1000070311

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥሌ “ቀዳሽ” ጥሌ “ተኳሽ” የፓክስታን ጥንቆላ ግብር

በፖለቲካ ተንኮል እና ደባ ያለ አቅሙ ከተፈናጠጠዉ የስልጣን ኮርቻ ሊፈነገል የተቃረበዉ አቶ ጥላሁን ከበደ በድብቅ ሲከዉን የነበረዉን “የተመረጠ ይልማ ሌላዉ ይድማ” የሙከራ ዉጥኑ /pilot projecet/ በመጠኑም ቢሆን ተሳክቶለታል፡፡

ከዚህ ቀደም በሐቅና በላባቸዉ ደክመዉ ጥሪት ካፈሩ የጋሞ የተከበሩ የግል ባለሃብቶች ትይዩ ፖለቲከኛ ከበርቴዎችን እና ድንገቴ ቱጃሮችን ፈብርከዉ ስኬታማ እንደሆኑም ይኩራራሉ፡፡

ችግሩ ግን ሃብት ማካበትን እና ጥሪት ማፍራትን “የእኔ” ለሚሏቸዉ ግን “የእርሳቸዉ” ባልሆኑ ግለሰቦች ዘንድ ጊዜያዊ ፌሽታን ይፈጥር ይሆን ይሆናል እንጂ ስለዘላቂነቱ እርሳቸዉ ራሳቸዉ እርግጠኛ አይደሉም፡፡

አብዛኛዎቹ ደግሞ “በእርሳቸዉ እና በስብስባቸዉ ፊት” የእርሳቸዉን ስም እንደ “ቅዱሳን” ገቢራቸዉን እንደ “ገድለ ጥላሁን” የሚዘክሩ ቢሆንም ከጀርባ የሚያወሩት ስለ ጊዜያዊ ጥቅም የኢኮኖሚ አሻጥሩም ለፖለቲካዊ መንበረ ጵጵስና ሲሉ የሚያደርጉት መሰይጠን እንደሆነም ደቀመዝሙሮቻቸዉም ሆኑ ርዕሰ መስተዳድሩ ራሳቸዉ አይጠፋቸዉም፡፡

ዛሬ ለፖለቲካ ሽቀጣ ያጀቧቸዉ እና በድብቅ “የፋነኑ” ንዑሳን ከበርቴዎች ነገ አብሯቸዉ እንደሚቆሙ መተማመኛ የላቸዉም ርዕሰ መስተዳድሩ ራሳቸዉ፡፡

ለዚህ እንደምሳሌ ብናነሳ ልከኛ ጠቋሚ የሚሆነዉ በአርባምንጭ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት ህንጻ መገንባት ጀምሮ ተንኮላቸዉ አልዋጥ ሲለዉ ያፈነገጠዉን “ተስፈኛ ባለሃብት” ከጅምር ህንፃዉ ምድር ቤት ዉስጥ ፈቅደዉለት አከማችቶ ይነግድ የነበረን ቤንዚን እና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር አዉለናል በሚል አስረዉት ከፍርድ ቤት እያመላለሱት ይገኛሉ፡፡

የልጁ ሀጢያት በሴራ ትብታብ መንገዳችሁ አልጓዝም በቃኝ ወደ ቀድሞ ማንነቴ ልመለስ ማለቱ ብቻ ነዉ፡፡ ቦረዳ ላይም የከሰል ማዕድን በሽርክና እንስራ ብለዉት በሚሊዮን የሚቀጠር አንጡራ ሃብቱን ካፈሰሰ በኋላ የከሰል ማዕድን ቦታዉ የፌደራል ፍርድ ቤት ዕግድ ያለበት ነዉ ሲሉ መልሰዉ ቀሙት፡፡

እርሱ ያለማዉን የዕግድ ስፍራ ደግሞ ከፍርድ ቤቱ ተጠያቂነት ቢያተርፈን ብለዉ ለጋሞ ልማት ማህበር አስተላለፉ፡፡

ከልጁ እስርና ማንገላታት ጀርባ ለጥላሁን በወደር የለሽ ተላላኪነቱ የሚንቆለጳጰሰዉ በዱባይ የአፓርታማ ባለቤት የሆነዉ የብርሃኑ ዘዉዴ እጅ የት ድረስ እንደሚረዝም በፖሊስ መዋቅርና እንደ ቀልድ በየጀበና ቡና ቦታ የሚነገር እዉነት ነዉ፡፡

