1000072251

ቡርጂና ኮንሶ ዞኖችን የሚያስተሳስረው መንገድ ግንባታ በተመለከተ የተሰጠው ሀሰተኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ቁጣ ቀስቅሷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ በክልሉ እየተጎተቱ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ ለገጽታ ግንባታ ተብሎ በሁሉም ሥራ አስፈጻሚ እየተሰጡ ባሉ ዘገባዎች ላይ የሰጡት ማብራሪያ በርካቶችን አስቆጥቷል።

በተለይም በቡርጂና ኮንሶ ዞኖችን ምንም አይነት የፀጥታ ችግር የሌለበትን የጸጥታ ችግር አለ ብለው ለሚዲያዎች የሰጡት ማብራሪያ ሠላማዊ ቀጠናን ግጭት እንዲቀሰቅስ የሚያገፋፋ እንደሆነና ከአንድ ከፍተኛ አመራር የማይጠበቅ መሆኑን የመረጃ ምንጫችን አስረዷል።

በሌላ በኩል እንደዚህ አይነት ሀሰተኛ መረጃዎች በአመራሮቹ ደረጃ ሲሰጥ ወደ አከባቢው እንቨስትመንት የሚመጡ ባለሀብቶች ሆነ የግንባታ ተቋራጮች የፀጥታ ስጋት አለ በሚል እንዳይመጣ የሚያደርግ አደገኛ ነገር ስለሆነ በአስቸኳይ ይቅርታ ህዝብን እንዲጠይቅ አሳስበዋል።

በርካታ በፌዴራልና በክልል መንግስት በቢሊዮን የሚከናወኑ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንዲሰሩ የሚመደቡት በጀቶች በግለሰቦች እንደምዘረፉና ከዚህ ለመሸሽ የገጽታ ግንባታና በሚል በዝናብ ወቅት ማሽነሮችን አሰልፎ ፎቶ በመነሳት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ መጠመዳቸው ከተቋሙ ስማቸው እንዳይጠቀሱ የፈለጉትን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የዘወትር ተከታያችን መረጃውን አጋርቷል።

በቀጣይ በቢሮ የተጋነኑ የውሸት ሪፖርቶችና የአመራሩ የእርስበርስ በፕሮጀክት ገንዘቦች ላይ የሚሰሩ ዝርፊያዎች ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ዝርዝር የሚያቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን።