የ “እንቃወማለን” ጭምብል ሲወልቅ-“ከ|ደኢህዴን ቤት እስከ ብልፅግና ድረስ በታማኝነት የዘለቀው ምስጢራዊ የሌብነት ሰንሰለት” – ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል
ዓለሟን የምትቀጨዉ አለምነሽ ማን ናት? ገረሴ ነዉ ትዉልድ አከባቢዋ፡፡ ያዉ ጋሞ ሳትሆን በጋሞ ስም ከሚነግዱ ባለጊዜዎችም ተርታ ትሰለፋለች፡፡ ለባለስልጣናት ደግሞ ባለዉለታ ናት በብዙ ፈርጅ፡፡ በተለይ ለጥላሁን “ሟች ናት “በምንም”፡፡ “ርዕሰ መስተዳሩ” ዛሬም በኢ-ሞራላዊ ድርጊቱ ክልሉን ሲያምስና የአንድ ዞን አስተዳዳሪ ይመስል እዚያዉ ሲንከባለል የሚፎክርበት የክልሉ ገቢ የሚዘወረዉ በዚህችዉ እንስት የሚመራዉ ቢሮ ነዉ፡፡
እዚህ ግባ የሚባል የኋላ ታሪክ የላትም፡፡ አይደለም የክልል ቢሮ ያዉም የክልሉን ገቢ ሴክተር ለመምራት የሚያስችል ኣቅም ሊኖራት ቀርቶ በዚህ ዕድሜዋ የረባ ተቋም ላይ አሻራ የላትም፡፡ መንገደኛ ተሿሚ ናት ይላሉ ብዙዎቹ፡፡ “ከእዉቀት ነፃ ሲሉም ያንቆለጳጵሷታል” የራሷ የቢሮ ሰራተኞች፡፡ እርሷም አታሳፍራቸዉም፡፡ ቢሮ ባለመግባት፤ በየአበል ቦታ በመዞር፤ ከፊት አመራሮች ጋር በማሽቃበጥ ታኮራቸዋለች፡፡ ታዲያ ይህቺ “ጉምቱ ባለዕዉቀት ምሁር” እንዴት የአዲሱ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ተደርገዉ ተሰየሙ ነዉ ዋናዉ ነጥብ፡፡
ወ/ሮ አለምነሽ አቶ ጥላሁን በቀድሞዉ ክልል የፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ እያለ ለዝርፊያዉ ይመቸዉ ዘንድ የፅ/ ቤቱ ፋይናንስ ሃላፊ ከዚያም የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ሰብሳቢ አድርጎ እንዳሻዉ ሊጋልባት ስልጣን አከናነባት፡፡

እቅዱ ተሳክቶለትም እንደፈለገዉ የፓርቲዉን ሃብት ተቀራመተዉ ዕድሜ ለአለምነሽ፡፡ መሃል ላይ ግን ዱብ ዕዳ መጣ፡፡ ጥላሁንን ጨምሮ የቀድሞዉ ክልል ቱባ አመራሮች ከሃገር ሳይወጡ አዉሮፓን እንደጎበኙ አስመስለዉ ከመከረኛዉ አባሉ የተሰበሰበ ሃብት የዘረፉበት ሰነድ የፓርቲዉ ዋና ፅ/ ቤት በኦዲት ሲያረጋግጥ አለምዬ ተረበሸች፡፡ እነርሱ አይጠየቁ ስህተቱ የኔ ነዉ ብላ እጇን አሳልፋ እሰከመስጠት ቆረጠች፡፡ ለወንድም አለሞቿ እና እህት አለሞቿ ፍቅር አስከመቃብር አለች፡፡
እላይ ታች ብላ ሰነድ ፈብርካና በሌላ ቱባ የብር እስር ጉቦ ጥላሁንን ጨምሮ ሌሎች ሌቦችን ከእስር ታደገች፡፡ ለዚህ ቃላት ለማይገልፁት ትጋቷ፤ ወደር ለማይገኝላለት ጀብዷ ቢሮ ሃላፊ መሆን ቢያንስባት እንጂ አይበዛባትም በሚል አቶ ጥላሁን ከጎኑ ሸጉጧት ይዞራል፡፡ እርሷም ዉለታዉን ሳትታክት ትመልስለታለች፡፡ ታማኝ ታዛዥ፤ ትጉህ ባለሟል፤ ብርቱ ተሟጋች ጠበቃዉ ሆናለች፡፡ ችግሩ ግን የጥላሁን ጀንበር ያዘቀዘቀች ዕለት የዓለምነሽ ፀሐይ መጥለቋ ነዉ እንጂ፡፡
