1000071484

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በሚያነሱ ዜጎች ላይ እስር፣ ግድያ፣ የንብረት ዝርፊያ እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሙስና እና በደል የሚያጋልጡ ግለሰቦች ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ እንደሆነ ተመላክቷል።

ከቀረበው መረጃ እንደተገኘው፣ የከምባ ተወላጅ የሆነው አቶ ሀብታሙ ሞገስ የዚህ በደል ሰለባ ከሆኑ ግለሰቦች አንዱ ናቸው። አቶ ሞገስ በፍርድ ቤት በዋስትና ቢለቀቁም፣ ተጨማሪ ክስ ተመስርቶባቸው አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ እና ሕክምና እንደተከለከሉ ተነግሯል።

ከጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች WT Media ባገኘው መረጃ መሠረት፣ በፖሊስ እና በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት እየተፈጸሙ ናቸው የተባሉት ወንጀሎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

👉 ዜጎችን ያለሕጋዊ የእስር ማዘዣ ማሰር እና ማሰቃየት።

👉 የዜጎችን ስልክ እና ንብረት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መውሰድ፣ እንዲሁም በሌሊት ቤት በመግባት የንብረት ዘረፋ መፈጸም።

👉 የታሰሩ ግለሰቦች የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኙ መከልከል ተመልክቷል።

👉 አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዘይሴ ቀበሌዎች ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ንጹሐን ዜጎች እና ሕፃናት ጭምር በፖሊስ እየተገደሉ መሆኑ ተዘግቧል።

👉 በምዕራብ አባያ ወረዳ፣ አርባምንጭ ዙሪያ በ”ኮሪደር ልማት” ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ ዜጎች ካሳ ሳያገኙ ንብረታቸው እንደወደመ እና ፍትሕ እንዳጡ ተገልጿል።

ለአብነትም ለፍትህ፣ ለሰብዓዊ መብት፣ ለሕግ የበላይነት በማህበራዊ ሚዲያ የተገለውን ግለሰብ ከሚኖርበት ከምባ ከተማ በጋሞ ዞን ፖሊስ በግፍ ተይዞ በአርባምንጭ ከተማ ሼቻ ፖሊስ ጣቢያ ሕክምና ተከልክሎ እንዲሰቃይ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ቆጎታ ወረዳ መልካም አስተዳደር ጥያቄ ያነሱ ግለሰቦች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቀበሌ ለቀናት ታስረዉ እየተሰቃዩ ይገኛሉ ተብሏል።

ዳራማሎ ወረዳ ምንም ያልታጠቁ የለጴ ቀበሌ ንጹሃንን በግፍ የገደሉ ፖሊሶች ላይ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ምስክርነት የሰጡ ግለሰቦች ቤት ፖሊስ በዉድቅት ሌሊት በመግባት ንብረት ዘረፋ፣ የመግደል ሙከራ እና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጸሞ ፍትህ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ቦረዳ ወረዳ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ኢንቨስትመንት ዉስጥ በባለስልጣናት የሚፈጸሙ ሙስና ወንጀሎች እየተቃወሙ የሚገኙ ዜጎች ለከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት፣ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት እና የመግደል ሙከራ ሰለባ መሆኑ ተገልጿል።

ቁጫ አልፋ ወረዳ መንገድ ልማት እጦት የመልካም አስተዳደርና ልማት ጥያቄ ያነሱ ዜጎችን የጋሞ ዞን ፖሊስ እያሳደዳቸዉ ይገኛል ተብሏል።

አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዘይሴ ቀበሌዎች ንጹሃንን ህጻናት ጭምር ፖሊስ እየገደለና ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንደሚገኝም ተነግሯል።

በምዕራብ አባያ ወረዳ በኮሪደር ልማት በሚል ምክንያት ከወጣትነት እስከ ሽምግልና ገንብተዉ ሀብት አፍርተዉ የሚኖሩ ዜጎች ያለ ምንም ካሳ ንብረታቸው በአስፈፃሚው አካላት ወድሞባቸዉ ፍትህ አጥተዉ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ቦንኬ ወረዳ እና ጋጮ ባባ ወረዳ ከአርባምንጭ ወደ ቦንኬ የሚወስድ የመንገድ ችግር በመኖሩ እሮሮ የሚያሰሙ ዜጎች በአስፈጻሚው አካላት ማስፈራሪያ ፣ ዛቻ እና ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነም ተገልጿል።

እነኚህ ለምሳሌ የተጠቀሱት በፖሊስና አስፈጻሚው የመንግስት አካል በጋሞ ዞን በዜጎች ላይ እየፈጸሟቸዉ የሚገኙት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ጥቂት ማሳያዎች ናቸዉ እንጂ ድምጻቸዉ ታፍኖ በየአካባቢው በስቃይ ዉስጥ የሚገኙ ዜጎች በርካቶች እንደሆነ ተነግሯል።

በተለይ በጋሞ ዞን እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ላይ በማህበራዊ ሚዲያ በተደረጉ የወንጀል ጥቆማዎች ያላስተባበሉ ሁሉ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ የማሰር፣ የማሳደድ እና የማሰቃየት እኩይ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ተጠናክረው መቀጠላቸዉ ተገልጿል።

