1000071258

አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰበሰበው ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ለተጎጂዎች ሳይደርስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች መመዝበሩ ተረጋገጠ።

በጎፋ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ቀይመስቀል ቤትና አስፈላጊ ነገሮቹን አሟልቶ ገንብቶ ካሰረከበ ከተለያዩ አካላት የተሰበሰበው 600 ሚሊዮንን ከልሉ ወደየት ወሰደ ? የሚለው አሁንም እንቆቅልሽ ሆኖ መቀጠሉም ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር በክልሉ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት እና ናዳ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ያስገነባቸውን 296 የመኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎት በማጠናቀቅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ማስረከቡን ኢቲቪ ዘግቧል።

በአሳዛኝ ክስተት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡትን፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለማገዝና ለማማቋቋም ተብሎ ከሀገር ውስጥ እስክ የውጭ ሀገራት እንዲሁም ግለሰቦች ከተለያዩ ቦታዎች ከ600 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ የተሰበሰበ ቢሆንም ገንዘቡ ለተጎጂዎች ሳይደርስ በክልሉና በአከባቢው ባለስልጣናት መሰወሩን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው ተጨባጭ መረጃ ያመለክታል።

እንደመረጃው ከሆነ በዚህ ሙስና ቅሌት በክልሉ የማዕድን ሀብት ከመስረቅ ጋር ስማቸው በተደጋጋሚ በመነሳት የሚታወቁት አቶ አክሊሉ አዳኝ፣ የክልሉ አደጋ ስራ አመራር ኮሚኒዩኬሽን አቶ ጋንታ ጋምኣ እና በዋናነት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የተጎጂዎችን ሀብት በማሸሽ ይጠቀሳሉ።

ቀይመስቀል እና ሌሎች በጎ ድርጅቶች ከረዷቸው ውጪ እነኚህ በመሬት ናዳ የተፈናቀሉ ወገኖች አሁንም ከ200 በላይ አባወራዎች በላስትክ በቶች በተጠለሉበት ምግብ ውሀ በለለት በራሀብና በችግር እየተሰቃዩ ሲሆን ከተጎዎቹ የጉልበት ስራ መስራት የሚችሉት ወደ ሳውላ ከተማና ወደ አጎራባች ወረዳዎች መሰደዳቸውን የመረጃ ምንጭ ጠቁመዋል።

“በአደጋው ሰዓት ዓለም ሁሉ ከጎናችን ነበር፥ ተጎጅዎችን መልሶ ለማቋቋምም በጥሬ ገንዘብ ብዙ ሚሊዮን ብሮች እና በቁሳቁስና በዓይነትም ለመገመት የሚያዳግት መጠን ያለው ሀብት ተሰብስቧል፤ በስተመጨረሻም ለተጎጅዎች የሚሰሩ 200 መጠለያዎች በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተከፋፍለው እንደተሰጡና በዋናነት በመዋቅሮቹ እየተገነቡ ነው” ብለዋል።

“በአጠቃላይ አሁን ቀይመስቀል ከደገፋቸው ወገኖች ባሻገር ይህንን ያህል ሰው ሜዳ ላይ ከተጣለ፤ የተሰሩ ቤቶችም የእንጨት ቤትና በአግባቡ ጭቃ እንኳን ያልተመረጉ ከሆነ፤ አከባቢው ንፁህ የመጠጥ ወሃና መብራት እንኳን ያላገኘ ከሆነ፤ ትምርት ቤት ተብሎ የተሰራው ዳስ እንጨቶች ብቻ የቆሙበትና በቂ የተማሪ ወንበር እንኳን የለላቸው ከሆኑ፤ የተሰበሰበው ገንዘብና ንብረት የት እንደገባ በአፋጣኝ ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት” በሚልም ጉዳዩን በቅርበት የተከታተለና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

አመራሩ አክለውም “ገንዘቡ ሲሰበሰብ በአንድ ቋት መሆን ሲገባው ክልሉ ለላ አካውንት፣ ዞኑ ሌላ አካውንት፣ ወረዳውም ለተወሰኑ ቀናቶች የራሱን አካውንት ከፍቶ በተለያዬ አድራሻ የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደገባ መጣራት አለበት፤ ሌብነትና ዘረፋ ውስጥ የገቡ አመራሮች ካሉም በአፋጣኝ ተጣርቶ በህግ ሊጠየቁና ውጤቱ ለህዝብም ይፋ መደረግ አለበት፥ ከህዝብ ለቅሶ ሳቅ አይዘረፍም!!! ይህ የዘመናችን ነውረኛ ተግባር ነው!! በጎፋዎችም ማሾ!! ማሾ!!! ይባላል” ብለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Gofa