በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር አመትን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የፈፀመው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ ከመቅጠሩ አስቀድሞ የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ እና አማካዩ በረከት ወልዴ ከጋቶች ፓኖም ቀጥሎ ፈረሰኞቹን ተቀላቅለዋል፡፡
ከዎላይታ ድቻ የታዳጊ ቡድን በ2008 ከተገኘ በኃላ በወጥነት ለስድስት ዓመታት በዋናው ቡድን መጫወት የቻለው የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ እና በተመሳሳይ እንደ ቸርነት ሁሉ ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በጦና ንቦቹ መለያ የደመቀው የተከላካይ አማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ በረከት ወልዴም ለሁለት ዓመት በይፋ ፈረሰኞቹን ተቀላቅለዋል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 08/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
