ያልተነገሩ ነገር ግን እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጆሮ የደረሱ የፕሬዘዳንቱ፣ የባለሀብቱና የጥቅም አጋሮቹ እስከ የአቡ ዳቢዉ ገዢ፤ የዩናይትድ ዓረብ ኢመሬትሱ ንጉስ መሃመድ ቢን ዛይድ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑትን ማጭበርበር ያካተተ አስገራሚ መረጃዎች – ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል
ገድለ ሌብነት ወኢያሱ ወሰን/Arbaminch/
ለቱሪዝም ኢንዱስትሪዉ ግዙፍ ዳና ያስቀመጠ ዘመናዊ ሪዞርት ዳዉሮ ዞን ላይ ተገነባ፡፡ የሃላላ ኬላ ሪዞርት፡፡ ሪዞርቱ እንደተመረቀ ወደ ስራ እንዲገባ ሲደረግ አገልግሎቱን የማስተዳደር ሃላፊነት በአቶ ጥላሁን ከበደ አማላጅነት ኢያሱ ወሰን በፓራዳይዝ ሪዞርት ባለቤትነት ስም ያስተዳድር ዘንድ ተሰጠዉ፡፡ አቶ ኢያሱ ይህን ትልቅ ሃላፊነት እና አደራ እንዲሁም ለበርካታ ትላልቅ ስራዎች የታጩበትን ዕድል በተራ ሌብነት አኮሰሰዉ፡፡
ሌብነቱ ወዲህ ነዉ፡፡ የጠቅላይ ሚንስትሩ የቅርብ ወዳጅም አጋርም ስለመሆናቸዉ የሚነገርላቸዉ የአቡ ዳቢዉ ገዢ፤ የዩናይትድ ዓረብ ኢመሬትሱ ንጉስ መሃመድ ቢን ዛይድ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አዲስ አበባ በእንግድነት ይመጣሉ፡፡ ጠቅላዩም አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ሃላላ ኬላ ሪዞርትን አይተዉ መንፈሳቸዉን ያድሱ ዘንድ ዳዉሮ ይልካሉ፡፡
የተከበሩ እንግዶቼ ናቸዉና ለሚያገኙት አገልግሎት ስባሪ ሳንቲም እንዳታስከፍሉ ሲሉም ለሪዞርቱ ባለአደራ አስተዳዳሪዎች ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሳስባሉ፡፡ የንጉሳዊያኑ ቤተሰቦች ቆይታቸዉን ጨርሰዉ ሲወጡ የ690 ሺህ ዶላር ክፍያ ይጠየቃሉ፡፡ ነገሩ ግራ ቢያጋባቸዉም ከፈሉ፡፡ አዲሳባ ሲመጡ ግን ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ሹክ አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ኢየሱ ወሰን ኪሱ የከተተዉን ዶላር በሰዓታት ልዩነት ለግለሰቦቹ አስመለሱ፡፡ ከሃላላ ኬላ ሪዞርትም አዉጥተዉ ጣሉት፡፡ ትልቁን ሃላላ ኬላ ሪዞርትን ከትንሹ ሰዉዬ እጅ ነጥቀዉ ለትልቁ አየር መንገድ ለስካይላይት ሪዞርት ሰጡት፡፡
ጠቅላዩ በኢያሱ የዘቀጠ ድርጊት ቢያዝኑም እንደ መሪ ሆደ ሰፊ ሆነዉ ትተዉታል፡፡ በርካታ የወንጀል ሴራ መረጃ እጃቸዉ ላይ ቢገባም አልፈዉታል፡፡ አሁን ግን ፈጦ የመጣዉን ብልግና እና ድፍረት በዝምታ የሚያልፉት አይሆንም፡፡
አርባምጭን የቱሪዝም ኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ በእርሳቸዉ ልዩ ክትትል እየተገነባ ያለዉ የቱሪዝም ኮንፈረንስ ማዕከል ግንባታ መሄጃ የአስፋልት መንገድ ግንባታ እስከአሁን አልተጀመረም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አቶ እያሱ ወሰን ካሳ ካልተከፈለኝ በቀር የሙዝ ማሳዬ ዘንድ አንድ ሰዉ እንዳይደርስ ሲል መዛቱ ነዉ፡፡ ልክ እንደርሱ ማሳ ያላቸዉ እነ ካይሮ ሆቴል ባለቤቶች ያለ ምንም ካሳ ይዞታቸዉን ሲለቁ እያሱ ወሰን ግን ማንም ከወሰኔ እንዳይጠጋ ብሎ ፕሮጀክቱ ተስተጓጉሏል፡፡
የሚገርመዉ ኢያሱ ከያዘዉ ማሳ ዉስጥ 120 ሄክታሩ በህግ ወጥ መንገድ በጉልበት የያዘዉ መሬት እንደሆነ ዞኑም፤ ከተማዉም ያዉቃል፡፡ ያዉ የጥላሁን የሌብነት ሽርክናዉን ተማምኖ ነዉ እንግዲህ የከተማዋን ልማት የሚያደናቅፈዉ፡፡
