አንድ የጋሞ ተወላጅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራር “የክልሉ ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ የራሱን ማንነት በመደበቅ የዝርፊያ ቡድንና ጥቅሙ ባለበት ብቻ በማተኮር ሌሎችን እየበደሉና ህዝቡ ከመንግሥት እንዲነጠል እያደረጉ እንደሆነ አጋለጡ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአከባቢ እና ደን ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ አቶ ግዛቴ ግጄ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ጥላሁን ከበደን የራሱን ማንነት በመደበቅ ከስልጣን የመወገድ ስጋት ሊቀርፍላቸው ይችላል በሚል የራሱ ቡድንና ጥቅም ባለበት ከተማ ልማት ብቻ በማተኮር ሌሎች መዋቅሮችን እየበደሉ ነው በሚል” በጽኑ ገምግመዋል።
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ መድረክ ላይ ሲሆን፣ አቶ ግዛቴ ግጄ አቶ ጥላሁን ከበደ ጋሞ ሳይሆኑ አማራ መሆናቸውን በመግለጽ ስራቸው ኢ-ፍትሐዊ እንደሆነ በግልፅ መናገሩ መነጋገሪያ መሆኑን አንድ በስብሰባው የተገኙ ከፍተኛ አመራር ለWT ሚዲያ አስረድተዋል።
አቶ ግዛቴ ሁኔታውን ሲገልፁ “የአቶ ጥላሁን ከበደ ወልዴ አማራ መሆን የሚያሳፍር ነገር አይደለም፥ ነገር ግን የራሱን ማንነት በመደበቅ ከስልጣን የመወገድ ስጋት ሊቀርፍላቸው ይችላል በሚል አንድ የራሱ ቡድንና ጥቅም ባለበት ከተማ ልማት ብቻ ትኩረት በማድረግ ለሌሎች የክልሉ ሆኑ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ መዋቅሮችን መርሳትና ትኩረት አለመስጠት ኃላፊነት የጎደለውና ትልቅ ኃላፊነትን መዘንጋት ነው” ብለዋል።
አክለውም አቶ ግዛቴ በግምገማው ወቅት “አቶ ጥላሁን ጋሞ አለመሆኑ የታወቀ ነው ጋሞ አቃፊ ነው፣ አይሰርቅም፣ አድሎ አይሰራም እሱ ደግሞ ጋሞ አለመሆኑ እየፈጠረ ያለውን ከስልጣን የመወገድ ስጋት ይቀርፋል” በሚል በሌሎች የክልሉ አከባቢ መሰራት ያለበትን ልማት በጀት ስብሰባ ሁሉ ወደ አርባምንጭ እየወሰደ መሆኑ ይታወቃል።” ብሏል።
በተጨማሪም የአቶ ጥላሁን ከበደ ኢፍትሐዊ አሰራርና ሌሎች ዞኖች ከልማት እንዲገለሉ ከማድረግ ባሻገር በጋሞ ዞን በዛይሴ፣ ቁጫ፣ ካምባ፣ ጨንቻ እና ሌሎች ቦታዎች የህዝብ መሰረት ልማት ጥያቄ ተነፍገው በመንገድ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም የጤና ተቋማት እጦት፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጭምር እየተሰቃዩ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ከክልሉ የተውጣጡ ምሁራን ለWT ሚዲያ የሰጡት አስተያየት ይፋ ባደረገው ዘገባ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት የክልሉ ሀብት በአብዛኛው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ ልማት እንደተዘዋወረና በልማት ስም ከፍተኛ ገንዘብ በጥቂት አመራሮችና ግለሰቦች እጅ መግባቱን በመግለፅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአከባቢ እና ደን ጥበቃ ቢሮ ሀላፊና የጋሞ ተወላጅ ዶርዜ አቶ አቶ ግዛቴ ግጄ ሀሳብ ትክክለኛ ስለመሆኑ ያረጋግጣል።
አቶ ጥላሁን ከበደ በየስብሰባው ስለአንድነት ስለብልፅግና የሚናገረው ቢሆንም በተግባር ግን በአርባምንጭ ዙሪያ ተቀምጦ የተለያዩ ፍላጎት ላላቸው ግለሰቦች አላማ ለማሳካት ብቻ የሚሰራ፣ ይሄንን አላማ ለማሳካትም ከኢፍትሐዊ አሰራር ባሻገር በአከባቢው የሚገኙ ህዝቦችን የሚያባላ አጀንዳ መፈጠር እንደሆነም አቶ ግዛቴ በግምገማው በድፍረት አንስተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥላሁን ከበደን ባልተለመደ ሁኔታ በድፍረት ሁሉም የክልሉ አመራሮች በተገኙበት የገመገመው የክልሉ የአከባቢ እና ደን ጥበቃ ቢሮ ሀላፊና የአከባቢው ተወላጅ ( ጋሞ ተወላጅ ዶርዜ ) አቶ ግዛቴ ግጄ፤ “እውነትን በመገፈጤ የሚመጣውን ጫና አውቃለሁ፥ ነገር ግን የትኛውንም ውጤት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ” በሚል አቋሙን ገልጸዋል።

