1000072267

“ራሱ ዳኛ ራሱ ቀማኛ” የጎፋ ፍርድቤት ውሎ ማስታወሻ – ከሳሽ የሆነው አመራር የራሱን ወንድም ዳኛ አድርገው ባለሀብቱን እንዴት እያሰቃየ ነው?

ከሶስት ቀን በፊት የተካሄደው ችሎቱ ባለሶስት ዳኛ ሆኖ ውሏል፣ በመሀል ዳኝነት የመራው ደግሞ የአክሊሉ አዳኝ ወንድም የሆነው ዳኛ አብራሃም አዳኝ ነው። የምርምራ መዝገብ ላይ ቤተሰብ ከሳሽን ወክለው በችሎት መቆም እና መከራከር የሚገባው መርማሪ ፖሊስ ቢሆንም በችሎቱ መርማሪ ፖሊስ ከመገኘት በስተቀር መዝገቡን ይዘው ስከራከር የነበረው የዎላይታ ተወላጅ የሆኑ የሃሰት ተከሳሾች የሀሰት ክስ በማደራጀት እንግልት እንዲያደርስ ከርዕሰ መስተዳድሩ ተልዕኮ የተቀበለው ዐቃቤ ኦሮቃ ሆኖ ውሏል።

ዳኞችን በኢፍትሃዊነት ከላይ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ በመቀበል በችሎት መወከል የሌለበትን ዐቃቤ ህግ በተከላካይ ጠበቆች በተደጋጋሚ አስተያየት እንዳይሰጥ በተቃውሞ ቢጠየቅም በዝምታ በማለፍ የተከላካይ ጠበቆች የመልስ መልስ እንዳይሰጡ በማድረግ ፍትህ እና የፍትህ ስርዓቱን በአፈፃፀሙ ደፍተውታል። የዚህን ተግባር በበላይነት የመራው የከሳሽ የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኤነርጂ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አክሊሉ አዳኝ ወንድም ዳኛ አብራሃም አዳኝ ናቸው።

ችሎቱ በግልጽ የዳኝነት ክፍተት የነበረው ሲሆን ዐቃቤ ህጉ ፖሊስ መርማሪ፣ ዳኛም ሆኖ እርሱ አስተያየት ሲሰጥ ተከላካይ ጠበቆች አስተያየት እንዳይሰጡና እንዳይከራከሩ ሊያደርግ እና ዳኞችን አጋፋሪ አድርገው እነርሱ ስዳኙ የዋሉበት በክልሉ ፍትህ የሌለበት መሆኑን በግልጽ ማሳያ ሆኖ ውሏል።

በአጠቃላይ በሀሰት የተወነጀለዉ እንጂነር ብራሀነመስቀል የማዕድን ፈቃድ ጋር በተያያዘ እና በፌደራል ፍርድቤት እየታየ ባለ ጉዳይ ሲሆን ግልጽ በፌዴራል ፍርድቤት በፍትሃብሔር ችሎት እየታየ የሚገኝ ጉዳይ፣ ጉዳዩን ምንም ግንኙነት በሌለው ሁኔታ የሙስና ወንጀል ነው በማለት ሲሆን ይህንን የሀሰት ለማስፈጸም ከህግ አግባብ ውጪ ለከሳሾች ማጭበርበር እና ፍትህን ለመቅበር ወደሚመቻቸው ወስደው በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ።

ከሳሽ አክሊሉ አዳኝ የትውልድ አካባቢ ጎፋ ወስዶ በመክሰስ እና በዳኝነትም ወንድማቸውን አቶ አብራሃም አዳኝን ዳኛ በማድረግ እራሱ ዳኛ ራሱ ቀመኛ የሆነበት ችሎት በመምራት እንጂነር ብርሃነመስቀል ያለጥፋቱ በሳውላ ማረሚያ አስሮ በመንከራተት ባሰራው “የማዕድን ስር ቁማርተኞች” ዘጋቢ ዶክመንተሪ ላይ ከተጋለጠው የወንጀል ተባባሪ ተጠያቂነት ለማምለጥ እየሰሩ ሲሆን ፃፃሱም፣ የክልሉ ርዕሰ መስተደድርም አፈፃፀሙን ከጀርባው ሆኖ እየተከታተሉ እንግልት በባለሀብቱ ላይ እንዲደርስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ይገኛሉ።