ሌሎችን ለማክሰም የሚኬድበት የኢኮኖሚ አሻጥር “ከእኔ ዉጪን” በአዕምሯቸዉ አጭቆ ሌላዉን እንደ ዜጋ መቁጠር እንኳን እስኪሳናቸዉ ስለመዝለቁ እኛ የአርባምንጭ ነዋሪዎች የምናዉቀዉን ሌላ እዉነት እንጨምርበት፡፡

ሻለቃ ሃይሌ ገብረ ስላሴ አርባምንጭ ላይ ሪዞርት እገነባለሁ ሲል ፕሮፖዛል ይዞ ከወቅቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ ቢሮ ገብቷል፡፡ በደቂቃዎች ዉስጥ የፓራዳይዝ ሎጅ ባለቤት እንዴት ተደርጎ ሲሉ ከተማችንን ወደ ማመስ ገቡ፡፡ ምክንያትዎ ምንድነዉ ሲባሉ ደግሞ “የእኔ ሪዞርት ዳዋ ሊለብስ አራሙቻ ሊበቅልበት ነዉ” ሲሉ ለያዥ ለገላጋይ አስቸገሩ፡፡

የዞኑ አስተዳዳሪ ሀገሪቱ የምትከተለዉ ነፃ ገበያ ነዉ በዉድድር እንጂ በሞኖፖል የሚያዝበት ዘመን አክትሟል ሲሉ የባለሃብቱን ዉሃ የማያነሳ አቤቱታ ዉሃ ቸለሱበት፡፡

የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስን በስልጣንህ አትቆያትም ዛቻ በባለ ሃቱ አቶ ኢያሱ እንደ ቀይና ነጭ ሽብር ተፋፋመ፡፡

ረብጣ ብሮችን የዘሩት አቶ ኢያሱ ተሳካላቸዉና ዋና አስተዳዳሪዉ ብዙም በስልጣናቸዉ ባይቆዩም ሃይሌ ምኑ ሞኝ ነዉ ፕሮፖዛሉን ፌደራል ወስዶ መሬት ስጡት አስባለና ለከተማችን ሌላ ጌጥ የሆነ ዘመናዊ ሪዞርት አጎናፀፈን፡፡

በእርግጥ አቶ ኢያሱ ወሰንም የፈሩት አልቀረም፡፡ ዘመናዊዉ ሃይሌ ሪዞርት ዘምኖ መጣና የአቶ ኢያሱን መኩራሪያ የአራሙቻ ብቻ ሳይሆን የከርከሮ መፈንጪያ አደረገዉ፡፡

እነ ጥላሁን እና ሌሎች ካድሬዎች ሄደዉ ካደሩበት እንጂ ለፎቶ እንኳን የሚሄድ የአርባምንጭ ነዋሪ እና ጎብኚ ጠፋ፡፡

በዚህ ቂም ያሳደሩት እና ለበቀል ያደቡት አቶ ኢያሱ ወሰን ፊንፊኔ ዙሪያ ሰበታ አካባቢ የደረሰን ጥቃት ተንተርሶ ወጣቶች ቁጣቸዉን ሲያሰሙ የጋሞ አባቶች ሰላም ለማዉረድ እርጥብ ሳር ይዘዉ ሲንበረከኩ አቶ ኢያሱ ግን አፍላ ወጣቶች በሃይላንድ ፕላስቲክ ቤንዚን አስይዞ ሃይሌ ሪዞርትን እንዲያቃጥሉ ሲያሰማራ እንደነበር አምላክ አይቷል፤ ኢያሱም አይክድም፤ ያሰማራቸዉ ወጣቶች እና የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጠንቅቀን እናዉቃለን፡፡ ‹ ዕድሜና ጤና ለጋሞ አባቶች ይሁንና የሚንቀለቀልን እሳት በእርጥብ ሳር አብርደዉ ታላቅ ታሪክ ሰሩ፡፡