የጥላሁን እና የዓለምነሽ ወዳጅነት ከዚህ ጥብቅ የጥቅም ትስስርም ሻገር ይላል፡፡ አለምነሽ የጥላሁን የቢዝነስ ፓርትነር የሆነዉ የፓራዳዝ ሎጅ ባለቤት የአቶ ኢያሱ ወሰን እህት ናት የሚሉኝ የመረጃ ምንጮቼ አብዛኛዉ ሰዉ በአባት ስም አለመመሳሰል እንደሚሸወድ ነዉ የነገሩኝ፡፡ አለምነሽ የኢያሱ ወሰን ካዝና ናት፡፡ ለዚህ ነዉ ቢሮዋ ከከተማ ዉጪ ያዉም ገና በጅምር ላይ ላለ ህንፃ በየወሩ 600 ሺህ ብር የቢሮ ኪራይ ከኢያሱ ወሰን ተከራይታ የክልሉን ሀብት ከወንድሟ የባንክ አካዉንት የምትሞጅረዉ፡፡
ክልሉ ላይ ያሉ የጋሞ አመራሮች በእርግጥ በዚህ ትብትብ ተክነዋል፡፡ ቀድሞ የጥላሁን ሸሪክ አሁን ግን ጥላሁን ላይ በየቦታዉ ተቋዉሞ ሲበረታ የእርሱን ቦታ ተካለሁ ብሎ ያደፈጠዉ ብርሃኑ ዘዉዴ የቅርብ ወዳጁ ከሆነዉና የዘረፈዉን ሃብቱን ከሚሸሽግለት አርባ ምንጭ ላይ የለስላሳ መጠጦች ወኪል አከፋፋይ ከሆነዉ ግለሰብ ነዉ በወር 650 ሺህ ብር ቢሮ የተከራየዉ፡፡
በዚህ ብቻም አላበቃም፡፡ አዚዉ ቢሮዉ አስፓልቱን ተሻግሮ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር ባለስልጣን የተከራየዉ ባለ አንድ ፎቅ ህንፃም የትላሁን ከበደ ስለመሆኑ ላጣራ የሚል አካል ከመጣ ለመረጃ ዝግጁ ነን፡፡
የክልሉ ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ቢሮ 10 ባለሙያ ብቻ ይዞ በፊት ከነበረበት ከአርባምንጭ ፖሊ ሳተላይት ኮሌጅ ግቢ ወጥቶ የቀድሞ የ40 ስፕሪንግ ሆቴል ባለቤት የወዲ ሚስት ከነበረችዉና አሁን ከተፋታችዉ ሮሚ ፔኒሲዮን እንዲገባ ተደርጎ በየወሩ 600 ሺህ ብር ይቀፈቅፋል፡፡ የቢሮዉ ሃላፊ አቶ አብዮት በተደጋጋሚ በዚህ ጉዳይ ከጥላሁን ጋር ስለመጋጨቱም ይወራል፡፡
ሮሚ እና ጥሌ በብዙ ይታማሉ፡፡ ስለ ግል ጉዳያቸዉ አያገባንም፡፡ ግን “ሮሚዬ” የጥላሁን ሃብት ማሸሻ ድብቅ “ህቡዕ” ናት፡፡ ሴቻ ላይ ዴሪክ ፊት ለፊት ከዉበቴ ሆቴል አጠገብ በነበረ ሰፊ ቦታ ላይ የተጀመረዉ ፕሮጀክት ግንባታ ስሙ “የሮሚዬ” ይሁን እንጂ ባለቤቶቹ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥላሁን እና ጂንካ ተመድቦ ከሳምንት እስከ ሳምንት የቢራ አንገት ከጧት አስከ ማታ አንቆ አርባምንጭ ላይ የሚሰክረዉ የቀድሞ ከንቲባ፤ የጋሞ ዞን የመንግስት ተጠሪ የአሁኑ የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ “ሓላፊ” የአቶ ሰብስቤ ቡናቤ/ በነገራችን ላይ ድፍረቱነን፤ ድድብናዉን በጣም እወድለታለሁ/ ስለመሆኑ አርባምንጮች አብጠርጥረን እናዉቃለን፡፡
ስናጠቃልል ፍግም ሊል የተቃረበዉ ጥላሁን ክልሉን ለመጋት እንጂ የክልሉ መሪ እንዳልሆነ ክቡር ጠቅላ ሚኒስትር ዐቢይም፤ አደም ፋራህም እናንተም እኔም እናዉቃለን፡፡ የቀን ጉዳይ ሆኖብን እንጂ ብዙ ጉድ ይወጣል፡፡ የዛሬ ዝምታ አይቀጥልም፡፡ ፖለቲካ ጊዜና ሁናቴን ስለሚያጤን እንጂ፡፡ መረጃው አላለቀም ደጋግመው እያነበቡ ይቆዩ ቀጣዩ ክፍል እስኪደርስ …..
ማሳሰቢያ፦ WT Media በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን። ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ WT ሚዲያ በደስታ ተቀብሎ ያስተናግዳል። በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media