እንደሚታወቀው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እግዱን ማክበር እና ምስከበር፣ መፈፀም ሲገባቸዉ የፍርድ ቤቱን የእግድ ትእዛዝ የተጣለበት ምክንያት በአካል ቀርበዉ እንዲያስረዱ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ከመጣስ ባሻገር ተበዳይ ባለሀብቱን በህገወጥ መንገድ ማሳሰሩ አነጋገሪ ስለመሆኑ በትናንትናው ዘገባችን ማሳወቃችን ይታወሳል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እግዱን ማክበር እና ምስከበር፣ መፈፀም ሲገባው የፍርድ ቤቱን የእግድ ትእዛዝ ያልተከበረበት ምክንያት በአካል ቀርበዉ እንዲያስረዱ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ከመጣስ ባሻገር ተበዳይ ባለሀብቱን በህገወጥ መንገድ ማሳሰሩ አነጋጋሪ ሆኖ መቀጠሉ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ም/ኮምሽነር ጉራማይሌ ጉርኣ የተባለ የክልሉ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ቀጥታ ከኮምሽኑ እውቅና ውጪ ከርዕሰ መስተዳድሩ የሚሰጠውን ተልዕኮ ብቻ በመውሰድ በክልሉ የወንጀል ተባባሪ መሆኑ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተገልጿል።

ኮምሽኑ ሁሉንም የመንግስት መዋቅርን በመጠቀም የራሱን ቡድን ፍላጎት ለማሳካት ህገወጥ መንገድ እየተጠቀሙ የሚገኙትን የርዕሰ መስተዳድሩን ህገወጥ ትዕዛዝ ለመፈጸም ተቋማዊና ሙያዊ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በአከባቢው ህዝብ በመንግሥት ላይ ያለውን እምነት እንዲያጣ እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል።

ለአብነትም የማራ ማይነርስ ባለቤት አቶ ብርሃነ መስቀል በደሉን ወደ ፍርድ ቤት ከመዉሰዱ ባሻገር የፓርቲ ሚዲያ የሆነዉ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን መጥቶ በክልሉ ዉሃና ማዕድን ቢሮ ዉስጥ የሚፈፀመዉን ብልሽትና ሌብነት እንዲያጋልጥ አድርጓል የሚል ቂም ይዘው ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የክልሉን ፖሊስ ኮምሽን (ም/ኮምሽነር ጉራማይሌ ጉርኣ) እና ሌሎች የፍትህ ተቋማትን በመጠቀም ጉዳዩ ገና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ጉዳይ ክርክር ላይ እያለ ህግን ጥሰው ባለሀብቱን አስሮ እያሰቃየ ይገኛል።

በተጨማሪም የባለሀብቱን ሰብዓዊ መብት በጣሰ መንገድ የክልሉ ልዩ ኃይል (አድማ ብተና) ካምፕ በማሰርና ህክምና ጭምር እንዳያገኝ በማድረግ ወደ ጉዳዩ ወዳለበት ወደ ጋሞ ሳይሆን ወደ ጎፋ ከሳሽ የሆነው የክልሉ ውሃና ማዕድን ኤነርጂ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አክሊሉ አዳኝ ታናሽ ወንድም የሆነው የጎፋ ዞን ዳኛ አቶ አብራሃም አዱኛ ጉዳዩን በበላይነት እንዲመራ ተደርጎ በሳውላ ከተማ ማረሚያ እንዲጣል መደረጉ ተነግሯል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 6ኛ ንግድ ይግባኝ ችሎት መዝገብ ቁጥር 337812 በሰጠው ትዕዛዝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ እግዱን ማክበር እና ምስከበር፣ መፈፀም ሲገባቸዉ የፍርድ ቤቱን የእግድ ትእዛዝ የተጣለበት ምክንያት በአካል ቀርበዉ በቀን 04/02/2018 ዓ.ም እንዲያስረዱ አዝዟል።