የጥላሁን ሩጫ መሰል ባለሃቶችን ማበራከት ነዉ ግቡ፡፡ በጋሞ ስም የሚነግዱ ከራስ በላይ ንፋስ የሆኑ ደሃዉን የፈጠሩ የሚመስላቸዉን ባለጠጎችን ነዉ ጥላሁን እየሄደ የሚመረኮዘዉ፡፡ ልክ እንደ እርሱ አብዛኛዎቹ የጋሞነትን ማንነት እና ስነ ልቦና ኖሯቸዉ ሳይሆን ለጥቅማቸዉ ተመሳስለዉ የሚሸቅጡ ናቸዉ።

ኢያሱ ወሰን ስለ ጎንደሬ አማራነቱ እንጂ የሚፎክረዉ ስለጋሞነቱ ሲያወራ አይደመጥም፡፡ ባስ ያለ የብሄር ማንነት ወሬ ሲነሳ እናቴ የገረሴ አካባቢ ሴት ናት ይላል። በነገራችን ላይ የጥላሁን እና ኢያሱ ወሰን የጥቅም አጋርነት ከኢትዮጵያ አልፎ እስከ ፓኪስታን ይዘልቃል፡፡ የፓኪስታን ጉዟቸዉ ደግሞ ለጥንቁልና መንፈስ ግብር መሆኑንም በገደምዳሜዉ ሰምተናል፡፡

ጥላሁን ከጨለማ ቤት የማይወጡ አያቱ ጨሌ እየቆጠሩ የሚካድሟት አቴቴ ብዙም እየረዱት አይደለም ሲሉ የሚያሙትም አሉ፡፡ እኛ ግን እንላለን ዶ/ር ዐቢይም ጥላሁን ላይ ርምጃ የማይወስዱት በእርሳቸዉ አቴቴ ልመና ይሆንን/ ከመሳቅ ዉጪ ምን ይባላል፡፡

ሌላኛዉ የአርባምጭ ከተማን የዉስጥ ለዉስጥ አስፓልት ግንባታን ለአመታት የተኛበትና ግጦ የበላዉ የጋሞን ለምድ ለብሶ የሚነቀሳቀሰዉ ፍጹም ታዬ የሚባል ቡርዧ ነዉ፡፡ በመንገድ ግንባታዉ ጥላሁንን በጥቅም ሸብቦ ከህግ ተጠያቂነት አምልጧ ተብሎ የሚታማዉ አቶ ፍፁም ሚስቱን እና ልጆቹን ከባህር ማዶ እያኖረ በጋሞ ስም ሲቸረችር አንዳች አያፍርም፡፡ አቶ ፍፄን ስለ ጋሞነት ብታነሱበት ያልተደወለለትን ስልክ ሃሎ እያለ ከአጠገባችሁ ካልሄደ ከምለሴ ፀጉር፡፡

አቶ ጥላሁን በዚህ ልክ የእርሱን የጥቅምና የዝርፊያ ጀሌዎች ሲያደራጅ ከጂንካ እስከ ሶዶ ከሳዉላ እሰከ ዲላ ያሉ ሌሎች ነጋዴዎች ይኮሰምኑ ዘንድ የማይፈነቅለዉ ድንጋይ የለም፡፡ እሱ የዉጪ ዜጎች የዩንቨርሲቲ መምህራን በግድ ተከራይተዉት በየወሩ የሚለቅመዉ የጫሞ ካምፓሱ አፓርታማ፤ የክልሉ ቴ/ሙ/ት/ስ ቢሮ ያለጨረታ ወርሃዊ የ4 መቶ ሺህ ብር ኪራይ ቁማር/ የቢሮ ሃላፊዉ የአቶ አብዮት ትግልና ኩርፊያ እንዲሁም የሮሚና የጥላሁን የዝርፊያና ሌላ ግለሰባዊ ሽርክና ተከድኖ ይብሰል ብንልም እዚህ ጋር ሳንጠቀስ አናልፍም/፤ ብርሃኑ ዘዉዴ ከሚመራዉ ቢሮ ፊት ለፊት የክልሉ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ኪራይ ላይ ያለ ቁማር መንግስት ሲነቃ መዘዙ ብዙ ይሆናል፡፡