ምሁራኑ እንደሚሉት፣ ሌላው ይቅርና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ መዋቅሮች ለመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል በሚቸገርበት ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ላይ ከፍተኛ የመዋለ ንዋይ ፍሰት ታይቷል።
በተቃራኒው፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ፣ በዎላይታ እና በኮንሶ ዞኖች የልማት ፕሮጀክቶች ተከልክለዋል፣ የጨረታ ሂደቶች ተስተጓጉለዋል እንዲሁም ከሌሎች ብሔረሰቦች የተወጣጡ ኮንትራክተሮች ከስራ ታግደዋል ወይም ታስረዋል ሲሉ ለWT ሚዲያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
እንደምሁራኑ ገለፃ፦ የርዕሰ መስተዳድሩ ኢፍትሐዊ አሰራርና ሌሎች ዞኖች ከልማት እንዲገለሉ ከማድረግ ባሻገር በጋሞ ዞን በዛይሴ፣ ቁጫ፣ ካምባ፣ ጨንቻ እና ሌሎች ቦታዎች የህዝብ መሰረት ልማት ጥያቄ ተነፍገው በመንገድ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም የጤና ተቋማት እጦት፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጭምር እየተሰቃዩ እንደሆነ ገልጸዋል።
አቶ ጥላሁን ከበደ አርባምንጭ ብቻ ትኩረት ያደረገበትን ሁኔታ ሲገልፁ፦ በያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ ከፍተኛ ጥቅም ትስስር በመፍጠር በግንባታ ሰበብ ለግሉ ገንዘብ ለመመዝበር እንዲመቸው እና አርባምንጭ ከተማ ውስጥ የረጅም ጊዜ የጥቅም ወዳጅ የሆኑ ግለሰቦች ፍላጎት ለማሳካት እንደሆነ አስረድተዋል።
ይህንን የምዝበራ አላማ ለማሳካት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚጠቀሙት ታማኝ ተላላኪ አመራሮችን በመሾም፣ ያለጨረታ በምስጢር ላደራጀው ኮንትራክተሮች ፕሮጀክቶችን እንዲሰሩ በማድረግ፣ የገቢዎች ቢሮን በመጠቀም እንዲሁም የህዝብ ተቋም የሆነውን ጋሞ ልማት ማህበር እንደ ጭምብል ተጠቅመው እንደሆነ ምሁራን አክለው አብራርተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነዋሪዎች፣ በተለይ ወጣቶች፣ ለፍትህ እና እኩል ልማት መብታቸው እንዲታገሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በተለይም የፌደራል መንግስት በክልሉ እየተስተዋለ ያለውን ኢፍትሃዊነት፣ ብልሹ አሰራሮችና ሌብነት ህዝብን ከመንግሥት ወደመነጠል ደረጃ እየተሸጋገረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ተጠይቋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነዋሪ ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙና የዛ አካባቢ ተወላጆች በተለይ የክላስተር ከተሞች የዎላይታ፣ የጌዲኦ፣ የአሪ፣ የጎፋ፣ ኮንሶ፣ ጋርዱላ፣ ባስኬቶ፣ ኧሌን ጨምሮ ሌሎች ዞኖች የአቶ ጥላሁን ከበደ አደገኛ አካሄድ ድርጊት የውሸት ትርክት ማጋለጣቸውን እንዲትቀጥሉ ጥሪያችን ነው ብሏል።
ዛሬ ይሄንን ዜና እያጠናቀረን ባለንበት ወቅት WT ሚዲያ በየጊዜው ሀቅንና እውነተኛ መረጃ በመጠቀም እያጋለጠ የሚገኘውን ዘገባ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች እያደረጉ ስላሉት ብርቱ እንቅስቃሴ መቋቋም የተሳናቸው አንዳንድ የምዝበራ አላማ ለማሳካት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚጠቀሙት ታማኝ ተላላኪ አመራሮችና የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦች “በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ር/መስተዳድር በክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ላይ በWT Media & Nuso የተጀመረው የጥላቻ እና የሴራ ፖለቲካ እቃወማለሁ!” የሚል የድጋፍ ዘመቻ በማህበራዊ ሚዲያ መጀመራቸውን ተመልክተናል። በጉዳዩ ዙሪያ እንመለስበታለን!
ማሳሰቢያ፦ እንደዚህ አይነት ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ WT ሚዲያ በደስታ ተቀብሎ ያስተናግዳል። በተለይም ሚዲያችን በሀገሪቱ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት በሚዲያ ይፋ እናደርጋለን። እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን!!