በአቶ እያሱ ወሰን ስም ያለዉ የፓራዳይዝ ሎጅን ጨምሮ /ኦሞቲክ ቢዝነስ ግሩፕ/ ስር ያሉ የጉዞ ወኪሎችም ሆኑ በግብርና ስራ እንዲሁም የማዕድን ተቋማቱ ግብር በአግባቡ የማይከፍሉና የዞኑ ገቢዎች ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ግብር ዕዳ እንዲከፍል ማስጠንቀቅያ ጭምር ስለመስጠቱ ብንሰማም ሰዉየዉ ግብር ከመክፈልና ሀገራዊ ግዴታዉን ከመወጣት ይልቅ አመራርን ከሃላፊነት አስነሳለሁ ሆኗል ፉከራዉ፡፡
ፓራዳይዝ ሎጅ ገብቶ የሚጎበኝ ማንኛዉም ሰዉ በተፈጥሮ የታደለዉን ግቢ እያደነቀ ወደ ከመጨረሻዎቹ የመኝታ ክፍሎች ሲደርስ አደገኛ ቦታ /Danger/ የሚል ምልክት ያገኛል፡፡ ማንም ከዚያ ቀይ መስመር አልፎ አይሄድም፡፡ የምልክቱ ሰቃይ አቶ ኢያሱ ሲሆን ያደረገበት ምክንያት አንዱ የባዕድ አምልኮ ስፍራዉ /ዘንዶ የሚቀልብበት/ ሲሆን ሌላኛዉ ዓላማዉ ደግሞ ሌላ ባለሃብት በአካባቢዉ ኢንቨስት እንዳያደርግ አጥሮና ከልሎ ለመያዝ የሚያደርገዉ ሙከራ ነዉ፡፡
በእርግጥ ሰዉየዉ ጉልበተኛ ነዉ፡፡ ለእርሱ ያላደሩ የዞን አስተዳዳሪዎችን ወንበር ነቅንቆ ገንድሷል፡፡ ኢሳያስ፤ አርኮ፤ አባይነህ ከእነዚህ መሃል ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይ አባይነህ አበራ እርሱማ ስለሆነ ነዉ ከህግ በላይ ነኝ የሚለዉ በሚል ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ ህግ ለማስከበር ያደረገዉ ጥረት በጥላሁን አልተወደደለትምና ከስልጣን እንዲነሳ ምክንያት ሆኖታል፡፡ ያለሙያው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አድርገው ቅጣት ጥሎበታል ጥልዬ!
ይህ ሁሉ ሌብነቱ እና ወንጀሉ እንዳይታወቅበት ከሰሞኑ ደግሞ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ጋር በመከረኛ የአፍሪካ ቦክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንትነት ስስ ስልጣን ስም የ4 መቶ ሺህ ብር ጓንትና ቲ-ሸርት ለኦሜድላ ክለብ ሰጥቶ መፋነን ፈልጓል፡፡ ጌታዬ ኮሚሽነር ጀነራሉ ሀገር የሚመራ የፍትህ እና የመርህ ሰዉ እንጂ አንተ እንደምታዉቃቸዉ ሸቀጦች አይደሉም አትድከም!! ከእርሳቸዉ ጋር ፎቶ ተነስቶ መፖሰት ከተጠያቂነት አያድንም የአባ ገዳ ልጅ ሀቀኛ ናቸዉ እርሳቸዉ፡፡
ቀድሞዉን ጠቅላይ ሚንስትሩ ቃሊቲ ያልሰደዱህ ወንጀል ስላልፈፀምክ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስም እንዳይጎድፍ ነዉ፡፡ ኢትዮጵያዊዉ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት በሌብነት ታሰሩ መባሉን ስለማይፈልጉ፡፡ የቀን ጉዳይ ነዉ እንጂ ሰማይ ቁና ሆኖ መደፋቱ አይቀርም Wait……..
የእሺ ፕሮዳክሽን ዶኩመንታሪ የት ደረሰች አቶ ኢያሱ ? የጋሞ ቴሌቪዥንስ ደግሞ 18 ሚሊየን ብር በ15 ቀን እምሽክ
ጥሌም ሰሞኑን ፊት የነሳዉን አደም ፋራህን አማልደኝ ሲል ከሙስጠፌ ተለጥፏል፡፡ ሲያጥላላዉ ከነበረዉ የሲዳማ ህዝብ ፊትም ደስኩሯል፡፡ በደስታ ሌዳሞ በኩል ኦቦ ሽመልስን አግኝቶ ብላ ብለ ብላ ለማያዉቁሽ ታጠኝ አለ ሰዉየዉ፡፡ ….. መረጃው አላለቀም ደጋግመው እያነበቡ ይቆዩ ቀጣዩ ክፍል እስኪደርስ …..
ማሳሰቢያ፦ WT Media በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን። ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ WT ሚዲያ በደስታ ተቀብሎ ያስተናግዳል። በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media