ሰፈፉ፤ ሰነፉ ሶፎኒያስ …. የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባለጉዳይ የሚያስተናግደው ራሱ በከፈተዉ ዊስኪ ቤት ነው?
ደረት ኪሱ ላይ ሁሌም የማይለየዉ “መገጣጠሚያ ” ነዉ፡፡ “ለሚመለከተዉ ሁሉ” ብሎ አሊያም የተቋም ስም ክፍት አድርጎ ቀንና የደብዳቤ የወጪ ፕሮቶኮል ያልተሞላበት ደብዳቤ በብዛት ከመኪናዉ ዉስጥ አያጣም፡፡ ይህ ባህሪዉ በተለይ የቀድሞዉ ደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ እያለ የሰርክ ተግባሩ ስለመሆኑ ሁሉም ይመሰክራሉ፤ በየኮሪደሩም ያሙታል፡፡
ዉሎ አበል የማይበቃዉ፤ ከሀዋሳ አርባምንጭ ደርሶ መልስ የነዳጅ ወጪዉ ደቡብ ሱዳን አድርሶት የሚመልሰዉ ስለመሆኑ የራሱ የተቋሙ ፋይናንስ ሃላፊዎች ሲያማርሩት ይደመጣል፡፡ ከርሳም ይሉታል፡፡

እኔ ደግሞ ሰፈፍ እለዋለዉ፡፡ ስልባቦትም ጭምር ነዉ፡፡ ያለአቅሙ የተቀመጠበትን የፍትህ ቢሮ ትልቅ ሃላፊነትን በተራ ሌብነትና በማይመለከተዉ የወረዳ መዋቅር ስብሰባ ጭምር ልጋጉን እየረጨ ደስኩሮ ዉሎ አበል የሚለቃቅም ጉቦኛ፡፡ ሲያወራ ሰዉ ይመስላል፡፡ ተግባር ላይ ግን ዉሃ የማያነሳ ገለባ፡፡ በእርግጥ እርሱ ምን ያድርግ፡፡ አሸርጋጅነቱን አይቶ ጥላሁን ነዉ የሚጫወትብን፡፡
ሚሊሻ የነበረዉን ሰዉ አንስቶ የደቡብ ክልል ፍትህ ምርምር ማዕከል ላይ የሆነ ቦታ ወሸቀዉ፡፡ ከዚያ ጎትቶት ፍትህ ቢሮ ጎለተዉ፡፡ ከዚያ እንዳሻዉ ያንደባልለዋል፡፡ እሰር፤ ፍታ፤ ክሰስ፤ ክስ አቋርጥ…….. ለሁሉም የጥላሁን ህቅታ ምላሹ እሺ ነዉ፡፡ በየመሸታ ቤቱ እንደሚያንቃርረዉ ጠርሙስ ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌለዉ ነዉና በዚህ ዕድሜዉ አሽከርነት አይሰለቸዉ እርሱ፡፡
አርባምንጭ ላይ የከተመዉን የክልሉን ፀረሙስና እንዲመራ የተሾመዉ ሶፎኒያስ ከኮሚሽኑ ይልቅ ባለጉዳይ የሚያስተናግደዉ እዚያዉ አርባምንጭ ከተማ ዉስጥ ራሱ በከፈተዉ ዊስኪ ቤት ስለመሆኑ የክልሉ ባለስልጣናት ዝም ቢሉም እኔ ግን ከማጋለጥ አልቦዝንም፡፡ አዎ ሶፎኒያስ አርባምንጭ ዉስጥ ዊስኪ ቤት ከፍቶ ከባለጉዳዮቹ ጋር ለሌብነት ሲደራደር ትንሹ መስፈርት “ብላክ” ወይም “ጎልድ” ማዉረድ ነዉ፡፡ ከዚያ ወደ “ካሽ” ያድጋል፡፡
የዛሬ 7 ወር ገደማ የሶፎኒያስ መኪና ሹፌር እንደተለመደዉ አለቃዉን ቢሮዉ አስቀምጦ የመኪናዉን አፍንጫ ወደ ሶዶ አድርጎ ይከንፋል፡፡ በአለቃዉ ቶሎ አድርሰህ ተመለስ ተብሏልና ሹፌሩ ሩጫዉ ሌላ ነዉ፡፡ የሲዳማ ብሄር ተወላጁ ሹፌር በርካታ መሰል ስራዎችን ከዚህ ቀደም ሰርቷልና ወንጀሎች ሁሉ ለእርሱ ሙዝ የመላጥ ያህል ይቀሉታል፡፡
ልጁን ሲከታተል የነበረዉ ፌደራል ፖሊስ ግን የዛረዉን ጉዞ አክብዶበታል፡፡ ቁም ተባለ፡፡ አልቆምም ብሎ አሻፈረኝ አለ፡፡ ጥሶ ለመሄድም መንገድ ጀመረ፡፡ ፌደራል ፖሊሶቹም በጥይት እሩምታ መኪናዉን ከጢሻ ከተቱትና ተያዘ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሶፎኒያስ ደስታ መኪና ሲፈተሸ በህገወጥ የጦር መሳሪያ ሽጉጦች የታጨቀ፤ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን የጫነ ሆኖ ተገኘ፡፡ መኪናዉም ሹፌሩም በህግ ጥላ ስር ዋሉ፡፡ ስነምግባር የሌላቸዉ ኮሚሽነሩ ከሃላፊነታቸዉ ይነሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ የርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ቁጥር አንድ ላሽ አጎንባሽ ናቸዉና ዛሬም ድረስ “ኮሚሽነር” እየተባሉ እየተላላኩ አሉ፡፡ ….. ክፍል 2…3.. 4 ይቀጥላል! እያዝናናን ቁምነገር እናስጨብጣለን ከእኛ ጋር ይቆዩ 🙏