በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልሹ አሰራርን የሚታገሉ ግለሰቦች ላይ “ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ” የሚፈጸሙ የአፈሳ እስር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ።
በክልሉ ጌዴኦ ዞን እና ሌሎች አከባቢዎች በዚህ አካሄድ የታሰሩት፦ የመንግስት ሰራተኞች፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ እንዲሁም የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት እንደሆነ ተነግሯል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ፣ በይርጋጨፌ ወረዳና ከተማ ከነሐሴ ወር ጀምሮ በርካታ ሰዎች “ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ” እየታሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው ለWT Media የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በጌዴኦ ዞን እየተካሄዱ ያሉት የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እና መርሆችን “ያልተከተሉ” እስሮች በአፋጣኝ እንዲቆም የጌደኦ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ (ጌህዴፖ) ተወካዮች
አሳስቧል።
ለእስራት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል “ቋሚ የሕክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው” እንደሚገኙበትና ህክምና አገልግሎት እንኳን እንዳያገኙ መከልከላቸው ተገልጿል።
እስረኞቹ ከታሰሩ አንድ ወር ገደማ እየደረሰ ቢሆንም ይህ ዜና እስከወጣበት ጊዜ ድረስ “ፍርድ ቤት ያልቀረቡ” መሆናቸውን አመልክቷል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቅስ ያልፈለጉ ጉዳያቸውን በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙ የመረጃ ጠቋማችን እንዳሉት አንድ ሲቪል ሰዎችን ለመያዝ እና በወንጀል ለመጠርጠር የሚያበቃ “በቂ ህጋዊ ምክንያት መኖሩን ማረጋገጥ” እንደሚገባ ተናግረዋል።
ይህ ባልሆነበት ከህግ አሰራር ውጪ በጌዴኦ ዞን እየተፈጸሙ ያሉ እስር የማይሆን መዘዝ ይዘው የሚመጣ መሆኑን አንስቷል።
ከዲላ ከተማ ነዋሪ ከታሰሩት መካከል አቶ ጴጥሮስ ወቴ በዲላ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት እስር ቤት እንዳልሆነና በጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ በአንድት ለማደር በማይመች ክፍል ውስጥ መደረጉ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ የአይን እማኞቹ ጠቅሶ ቀደም ሲል በዞኑ ዲላ ከተማ መዋቅር ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊ እንደነበሩና ብልሽቶችን አጥብቆ የሚታገሉ እንደነበሩ ተገልጿል።
በይርጋጨፌ ወረዳና ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ ሀላፊነት ቦታዎች በፓርቲና በመንግስት ሀላፊነት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ አቶ ምትኩ ወራሳ፤ አቶ ኃይለማሪያም ጥላሁን እንዲሁም አቶ አብዮት ጄቦ በቅንነት በታማኝነት ህዝቡን እያገለገሉ የቆዩ መሆናቸው ባልተመቸው በአንድ እስር ቤት እንደሚገኙ ነው የተገለፀው።
ትዕዛዙ ከማን የተሰጠ እንደሆነ ከታሰሩ ሰዎች ቤተሰብ ባገኘነው መረጃ መሠረት በዞኑ አስተዳደሪ በዶ/ር ዝናቡ ወልዴ ከርዕሰ መስተዳደሩ ጋር ባላቸው ጥብቅ የጥቅም ግንኙነት ትዕዛዝ ተቀብለው እንደሆነ ጠቁመዋል።
ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለዞኑን አስተዳዳርና ለፖሊስ መምሪያ በእጅ ስልካቸው ሲደውል አንስተው የስብሰባ መድረክ ላይ የሚደመጠው ድምፅ እያሰሙ በመሆናቸው በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ጋሞ ዞን፣ ዎላይታ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ሌሎች አከባቢዎችም የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በሚያነሱ ዜጎች ላይ እስር፣ ግድያ፣ የንብረት ዝርፊያ እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ስለመሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዝርዝር እንመለስበታለን!!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነዋሪዎች፣ በተለይ ወጣቶች፣ ለፍትህ እና እኩል ልማት መብታቸው እንዲታገሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በተለይም የፌደራል መንግስት በክልሉ እየተስተዋለ ያለውን ኢፍትሃዊነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ብልሹ አሰራሮችና ሌብነት ህዝብን ከመንግሥት ወደመነጠል ደረጃ እየተሸጋገረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ WT MEDIA በደስታ ተቀብሎ ያስተናግዳል። በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media