አቶ ጥላሁን አንተ በሰላም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም/የማስመሰያ የ100 ሺህ ብር አክሲዮን ግዢህ ባሻገር ያለህን ድርሻ /አደራ የኦሞ ባንኩንም እናዉቃለን/ በዚያ ልክ ሃብት ማካበትን እየተረማመድክበትና የፍትሃዊነት ትግል ጥያቄን የብሄር ዘዉግ እያላበስከዉ ከሄድክ ክልሉንም አንተንምና ባንተ ዙሪያ የተሰበሰቡት ሳሩን እንጂ ገደሉን ማየት የተሳናቸዉን ይዘህ ትገነደሳለህ፡፡ አወዳቅህም አያምርም፡፡

ዎላይታዎቹን ያዕቆብ አልታዬን፤ ጥላሁን ፋንታን፤ ፈለቀ ፋንታ ዞኮሎን፤ ማራ ማይነርስን የመሳሰሉ ባለሃብቶችን ስልጣንህን መከታ በማድረግ አንዴ በባንክ ብድር ዕዳ አመላለስ አንዴ ደግሞ በግብር እያሰፈራራህና የኢንቨስትመንት ፍቃዳቸዉን እየሰረዝክ ማሳደዱን ተያይዘኸዋል፡፡

አባቴ ስልጣን ያዉም የአሁን ትቢያ በለዉ፡፡ በወላይታና በወንድም የጋሞ ህዝብ መሃል የምትገነባዉን የጠብ ግድግዳ ለዘመናት አብሮ የኖረ ህዝብ ነዉና ግድየለህም በቁምህ የገነባኸዉ ግንብ ሲናድ ታያለህ፡፡የጋሞ ህዝብ አንተ በቁጥር አደራጅተህ በስሙ የምትነግድበት 10 ወይ 20 አይደለም፡፡

ሰሞንኛ ወሬዎች፡-

ከአንድ ሌብነታቸዉን በሚዲያ ካጋለጠ እና ሃቁን ከፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ወስዶ የሚሞግትን ግለሰብ ጉዳይ እንደ ጉድ እያጯጯሁት ነዉ፡፡ ራሳቸዉ የለጠፉት የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ቅጂ እንደሚያመላክተዉ የመጨረሻ እልባት ያገኘ አይደለም፡፡ ችሎቱም ከዚህ ቀደም ያገደዉን እግድ አንስቷል፡፡ ጉዳዩ በግልግል ዳኝነት እንዲታይ ይላል፡፡ ለይግባኝም ክፍት ነዉ፡፡ ዛሬ የተነሳ እግድ ነገ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍድ ቤት አሊያም በግልግል ዳኞች ሲታገድ ምን ዉስጥ ልትገቡ ይሆን ( እረ የሰከነ ሰዉ እንጣ ከመሃላችሁ ( ወ/ሮ ሄለን እንደዚህ በዚህ በቀላሉ የሚረሳ አይደለም የፈፀምሽዉ ብልሽት፡፡

ምርመራ የሚያስፈልገዉ የምርመራ ዘገባ ብለዉ ሚሊየን ብር አዉጥተዉ አሰሩ፡፡ የሚቀበላቸዉን ኦፊሺያል ሚዲያ አጡ፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ በቅርብ ቀን አሉ፡፡ እስቲ እየጠበቅን ነዉ፡፡ ግለሰቦችን እና ፋና ሚዲያን ነዉ አሉ ስድቡ፡፡ የተዋጣዉ በሚሊየን የሚቆጠር ብር ዞግ #ዱፄም አፍ ፈታ አሉ በዚህኛዉ ዘገባ፡፡ አፀደም ለያዥ ለገላጋይ አስቸግራለች፡፡ በልጇ ስም በተሰየመ PLC የማዕድን ቦታ ወስዳ ሸንሽና ስለመቸብቸቧ አናዉቅም አሉ ( ፖርታል ላይ ያለ ፋይል ከሰርቨር ለማስጠፋት ደቡብ አፍሪካ ድረስ መኳተናችሁንም አልሰማንም አሉ! አፄ በልጅሽ ስም ከባለሃብቶች የተላከልሽንም ብር እናዉቃለን/ ምን እንኳን ተቸግሮ ተበድሮ ነዉ ልጄ እያልሽ ብተለፈልፊም/ ጊዜዉ ሲደርስ እርሱም ከነ ባንክ ስሊፕ ጀባ ይባልልሻል፡፡ #ከዎላይታ ህዝብ ጫንቃም ላትመለሺ ትወገጂያለሽ፡፡

