received_1266158755051702

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደደሩን የማዳን የሚዲያ ክተት አዋጅ ታወጀ

በበርካታ ብልሽቶች ውስጥ የተዘፈቁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር ጥላሉን ከበደ እየጠነከረ የመጣሁን የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ የማጋለጥ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተከትሎ መረጃውን ለማድበስበስ የሚዲያ ክተት አዋጅ በዛሬው ዕለት በይፋ መታወጁ ተረጋግጧል።

WT ሚዲያ በየጊዜው ሀቅንና እውነተኛ መረጃ በመጠቀም እያጋለጠ የሚገኘውን ዘገባ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች እያደረጉ ስላሉት ብርቱ እንቅስቃሴ መቋቋም የተሳናቸው አንዳንድ የምዝበራ አላማ ለማሳካት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚጠቀሙት ታማኝ ተላላኪ አመራሮችና የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦች የር/መስተዳድሩን የክተት አዋጅ ተቀብለው የድጋፍ ዘመቻ በማህበራዊ ሚዲያ መጀመራቸውን ተመልክተናል።

በዚህም በርካታ የክልል የዞን ከፍተኛ አመራሮች የክተት አዋጁን በመቀላቀል በማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ መጀመራቸውን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

በርዕሰ መስተዳደሩ እየተስተዋሉ ያሉ ብልሽቶችንና አሰራርን ለመደበቅ ህዝቡን ወደ ጎን በመተው አመራሩ በክተት ጥሪ መሳተፋቸው እየወጡ ባሉ ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው ጽሁፎች በርካቶችን ትዝብት ውስጥ ክልሉን ማስገባታቸውን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያነጋገራቸው የጂንካ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቁሟል።

እንደ ፖለቲካ ተንታኙ ገለፃ ሚዲያዎች ለህዝብ እያደረሱ ያሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርና የሌሎች አመራሮች ብልሽት አጠናክሮ እንዲቀጥል በማሳሰብ አድናቆታቸውን ለህዝብ ጆሮ ለሆነው ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።

ምሁራኑ እንደሚሉት፦ የርዕሰ መስተዳድሩ ኢፍትሐዊ አሰራርና ሌሎች ዞኖች ከልማት እንዲገለሉ ከማድረግ ባሻገር በጋሞ ዞን በዛይሴ፣ ቁጫ፣ ካምባ፣ ጨንቻ እና ሌሎች ቦታዎች የህዝብ መሰረት ልማት ጥያቄ ተነፍገው በመንገድ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም የጤና ተቋማት እጦት፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጭምር እየተሰቃዩ እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ አርባምንጭ ብቻ ትኩረት ያደረገበትን ሁኔታ ሲገልፁ፦ በያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ ከፍተኛ ጥቅም ትስስር በመፍጠር በግንባታ ሰበብ ለግሉ ገንዘብ ለመመዝበር እንዲመቸው እና አርባምንጭ ከተማ ውስጥ የረጅም ጊዜ የጥቅም ወዳጅ የሆኑ ግለሰቦች ፍላጎት ለማሳካት እንደሆነ አስረድተዋል።

ይህንን የምዝበራ አላማ ለማሳካት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚጠቀሙት ታማኝ ተላላኪ አመራሮችን በመሾም፣ ያለጨረታ በምስጢር ላደራጀው ኮንትራክተሮች ፕሮጀክቶችን እንዲሰሩ በማድረግ፣ የገቢዎች ቢሮን በመጠቀም እንዲሁም የህዝብ ተቋም የሆነውን ጋሞ ልማት ማህበር እንደ ጭምብል ተጠቅመው እንደሆነ ምሁራን አክለው አብራርተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነዋሪዎች፣ በተለይ ወጣቶች፣ ለፍትህ እና እኩል ልማት መብታቸው እንዲታገሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በተለይም የፌደራል መንግስት በክልሉ እየተስተዋለ ያለውን ኢፍትሃዊነት፣ ብልሹ አሰራሮችና ሌብነት ህዝብን ከመንግሥት ወደመነጠል ደረጃ እየተሸጋገረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ተጠይቋል።

Ethiopia #southernethiopia