በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲሆን የማይሰራ ህግ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንዴት ሰራ?
ዎላይታ ሶዶ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስተዳደርና ፖለቲካ ማዕከል የማዕከላዊ ክልል ፖለቲካና አስተዳደር ማዕከል ሆሳዕና ከተማ ነው። ነገር ግን የሀገሪቱ ህግ ሁለቱም እኩል የሚጎናፀፉት ህገመንግስታዊ መብት ቢኖራቸውም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከአሰራር ውጪ ይፈፀማል።
ባለፈው አመት 19ኛው ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ መከበሩ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለመከበር ሲወሰን በክልሉ አስተዳደርና ፖለቲካ ማዕከል ወይም በክልሉ ዋና መቀመጫ በሆነችው በዎላይታ ሶዶ ከተማ እንደሚሆን ሀገር ያወቀውን ሀቅ ሲሆን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በትውልድ አከባቢያቸው አስከብረው ነበረ።
የዚህ ፅሁፍ አላማ ኢፍትሃዊነት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከልክ ባለፈ መልኩ የክልሉን በጀት ስታድየም ግንባታ በሚል የክልሉ ገፅታ ለመቀየር በሚል በርካታ ቢሊዮን ብር ባክኗል።
ይህን ለማክበር ሲባል የምክር ቤት መቀመጫ ባለበት ከተማ ብሎ ቀጥታ አርባምንጭ ሲወስድ በወቅቱ የዎላይታ ሙሁራን ወጣቶች የሀገር ሽማጌሌዎች ሳይቀሩ ሲጮኹ ነበረ ሰሚ አጡ እንጂ ዛሬ ላይ ተመሳሳይ ኢቨንት በማዕከላዊ ክልል ዋና መቀመጫ ሆሳዕና ከተማ እንዲከበር ከሞት የተረፉት አቶ አገኘው ተሻገር መግለጫ ሲሰጥ ተመልክተናል ይህ ግፍ ይህ ኢፍትሃዊነት ይህ ለአንድ አከባቢ ብቻ የሚደረግ ልማት ዛሬም በሌሎች ልማቶች መቀጠሉ ያሳዝናል ያሳዝናል በሚል በርካቶች እየገለፁ ይገኛሉ።
አስተያየት ሰጪዎቹ “አሁንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ አጠቃላይ ልማቶች ከ70% በላይ በአንድ አከባቢ ነው ዶ/ር አብይ ይህንን ጉዳይ ሳይረዳ የቀሩ አይመስለኝም በቀጠናው በሚያደርጉት ጉብኝት እንደማሳያ በማቅረብ በተለይ ዎላይታ ሶዶ ከተማን ጨምሮ በሌሎች አከባቢዎች የሚደረግ የኢፍትሃዊነት ችግርን ማጋለጥ ያስፈልጋል” ብሏል።
ጩኼቱ ከሁሉም አከባቢ መሆን ካልቻለ እንኮን የዎላይታ ሶዶ ከተማ በ19ኛ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በአልን የማክበር ህገመንግስታዊ ሞራላዊ ኢክኖሚያዊ ብቃት እያላት በአድሎና በኢፍትዊነት ምክኒያት ተከልክላ ወደ አርባምንጭ ከተማ በርዕሰ መስተዳድሩ የዞረው ዎላይታ ከነበረበት ክልል ውጪ ሲሆን ግን በቀጥታ ለአስተዳደርና ፖለቲካ መቀመጫ ወደ ሆነችው ሆሳዕና ከተማ መደረጉ የተፈፀመና እየተፈፀመ ያለን በደል ለማስታወስ ነው።
“አሁንም ቢሆን ለማሳያነት ነው እንጂ በብዙ መልኩ በደል እየደረሰ እንዳለ ማወቅ እንዲቻል ነው። የሆሳዕና ከተማ ወጣቶች ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ክብራችሁን በትክክል እናንተ አስመልሳችሃል ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን በአስተዳደራዊ በደል ውሰጥ ነው በተለይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በሚፈፀም አድሎአዊ አሰራር ገደብ የለለው ሆኖ ቀጥሏል” ብሏል።
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብሄር ብሄረሰቦች ታፍነው በሚኖሩበት ዞን እንዲከበር መደረጉን ተከትሎ ለስታዲየም ግንባታ ተብሎ በዓል አከባበር ወቅት ከየዞኖች፣ ከክልል መዋቅሮች እንዲሁም ከባለሀብቶች የተሰበሰበው ዳጎስ ያሉ ገንዘብ ገንዘብ አሁን ላይ የአርባምንጭ ከተማ አስፋልት፣ ኮሪደር ልማት፣ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት፣ መንገዶች ከፈታና የወንዝ ዳር ልማት ተብሎ ለአንድ ዞን ብቻ ልማት እየተሰራ እንደሚገኝ ታማኝ ምንጫችን አረጋግጠዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በርዕሰ መስተዳደሩ ኢፍትሃዊነት ምክንያት በክልሉ ክላስተር ከተሞች ላይ የመንገድ፣ የንፁህ የመጠጥ ውሃ፣ የመስኖ ግንባታ፣ የጤና፣ የኤሌክትሪክ፣ የድልድይ እና የቴሌኮም አገልግሎትና ሌሎች የመሠረተ ልማት ግንባታ ጥያቄዎች በተመለከተ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ትኩረት ካልተሰጠ አደገኛ ሁኔታ መኖሩ እየተሰማ ይገኛል።