ከወደ ፖለቲካዉ ንግድ ደግሞ

ከብቸኛ ደጋፊዉ አደም ፋራህ ፊት የተነሳዉ ጥላሁን ሙስጤፌ ጋር ገጥሞ ሼክ ካልሆንኩ እያለ ነዉ፡፡ አማልደኝ #ከአደም ፋራህ ነዉ ነገሩ፡፡ ተከትሎትም ፊቼ ጫምባላላን ሊያከብር ሀዋሳ ገብቷል፡፡ ከኦቦ ሽሜ እግር ስር ሊወድቅ መሆኑን ሰምተናል ደስታን እና ሙስጠፌን ይዞ አትርፈኝ ነዉ ልምምጡ፡፡

ወጣቱ ፖለቲከኛ ኦቦ ሽመልስ ጥላሁንን በብዙ መዝኖት ዉሃ የሚያነሳ መሪ አለመሆኑን ከተረዳ ቆየ፡፡ ሁለት ነገሮችን ላንሳ እዚህ ጋ፡፡

አንደኛዉ ጥላሁን በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ጉዳይ ኦሮሚያን በተደጋጋሚ በሚዲያዎች ያዘልፋል ተስፋፊ ሃይል እያለ፡፡ ጥልዬ ኦሮሚያ ራሱ ሀገር ሆኖ ያንተ ቁራጭ የአዉሬ መፈንጫ ሜዳ ምን ያደርግለታል ብለህ ነዉ(! እረ ኦቦ ሽሜ መቼም ትዝ አትለዉም፡፡ ሁለተኛዉ ደግሞ እየተገነባ ያለዉ የአርባምንጭ ስታዲየም ቀድሞ ኦርቶዶክሳዊያን ለጥምቀት ከተራ ይከትሩበታል፡፡ ከኢዜማ እና እናት ፓርቲ የተወጣጡ በአማራ ስነ ልቦና የተጠመቁ ወጣቶች ያምፁ ዘንድ ከጀርባ ጎነጎነ፡፡ ብዝሀ ማንነት ባለዉ ክልል በሃይማኖትም ሽፋን መጫወት አማራት ጥሌ፡፡ ብዙ ወጣቶች ታሰሩ፡፡ የአዱገነት ከንቲባ አዴ አዱ እና ኦቦ ሽሜ መረጃዉ ደርሷቸዉ ጥሌን ጥንብ እርኩሱን አዉጥተዉ አጀንዳዉን ዘጉት፡፡

ሌላ ራሱን የቻለ ግዙፍ እዉነት አርባምንጭ ፓራዳይዝ/ የኢያሱ ቤት/ የፌደሬሽን ምክር ቤቱ ጉምቱ እንዳመጣላቸዉ ይዘባርቃሉ ያሽካካሉ፡፡ ለስጋ ደስታ የሚሰጥ ሁሉ ተሟልቶላቸዋል፡፡ በዚህ ንግግራቸዉ ግን ጥላሁን ተነስቶ ገንፎ ሲያጎርሳቸዉ ሌሎች ታዳሚያን ግን ተሳቀቁ፡፡ እዉነት ይህ ሰዉ ስለ ብሄር ብሄረሰቦች መብት ይሟገታል ሲሉ አዘኑ፡፡ በስካር መንፈስ በአልኮል ድንዛዜ የተወረወረችዉ አረፍተ ነገር እንዲህ ትላለች “የቁጫ እና የዎብን ተወካዮች ጨርቃቸዉን/የባህል ልብስን መሆኑ ነዉ/ ለብሰዉ ሲመጡ ወደ ቢሮዬ አጥር እንዳይደርሱ አድረጊያለሁ”

ይህ የተጠና የጥላሁን የዎላይታ ባለሃብቶችን የማክሰርና የማዋረድ ተግባር በጊዜ የማይገታ ከሆነ ክልሉን ወደ ማይወጣበት አረንቋ ማንደርደሩ አይቀርምና በተለይ የዎላይታ አመራሮች ዛሬን ሳይሆን ነገን አሻግሮ በመመልከት ከህዝብ ጎን በመቆም እነኚህንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ባለሃብቶቻችንን ለማዳን መንቀሳቀሻ ጊዜዉ ነገ ሳይሆን ቅዱስ ቃሉ እንደሚለዉ ዛሬ ነዉ፡፡

ትንታኔው በዚህ አልበቃም ይቀጥላል …….