከተማው ያበረከተው አንዳች ልማት ስለሌለ ለከተማው እድገት የሚጨነቅ አይደለም፡፡ እንዲሁም ወደፊት ከተማው አቅዶ የሚሰራቸውን የልማት ፕሮጀክቶች መረጣ እና አካሄድ እንዲሁም ትግበራ ላይ በቀጥታ ጣልቃ እየገባ እንዲያሰናክል ዕድል ይሰጠዋል፤
👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ በልዩ ፍጥነት ካደጉ የኢትዮጵያ ከተሞች ( በተለይም ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት አመታት ) ተርታ የተሰለፈችው በብሄሩ እና ነዋሪ ህዝቦች ድጋፍ፣ መዋጮ እና ተሳትፎ እንዲሁም የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ድጋፍ ሆኖ ሳለ በከተማው እድገት ውስጥ እዚህ ግባ የማይባልና ብሄሩንም ጭምር ከፖለቲካ ስልጣኑ የሚገፋው የክልል መዋቅር የከተማውን ተጠሪነት ለክል ላድርገው ብሎ ለመወሰን መሄድ ለብሄሩ ይሁኝታ ያለውን ንቀት ማሳያ ነው፤
👉 የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ 2005 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ ገቢ የሚተዳደር ከተማ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዎላይታ ዞን ዓመታዊ የበጀት ቀመር የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎችን የሚያካትትና ዞኑ በከተማው ነዋሪዎች ስም ጭምር የሚያገኘውን በጀት ከተማው በራሱ በጀት ስለሚተዳደር ለቀሪ ወረዳዎች በማከፋፈል ዞኑ ያለበትን የበጀት ጉድለት ይመራበታል፤
👉 ይሁን እንጂ አሁን በተያዘው ከተማዋን ለክልሉ ተጠሪ የማድረግ ሴራ በከተማው ህዝብ ቁጥር በጀት ከዞኑ ይቀነስና ከተማው ደግሞ ራሱን በራሱ ስለሚያስተዳድር ለክልሉ ፈሰስ እንዲደረግ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻውን ከዎላይታ ዞን በጀት ብዙ መቶ ሚሊዮን ብሮች እንዲቀነሱ ያደርጋል፤
👉 የከተማው ሁለንተናዊ ዕድገትና እንቅስቃሴ ከዎላይታ ብሄር ፍላጎትና ዕቅድ ውጪ የሚመራ ይሆናል።
ልዩ ትኩረት መደረግ ያለበት ጉዳይስ ?
በየትኛውም መልኩ የሚቀርብ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ማህበራዊ መደራደሪያ ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ለክልል ተጠሪነት አንጻር በፍጹም፣ በፍጹም ልዩንት እንዲያመጣ መፈቀድ የለበትም።
በመሆኑም ከላይ በዝርዝር የቀረበው ማብራሪያ የዛሬው ኦቶና ሆስፒታል መቃጠል መንሴ ምንድነው ለሚለውንና በዛሬው ዕለት የዎላይታ ዞን ምክርቤት እና የዎላይታ ሶዶ ከተማ ምክርቤት ተመሳሳይ ቀን ለየብቻ ጉባኤ ለምን አደረጉ ለሚለው በቂ ምላሽ ሰጥቷል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WT ሚዲያ👏