1000070728

“የጥላሁን እና የተፈሪ አባተ የዝርፊያ ወዳጅነት ነቁጥ ማሳያ” – የአይን አማኝ ምሁር ምስክርነት

“አሸናፊ አርሼ የተባለ ኮንክራክተር አርባምንጭ መምህራን ትምህር ኮሌጅ ያወጣዉን የተጨማሪ ብሎኮች ግንባታ ጨረታ አሸንፎ ግንባታዉን እያፋጠነ ክፍያ ይጠይቃል፡፡ ክፍያዉ ሲዘገይበት ስልክ ያነሳና ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ይደዉላል፡፡ አቶ ተፈሪም ስልክ ያነሳና “ምንድነዉ 10 ሚሊየን ላይ ችክ የምትለዉ” ሲል አቶ አሸናፊን አስደንግጦ ስልክ ይዘጋበታል፡፡

አቶ አሸናፊም እንዴ የሰራሁትን የጠየኩት ሲል ተደናብሮ ክፍያዉን ዝቅ አድርጎ ዳግም ለመጠየቅ እያሰበ እያለ አቶ ተፈሪ ለአቶ አሸናፊ ደዉሎ ነገ ዎላይታ ሶዶ እና እንነጋገራለን ብሎ ዘጋ፡፡

አቶ አሸናፊም በተባለዉ ቀን ሶዶ ከተመና መጥቻለሁ አለዉ አቶ ተፈሪን፡፡ አቶ ተፈሪም ሁነኛ ሰዉ እልካለሁ ከእርሱ ጋር አዉራ፤ የሚልህን በአግባቡ አድምጠህ ግብር ሲል መንግስታዊ የሌብነት ጉዳይ ገዳዩን በወቅቱ የክልሉ ግዢ ኤጀንሲ ላይ በሃላፊነት ይሰራ የነበረዉ ከቁጫዉ ተወላጅ ጋር በሶዶ ሌዊ ተገናኘ፡፡

በዉይይታቸዉ የተፈሪ “ምንድነዉ 10 ሚሊየን ላይ ችክ የምትለዉ” ንግግር በቁጫዉ አደራዳሪም ተደገመ፡፡ ኮንትራክተሩ ምንድነዉ የምትፈልጉት ሲል ፍላጎታቸዉን ጠየቀ፡፡ 10 ሚሊየን የሚለዉን ተዉና 40 ሚሊየን ክፍያ ጠይቅ የድርሻህ 10 ሚሊየን ይሰጥሃል፤ ሌላዉ ለሌላ ስራ ማስፈፀሚያ ይዉላል ይህንን ተግብር ብሎ አስጠነቀቀዉ፡፡

በዚህ መሃል ሌዊ ሌላ እንግዳ ደረሰ፡፡ ከተፈሪ ቪ8 ተፈሪ እና አቶ ጥላሁን ወረዱ። አሸናፊንም ስለትብብሩ አመሰገኑት፡፡ “ከአሁን በኋላ ግን የአርባምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ብሎኮች ግንባታ ከአንተ እጅ ወጥቶ ለአቶ አንጁሎ ይሰጣል ክፍያህም በእርሱ በኩል ይፈፀማል” የጥላሁን ማሳረጊያ ትዕዛዝ ነዉ፡፡
አሸናፊ ይጠጣ የነበረዉ ወይን ጋር የጥላሁን ንግግር ተዳምሮ በቆመበት አደረቀዉ፡፡ ቃል ሳይተነፍስ በዓይኑ ብቻ “ባለስልጣናቱን” ሸኛቸዉ፡፡

አቶ አንጁሎ አርሼ የአሸናፊ አርሼ ታላቅ ወንድም ናቸዉ፡፡ ያዉም የዘመኑ ሙሰኛ ኮንትራክተር፡፡ ቡሌ ሆራ ዩንቨርሲቲን ግጠዉ በልተዉ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ይታሰራሉ ሲባሉ ከሀገር ኮብልለዉ ወጡ፡፡ ጥላሁን ባለዉለታዉን አይረሳምና ስልጣኑን ተገን አድርጎ ከሰዉ ሀገር መለሰዉ፡፡ እንዳይከሰስም አደረገዉ፡፡

ሌላ ላክል፡፡ የዚህን “ክትራክተራዊያንን” ቤተሰብ ሌላ ሰሞንኛ ሌብነት፡፡ የአንጁሎ አርሼ ልጅ ቸሬ የሚሉት አለ፡፡ ጋሞ ዞን ላይ ምዕራብ አባያ ብርብር፤ ቁጫ ወረዳ ሰላም በር እንዲሁም ቦረዳ ወረዳ ዘፍኔ ከተሞች ላይ የመንገድ ዳር መብራት ያለ ጨረታ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ተሰጥቶት እየሰራ ነዉ፡፡
ስራ መስራቱ ባልከፋ፡፡ ነገር ግን ለሌላዉ የጋሞ ተወላጅ ተነፍጎ ህግ ተሸሮ ለራሳቸዉ ሌብነት ሲሉ ታዳጊዉን ቸሬን ነገ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

ማሳረጊያ፡- ከሰሞኑ አቶ ጥላሁን ስልጣኔን ማንም አይነካም ምርጫ ከፊት ለፊት ስላለ እያለ ይፎክራል፡፡ አባቴ ያንተ ስልጣን በክር ጫፍ ላይ ስለመድረሱ ዛሬም ዳግም ላስታወስህ? ደግሞ ምነዉ በ3 ወር ዉስጥ ተመለጥክ? እረ ስኳሬ መርፌም መጠቅጠቅ ጀመርክ አሉ? አሉ ነዉ እንግዲህ!! ያዉ በቀጣይ በሜርኩሪዉ በል በቁርጥ ዋጋ እያልክ በቀድሞዉ ክልል ስላደልከዉ ፕሮጀክትና ስለ ተዘዋዋሪ ፈንድ እመለስብሀለሁ፡፡

የቀበሌ ሚሊሻ የነበረዉን ሶፎኒያስን ፍትህ ቢሮ ሃላፊ/ ፀረ ሙስና ብለህ እንዳሻህ ስለጋለብከዉ ሰዉም እመለሳለሁ፡፡ ዳዊትን በሀልገዮ የመተካትህ ቁማርም በኮንሶ ምነኛ እንዳንፈራፈረህ ሰምተናል፡፡ ምነዉ ዳዊት ላይ የተወራጨኸዉን ያህል የሶፎኒያስ መኪና ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አጭቆ ተይዞ መስሚያዬ ድፍን ነዉ አልክሳ …… ይቀጥላል …. በተጨማሪ እንመለስበታለን። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጠና ታሟል አስቸኳይ ህክምና ያስፈልገዋል!!”

ማሳሰቢያ፦ እንደዚህ አይነት ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ WT ሚዲያ በደስታ ተቀብሎ ያስተናግዳል። በተለይም ሚዲያችን በሀገሪቱ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት በሚዲያ ይፋ እናደርጋለን። እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን!!