ለመልስ ሰጪ ፍርድ ቤቱ ደግሞ ችሎቱ የሰጠዉ የእግድ ትእዛዝ መሰረት በስሩ ካሉት የጋሞ ዞን አስተዳደር፣ የቦረዳ ወረዳ አስተዳደር ጋር በመሆን እንዲያከብር እና እንዲያስከብር፣ እግዱ እንዲፈፀም በጥብቅ ታዟል ሲል WT Media የተመለከተው ከፍርድቤት የወጣ ስነድ ያስረዳል።

በተጨማሪም ፍርድቤቱ፦ “የፌደራል ፖሊስ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ፣ የጋሞ ዞን ፖሊስ፣ የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ በዚህ ፍርድ ቤቱ በቀን 06/08/2017 ዓ/ም እና በቀን 13/08/2017 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ የእግድ ትእዛዝ እንዲደርሳቸዉ፣ እግዱ እንዲከበር እና እንዳይጣስ ተገቢዉን ክትትልና እንዲፈፀም እንዲያደርጉ በጥብቅ ታዟል” የሚል ግልጽ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮምሽን እና የክልሉ ፍትህ ተቋማት የርዕሰ መስተዳድሩን ህገወጥ ትዕዛዝ ለመፈጸም ተቋማዊና ሙያዊ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በአከባቢው ህዝብ በመንግሥት ላይ ያለውን እምነት እንዳይጥል እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ተበዳይ ወጣት ባለሀብት ብርሀነመስቀል እንዲታሰር በማድረግ በክስ ሂደት ላይ ባለው ቦታ ገብተው በርዕሰ መስተዳድሩ ትዕዛዝ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከአምስት ባላይ ድርጅቶች እየሰሩ እንደሚገኙ የዕግድ ትዕዛዝ ለመስጠት የመጡት የፈደራል ፖሊስ ከትናንት በስትያ ከቦታው አረጋግጠዋል።

ከ32 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች ያቀፈዉን ክልል ይመሩ ዘንድ ቢሾሙም ሌላዉን አካባቢ ማየት ተስኗቸዋል ተብለዉ እና ስልጣናቸዉን ተገን በማድረግ ሌብነት ዉስጥ በመዘፈቃቸዉ በተጨባጭ የሚተቹት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ ከከሰል ድንጋይ ማዕድን ጋር በተገናኘ የተፈፀመበትን በደል በፍርድ ቤት እየሞገተ የሚገኘዉን ወጣቱን የማራ ማይነርስ ባለቤትን አቶ ብርሃነ መስቀልን የባለሀብቱን ሰብዓዊ መብት በጣሰ መንገድ ከከተማ ወደ ከተማ እያዞሩ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል (አድማ ብተና) ካምፕ በማሰርና ህክምና ጭምር እንዳያገኝ በማድረግ ወደ ጉዳዩ ወዳለበት ወደ ጋሞ ሳይሆን ወደ ሳውላ ከተማ ማረሚያ እንዲጣል መደረጉ ተነግሯል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአከባቢው ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና ያላቸውን የንግዱ ማህበረሰበንና ባለሀብቶችን የማሳደድና ተረጋግተው እንዳይሰሩ እየተወሰደ የሚገኘው እርምጃ በግልጽ የከተማዋን ዕድገት ወደኋላ የመመለስ እቅድ የተሰራ እንዲሁም በህጋዊ መንገድ የተለያዩ ግዙፍ ፋብሪካ ጀምሮ እንቨስትመንት ለመስራት መሬት ተረክበው በአከባቢው ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ እንቅስቃሴ የጀመሩ ባለሀብቶች ስራ እንዲቆም መደረጉን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Ethiopia #southethiopia