
የዎላይታ ተወላጆችን ዓላማ ለማስፈንና መብቶቻቸውን ለማስከበር ታስቦ የተቋቋመው የወላይታ ዓለምአቀፍ ጥምረት (WoGA) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሙሉ እውቅናና ፈቃድ አግኝቶ በይፋ መመስረቱ ተገልጿል።
ድርጅቱ ይህንን መረጃ ለ WT Media በላከው መግለጫ አስታውቋል።
WoGA በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩና ለዎላይታ ሕዝብ ዕድገትና መብት በሚቆረቆሩ ባለሙያዎች (Elite group) የተመሰረተ ነው ተብሏል።
ዋና ዓላማውም በዎላይታ ሕዝብ ላይ የሚደርሱ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኢፍትሃዊነቶችን እንዲሁም በደሎችን መታገል፣ መብትን ማስከበር እና ለሚመለከታቸው አካላት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማቅረብ ነው።

ጥምረቱ ይህንን ዓላማ ለመደገፍና በተቋሙ ስር ለመንቀሳቀስ ለሚፈልጉ በሰሜን አሜሪካ ለሚኖሩ ትውልደ ዎላይታዊያን በሮቹ ክፍት እንደሆኑ አስታውቋል።
ይህ ጥሪ የዎላይታን ሕዝብ ጉዳይ በጋራ ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የWoGA መመስረት ለዎላይታ ሕዝብ መብት መከበርና ሁለንተናዊ እድገት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳልም ተብሏል።