1000072605

“የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በባለሃብቱ ኢንጅነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ላይ የመሰረቱት ክስ ፍሬ ነገር ሲጨመቅ ባለሃብቱን ለማጉላላትና በማረሚያ አክርሞ ለመበቀል ካልሆነ በቀር ጭብጡ ዉሃ የሚያነሳ አይደለም” ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግሯል፡፡

በቀዳሚነት የሙስና ወንጀል ዋና ፈፃሚ ሳይኖር ከዋና ፈፃሚዎች ጋር በድርጊት በመተባበር በሚል የቀረበዉ ክስ የት ከማን ጋር መቼ እና እንዴት የሚሉ መሰረታዉ የድርጊት ወይም ክዋኔ ዑደቱችንና ሂደቶችን የማያመላክት እጭቅ ፍረጃ እንጂ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦበት የተደራጀ ክስ አይደለም ብሏል፡፡

ሲቀጥል በፍትሃ ብሄር የወንጀል ዘዉግ ላይ የሚወድቀዉ ይህን ያህል ኪሳራ ደርሶብኛል የሚለዉ ክስም ቢሆን ግለሰቡ ከክልሉ ጋር ያለዉን አለመግባባት በዉይይትም ሆነ በድርድር ለመፍታ የሚያስችል ቀናነት በማጣቱና በደምና በአከባቢያዊነት ማሰብና መመዘን በመጀመሩ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ፍርድ ቤቶች ወስዷል ሲል ባለሙያዎቹ አስረድተዋል፡፡

ጉዳዩ በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እየታየ እያለ የፍርድ ቤት እግድ ጥሰዉ የእኛ ለሚሏቸዉና በጥቅም ለተሳሰሯቸዉ ባለሃብት ግለሰቦች/ ጥላሁን ከበደ፤ አክሊሉ አዳኝ፤ ብርሃኑ ከበደ፤ አፀደ አይዛ፤ ሄለን ዮሀንስ፤ አለማየሁ ባዉዲ፤ተፈሪ አባተና የመሳሰሉ የክልሉ ቱባ ሌቦች በስዉር ባደራጇቸዉ ማህበራት/ሊቀራመቱ የግለሰቡን ይዞታ መሸንሸን ተገቢነት የለለው ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

“ፋና ቲቪም ገመናቸዉን አሰጣ፡፡ ብርሃነመስቀልም ፋና ዶክመንተሪ ላይ በደሉን ዘረገፈ፡፡ ሀገር ጉድ አለ፡፡ ጥላሁን ጥርሱን ነከሰበት፡፡ ስልጣኑን ተገን በማድረግ ተስፈኛዉን ወጣት ማረሚያ አስገብቶ መጫወት ጀመረ፡፡ ሲጀመር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ በክስ ሂደት ላይ ያለን ጉዳይ ወደ ግልግል ዳኝነት እንዲያመራ ዳኛ መርጠዉ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ በህገ ወጥ መንገድ የተሸነሸነዉና ዕግድ የተላለፈበት ቦታ ይከበር በሚል እየጠየቀ ሳለ ባልተቋጨ ክርክር ረቺም ተረቺም ባልተለየበት ጉዳት ደርሶብኛል ብሎ መክሰስ ክሽፈት ነዉ” ብሏል፡፡

በተጨማሪም “ክልሉ ላይ ፖሊስ የጥቂት ባለስልጣን ነን ባዮች መቀለጃ ወደመሆን እየተቃረበ መጥቷል፡፡ እከሌን እሰር ሲባል የሚያስር ፍታ ሲባል የሚፈታ ተላላኪ ሆኗል፡፡ ከሙያቸዉ ይልቅ ሆዳቸዉን የሚያስቀድሙ አዛዥ ነን ባይ ደላሎች መዋቅሩን ሞልተዉታል፡፡ እናዝናለን፡፡ ፍርድ ቤቶች በአንፃራዊነት ተቋማዊ ነፃነታቸዉን ድንበር አያስደፍሩም፡፡ ጥቂቶች ቢያሸረግዱም አብዛኛዎቹ በህሊናቸዉ ይዳኛሉ፡፡ ከጳጉሜ 5ቱ ችሎትም የምንጠብቀዉ ይህንኑ ነዉ፡፡ ህዝብም ይጠብቃችኋል፡፡ ፍትህ ሲሰፍን ሀገር ነዉና የሚረካዉ” በሚል የህግ ባለሙያዎች ሀሳባቸውን አክሏል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በባለሃብቱ ኢንጅነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ላይ የመሰረቱት ክስ ፍሬ ነገር ሲጨመቅ ባለሃብቱን ለማጉላላትና በማረሚያ አክርሞ ለመበቀል ካልሆነ በቀር ጭብጡ ዉሃ የሚያነሳ አይደለም ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ገለፁ፡፡

በቀዳሚነት የሙስና ወንጀል ዋና ፈፃሚ ሳይኖር ከዋና ፈፃሚዎች ጋር በድርጊት በመተባበር በሚል የቀረበዉ ክስ የት ከማን ጋር መቼ እና እንዴት የሚሉ መሰረታዉ የድርጊት ወይም ክዋኔ ዑደቱችንና ሂደቶችን የማያመላክት እጭቅ ፍረጃ እንጂ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦበት የተደራጀ ክስ አይደለም ብሏል፡፡

ሲቀጥል በፍትሃ ብሄር የወንጀል ዘዉግ ላይ የሚወድቀዉ ይህን ያህል ኪሳራ ደርሶብኛል የሚለዉ ክስም ቢሆን ግለሰቡ ከክልሉ ጋር ያለዉን አለመግባባት በዉይይትም ሆነ በድርድር ለመፍታ የሚያስችል ቀናነት በማጣቱና በደምና በአከባቢያዊነት ማሰብና መመዘን በመጀመሩ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ፍርድ ቤቶች ወስዷል ሲል ባለሙያዎቹ አስረድተዋል፡፡