በአጠቃላይ በጋሞ ዞን ከከምባ ወረዳ፣ ቆጎታ ወረዳ፣ ቦረዳ ወረዳ፣ ምዕራብ አባያ ወረዳ፣ ዲታ ወረዳ፣ ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ፣ ቦንኬ ወረዳ፣ ጋጮ ባባ ወረዳ፣ ገረሰ ወረዳ፣ ቁጫ አልፋ ወረዳ፣ ሰላምበር እና ሌሎች ቦታዎች ላይም የሰብአዊ መብት ጥሰት በብዛት እየተስተዋለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ምሁራን እንደገለጹት፣ አቶ ጥላሁን አርባምንጭ ከተማ ላይ ብቻ በማተኮር በግንባታ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ገንዘብ እንደሚመዘብሩ ተገልጿል።

ይህም በዞኑ ውስጥ ያሉ ሌሎች አካባቢዎች ከልማት እንዲገለሉ አድርጓል ተብሏል።

ይህንን የምዝበራ ዓላማ ለማሳካትም ታማኝ የሚሏቸውን አመራሮች በመሾም፣ ፕሮጀክቶችን ያለጨረታ በመስጠት እና የጋሞ ልማት ማኅበርን እንደ ሽፋን በመጠቀም እንደሚንቀሳቀሱ ተነግሯል።

WT ሚዲያ በየጊዜው ሀቅንና እውነተኛ መረጃ በመጠቀም እያጋለጠ የሚገኘውን ዘገባ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች እያደረጉ ስላሉት ብርቱ እንቅስቃሴ መቋቋም የተሳናቸው አንዳንድ የምዝበራ አላማ ለማሳካት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚጠቀሙት ታማኝ ተላላኪ አመራሮችና የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦች የርዕሰ መስተዳድሩ የክተት አዋጅ ከክልሉ፣ ከየዞኑ ከፍተኛ አመራሮችም የድጋፍ ዘመቻ በመቀበል በማህበራዊ ሚዲያ መጀመራቸውን ተመልክተን መዘገባችን ይታወሳል።

በርዕሰ መስተዳደሩ እየተስተዋሉ ያሉ ብልሽቶችንና አሰራርን ለመደበቅ ህዝቡን ወደ ጎን በመተው አመራሩ በክተት ጥሪ መሳተፋቸው እየወጡ ባሉ ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው ጽሁፎች በርካቶችን ትዝብት ውስጥ ክልሉን ማስገባታቸውን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያነጋገራቸው የጂንካ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቁመው ነበር።

እንደ ፖለቲካ ተንታኙ ገለፃ ሚዲያዎች ለህዝብ እያደረሱ ያሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርና የሌሎች አመራሮች ብልሽት አጠናክሮ እንዲቀጥል በማሳሰብ አድናቆታቸውን ለህዝብ ጆሮ ለሆነው ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ( WT MEDIA ) ገልጿል።

ምሁራኑ እንደሚሉት፦ የርዕሰ መስተዳድሩ ኢፍትሐዊ አሰራርና ሌሎች ዞኖች ከልማት እንዲገለሉ ከማድረግ ባሻገር በጋሞ ዞን በዛይሴ፣ ቁጫ፣ ካምባ፣ ጨንቻ እና ሌሎች ቦታዎች የህዝብ መሰረት ልማት ጥያቄ ተነፍገው በመንገድ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም የጤና ተቋማት እጦት፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጭምር እየተሰቃዩ እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ አርባምንጭ ብቻ ትኩረት ያደረገበትን ሁኔታ ሲገልፁ፦ በያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ ከፍተኛ ጥቅም ትስስር በመፍጠር በግንባታ ሰበብ ለግሉ ገንዘብ ለመመዝበር እንዲመቸው እና አርባምንጭ ከተማ ውስጥ የረጅም ጊዜ የጥቅም ወዳጅ የሆኑ ግለሰቦች ፍላጎት ለማሳካት እንደሆነ አስረድተዋል።

ይህንን የምዝበራ አላማ ለማሳካት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚጠቀሙት ታማኝ ተላላኪ አመራሮችን በመሾም፣ ያለጨረታ በምስጢር ላደራጀው ኮንትራክተሮች ፕሮጀክቶችን እንዲሰሩ በማድረግ፣ የገቢዎች ቢሮን በመጠቀም እንዲሁም የህዝብ ተቋም የሆነውን ጋሞ ልማት ማህበር እንደ ጭምብል ተጠቅመው እንደሆነ ምሁራን አክለው አብራርተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነዋሪዎች፣ በተለይ ወጣቶች፣ ለፍትህ እና እኩል ልማት መብታቸው እንዲታገሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በተለይም የፌደራል መንግስት በክልሉ እየተስተዋለ ያለውን ኢፍትሃዊነት፣ ብልሹ አሰራሮችና ሌብነት ህዝብን ከመንግሥት ወደመነጠል ደረጃ እየተሸጋገረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ተጠይቋል።

ይሄንን ዘገባ WT MEDIA እያጠናቀረ ባለበት ወቅት ከትናንት ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በሚያነሱ ዜጎች ላይ እስር፣ ግድያ፣ የንብረት ዝርፊያ እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ስለመሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዝርዝር እንመለስበታለን!!

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን። ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ WT MEDIA በደስታ ተቀብሎ ያስተናግዳል። በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media