ጉዳዩ በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እየታየ እያለ የፍርድ ቤት እግድ ጥሰዉ የእኛ ለሚሏቸዉና በጥቅም ለተሳሰሯቸዉ ባለሃብት ግለሰቦች/ ጥላሁን ከበደ፤ አክሊሉ አዳኝ፤ ብርሃኑ ከበደ፤ አፀደ አይዛ፤ ሄለን ዮሀንስ፤ አለማየሁ ባዉዲ፤ተፈሪ አባተና የመሳሰሉ የክልሉ ቱባ ሌቦች በስዉር ባደራጇቸዉ ማህበራት/ሊቀራመቱ የግለሰቡን ይዞታ መሸንሸን ተገቢነት የለለው ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

“ፋና ቲቪም ገመናቸዉን አሰጣ፡፡ ብርሃነመስቀልም ፋና ዶክመንተሪ ላይ በደሉን ዘረገፈ፡፡ ሀገር ጉድ አለ፡፡ ጥላሁን ጥርሱን ነከሰበት፡፡ ስልጣኑን ተገን በማድረግ ተስፈኛዉን ወጣት ማረሚያ አስገብቶ መጫወት ጀመረ፡፡ ሲጀመር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ በክስ ሂደት ላይ ያለን ጉዳይ ወደ ግልግል ዳኝነት እንዲያመራ ዳኛ መርጠዉ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ በህገ ወጥ መንገድ የተሸነሸነዉና ዕግድ የተላለፈበት ቦታ ይከበር በሚል እየጠየቀ ሳለ ባልተቋጨ ክርክር ረቺም ተረቺም ባልተለየበት ጉዳት ደርሶብኛል ብሎ መክሰስ ክሽፈት ነዉ” ብሏል፡፡

በተጨማሪም “ክልሉ ላይ ፖሊስ የጥቂት ባለስልጣን ነን ባዮች መቀለጃ ወደመሆን እየተቃረበ መጥቷል፡፡ እከሌን እሰር ሲባል የሚያስር ፍታ ሲባል የሚፈታ ተላላኪ ሆኗል፡፡ ከሙያቸዉ ይልቅ ሆዳቸዉን የሚያስቀድሙ አዛዥ ነን ባይ ደላሎች መዋቅሩን ሞልተዉታል፡፡ እናዝናለን፡፡ ፍርድ ቤቶች በአንፃራዊነት ተቋማዊ ነፃነታቸዉን ድንበር አያስደፍሩም፡፡ ጥቂቶች ቢያሸረግዱም አብዛኛዎቹ በህሊናቸዉ ይዳኛሉ፡፡ ከጳጉሜ 5ቱ ችሎትም የምንጠብቀዉ ይህንኑ ነዉ፡፡ ህዝብም ይጠብቃችኋል፡፡ ፍትህ ሲሰፍን ሀገር ነዉና የሚረካዉ” በሚል የህግ ባለሙያዎች ሀሳባቸውን አክሏል፡፡

ሌላኛው በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ መምህርና የህግ ጠበቃ በጉዳዩ ዙሪያ ለ WT Media በሰጠው ሙያዊ ሀሳብ “በአዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 5 ላይ መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልል (አ.አ) ጨምሮ በሚኖሮ አካላት መካከል የሚከሰት ክስ የማየት ስልጣን የፌዴራል ፍ/ቤቶች ነው። የክልሉ ዐቃቤ ህግ አድራሻ ሳውላ ተከሳሽ አዲስ አበባ መሆኑ ብቻውን የክልል ፍርድ ቤትን ስልጣን ያሳጣል” ብሏል።

አክለውም “ሌላው በህገመንግስቱ አንቀጽ 80 መሠረት የውክልና ስልጣን ለክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤተት ተሰጥቷል እንዳይባል ለክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውክልና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መሆኑን ከህገመንግስቱ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል። ይህን ይዘን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣን ስንመለከት ከአስር ሚሊዮን በታች የገንዘብ ግምት ያላቸውን ጉዳዮችን ብቻ እንደሚመለከት ከአዋጁ 1234/13 አንቀጽ 11 መረዳት ይቻላል” በሚል አስረድተዋል።

ባለሙያው ሁኔታውን ሲያስረዳ “ይህ ማለት በሌላ አነጋገር ውክልና የተሰጠው የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአስር ሚሊዮን ገንዘብ መጠን የበለጠውን መዳኘት ስረ ነገር ስልጣን የለውም። የ1.3 ቢሊዮን ብር ግምት የፌዴራል ጉዳይ የማየት ብቸኛ ስረ ነገር ስልጣን የሚኖረው ተከሳሽ የሚገኝበት ፌደራል ከፍተኛ ማለትም ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት ብቻ ነው” ብሏል።

“ዐ/ህግ ክስ የከፈተ አካል የሚያስጠይቅ ነው። ሌላው በዚህ ጉዳይ ይግበኛ ወደፊት ለማቅረብ የዳኝነት ከአምስ እስከ አስር ሚሊዮን ብር በአዲሱ ህግ ያስከፍላል። በተቃራኒው መንግስት የዳኝነት ክፍያ ስለማይከፍል ተቃራኒ ወገን ለመጉዳት ግዙፍ ቁጥር ገምተው አቅርበዋል” በሚል የህግ ባለሙያው ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥቷል።

Ethiopia #southethiopia